መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ባህልን ኅብረተ-ሰብን >  2012-10-03 14:23:10
A+ A- ገጹን ለማተም47ኛው የኢጣሊያ ብሔራዊ የማኅበራዊ ሳምንትእ.ኤ.አ. ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ብሔራው የማኅብራዊ ሳምንት ትኩረት በቤተሰብ ዙሪያ መሆኑ በኢጣሊያ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች የማኅበራዊ ሳምንት አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የካሊያሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አሪጎ ሚሊዮና የቶሪኖ RealAudioMP3 ሊቀ ጳጳስ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ኖሲሊያና የቶሪኖ ከተማ ከንቲባ ፒየሮ ፋሲኖ ትላትና በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ብፁዕ አቡነ ሚሊዮና “ቤተሰብ ለኅብረተሰብ እስትንፋስ ተስፋ እና መጻኢ በመሆኑ፣ በኤኮኖሚው ረገድ እንደሚባለውም ቤተሰብ ኤኮኖሚያዊ ሃብት ነው ከሚለው አገላለጥ በፊት ቤተሰብ የኅብረሰብ መሠረት ሲሆን፣ በኅብረተሰብ ዘንድ የቤተሰብ መብትና ክብር የሚያስተጋባ ትርጉም ነው። ስለዚህ ቤተሰብ ሲባል በሚሥጢረ ተክሊል እውን የሚሆን ቤተሰብ እርሱም በአንድ ወንድና አንዲት ሴት መካከል የሚጸና ከሁለት ወደ አንድነት የሚያሸጋግር ጸጋ መሆኑ” በመግለጥ፣ የኢጣሊያ የኅብረተሰ ሳምንት ማእከል የሚያደርገው ቤተሰብ መለያውን አመልክተዋል።
በዚህ በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በኤኮኖሚ ቀውስ እጅግ በተጠቃበት ወቅት የዚህ ችግር እጅግ ተጥቂው የኅብረተሰብ ክፍል ቤተሰብ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ቤተሰብ መደገፍና ለቤተሰብ የተሟላ ትብብር ማቅረብ ኅብረተሰብ መደገፍ ማለት መሆኑ ብፁዕነታቸው አብራርተው፣ እያንዳንዱ ዜጋ የቤተሰብ ሃብት ነው። ቤተሰብ የኅብረተሰብ ሃብት ነው። ይኽ ሃብት በሰብአዊ መሆን ላይ የጸና ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ በአምራችነት እርሱም በኤኮኖሚ ረገድ መለካት የለበት። የሰው ልጅ መለኪያው የታደለው ሰብአዊነቱ መሆኑ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ