መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2012-10-01 15:11:38
A+ A- ገጹን ለማተምየኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረትበስዊዘርላንድ ሳን ጋሎ ሲካሄድ የሰነበተው የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ምሉእ ጉባኤ መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ የተካሄደው ጉባኤ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ፣ ሥነ ምግባራዊ ነክ ጥያቄዎች ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝርከ 50ኛው ዓመት የእምነት ዓመት፣ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ሲኖዶስ በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ትንተና የተከናወነበት መሆኑ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሪዮ ጋልጋኖ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ምክልት ሊቀ መንበር፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ኤውሮጳ ማእከላዊነት ያለው የህይወቷ እንኳር እርሱም የእምነት የመንፈሳዊነት የግብረ ገብ ማእከላዊው መለያዋ ከጥንት ጀምሮ የኤውሮጳ አበው ያጎሉት የኤውሮጳ ማንነት መሠረት ዳግም ሕያው ማድረግ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ኤውሮጳ የተጋረጡባት ችግሮች ጠቅሰው መሠረታዊ መለያዋ ከመኖር የሚያግዳት ተጋርጦ ትላቀቅ ዘንድ አቢይ ጥረት ብቻ ሳይሆን ክርስትያናዊ መሠረትዋን ሕያው በማድረግ በእርሱ መንፈስ መመራት ይኖርባታል። በዚህ መንገድ ብቻ ነው ከተለያዩ ዓበይት ችግሮች ለመላቀቅ የምትችለው” ብለዋል።
“የኤውሮጳ ነጻነት በኤውሮጳ እየተኖረ ያለው ነጻነት ወንጌላዊ ነጻነት ነው፣ ስለዚህ ይህ አለ ምንም ልዩነት ለመኖር የሚያበቃው ነጻነት የፖለቲካ ውጤት አይደለም” ካሉ በኋላ “ኤውሮጳ የኤኮኖሚ ኅብረት ብቻ ሳትሆን ፖለቲካዊ ኅብረት ሊኖራትም ይገባል ይኽ ደግሞ አንድ መፍትሔ የሚያሻው ጥያቄ ነው። የኤውሮጳ አገሮች ኅብረት እኩልነት የሚጎላበት የሚከበርበት፣ አንዱ አገር በሌላው አገር ላይ ተጽእኖ የማይሆንበት እውነተኛ ኅብረት ማረጋገጥ አስፍፈላጊ ነው።” የእውነተኛይቱ ኤውሮጳ መሠረት “መንፈሳዊ መለያዋ ነው” ብለዋል። “ለኤውሮጳ ሃይማኖታዊ አድማስ ግምት መስጠት የምትችል ኤውሮጳ፣ ከገዛ እራሷ ጋር ትገናኛለች፣ ስለዚህ ኤውሮጳዊነት ከዚህ አድማስ ውጭ ለማረጋገጥና ኅብረት እንዲኖራት መሞከር ድካም ነው፣ ሃይማኖታዊ አድማስ ግምት መስጠት ማለት በሰው ልጅ በኑባሬ ያለው የህልወት እግዚአብሔር እውቅና መስጠት ማለት ነው። ይኸንን ባህርይ ወይንም አድማስ ግምት አለ መስጠት የኤወሮጳ ኅብረት ማራቅ ይሆናል” ብለዋል።
በመጨረሻም “የታወጀው የእምነት ዓመት በእያንዳንዱ ምእመን እምነትን የሚያነቃቃ በመሆኑ መለወጥን የሚጠይቅ ጸጋና አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቅም ጭምር ነው። ስለዚህ በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ የሚያገለግሉት ሁሉም የሚመለከት ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ እንዳሉትን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የቤተ ክርስትያኑ ተከታይ መሆን ያለው ደስታና የእምነት ዓመት እምነት የሚሰጠው ኃሴት የሚገለጥበት የሚመሰከርበት ዓመት ነው። እያንዳንዱ ኤወሮጳዊ ምእመን ይኸንን የእምነት አመት በሚገባ ከኖረ ኤውሮጳ የዚህ ጸጋ ውጤት ተጠቃሚ እንድትሆን ያደርጋታል። በኤውሮጳ እምነትን ማነቃቃት ማለት ክፍለ ዓለሟ ለተሟላ ውህደት ለምትከተለው ጉዞ እውነተኛውን መሠረት በማስያዝ እውነተኛው የኤውሮጳ ውህደት ቤተሰብ የሕይወት ባህል ስብአዊነት በሙላት የሚረጋገጥበት ሁኔታ መፍጠርና ይኸንን የሚደግፍ ሥርዓት ማቆም ማለት ነው” ብለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ