መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2012-10-02 15:18:19
A+ A- ገጹን ለማተምየአባ አለግራ ሥርዓተ ብፅዕናአባ ጋብርኤለ ማርያ አለግራ የተባሉ ፍራንቸስካዊ መነኵሴና የቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ ለመጀመርያ ጊዜ ቅዱስ መጽሓፍን በቻይና ቋንቋ የተረጐሙ ትናንትና ብፁዕ ተብለዋል፣ የብፅዕናቸው ሥነ ሥርዓትም በአቺረያለ ቤተ ክርስትያን አደባባይ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛን ወክለው እዛ በተገኙ የቅዱሳን ጉዳይ የምትከታተል ማኅበር ኃላፊ በሆኑ በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ተፈጸመ፣ በሥርዓቱ የፓለርሞ ሊቀ ጳጳስ እና የሲቺልያ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል፤ የሆንግ ኮንግ ካዲናል ጆን ቶንግ ሆን፤ የንኡሳን አኃው ካፑቺኒ ማኅበር ጠቅላይ ኃላፊ ጥቀ ክቡር አባ ኾዘ ሮድሪገዝ ካርባሎ እና ከሲቺልያ ሃገረ ስብከቶች የተሰበሰቡ ብዙ ምእመናን ተገኝተዋል፣
ብፁዕ አባ ጋብር ኤለ ማርያ አለግራ በሲቺልያ አከባቢ ሳን ጆቫኒ ላ ፑንታ በምትባል ከተማ በካታንያ ክፍለ ሃገር በ1907 ዓም ተወለደ፣ በ23 ዓመት ዕድሜው የን ኡሳን አኃው ካፑቺኒ ማኅበር ካህን ሆነ፤ ለስብከተ ወንጌል ቻይና ሂዶ በፐኪኖ ከተማ የፍራንቸስካውያን የቅዱስ መጽሐፍ ጥናት ትምህርት ቤት መሥረተዋል፣ ከዛ በውግያ ምክንያት ወደ ሆንግ ኮንግ ተሸጋግረዋል፣ ለ26 ዓመታት በትጋትና ጥራት ሰርተው ቅዱስ መጽሓፍን ወደ ቻይና ቋንቋ ተርጉመዋል፣ በ1976 ዓም በቅዱሳን ሞት ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፣ ቤተ ክርስትያንም ሕይወታቸውን እና የነበራቸውን መንፈሳውያን ኃይላት መርምራና አጥንታ በትናንትናው ዕለት ስማቸውን በብፅ ዕና ደረጃ በመዝገበ ቅዱሳን አሰፈረችው፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ