መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ናይ ፍቕሪ ሥራሕን ምትኅብባርን  >  2013-05-13 15:50:56
A+ A- ገጹን ለማተምሉርድ ዲያቆናዊ መንፈስ 2013 ዓ.ም.RealAudioMP3 በላቲን ሥርዓት በተከበረው በበዓለ ዕርገት እ.ኤ.አ. ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በፈረንሳይ ሉርድ፦ “ዲያቆናዊ 2013 ዓ.ም. ወንድማማችነትን ለማገልገል፣ ቤተ ክርስቲያናዊነታችን ከድኾች ጋር በመሆ” በሚል ቃል ተመርቶ የውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካዲናል ሮበርት ሳራሕ በቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ባዚሊካ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተከፈተው በፈረንሳይ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮዋ በጥልቅ የምትገመግምበት ብሔራዊ ጉባኤ ትላትና እሁድ መጠናቀቁ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ኅትመቱ አስታውቀዋል።
በዚህ 12 ሺሕ ተጋብእያን ያሳተፈው ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ሳራሕ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ “ሐዋርያዊ አገልግሎት ወይንም ሐዋርያዊነት ለክርስቲያን አማራጭ ወይንም ታካይ ተግባር ሳይሆን ሁሉም በተሰማራበት ሙያ የሚኖረው ክርስቲያናዊ ጥሪ ነው። ስለዚህ ለሁሉም የእግዚአብሔር ፍቅርና ቅርበት የሚመሰክርበት ለሚሰቃዩት በድኽነት ለሚገኙት የእግዚአብሔር በቤተ ክስቲያን ቅርበት ለመመስከር መጠራት አማራጭ አይደለም። ክርስቲያን ይኸንን ፍቅር የሚመሰክር ነው” እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ገለጠ።
የላ ሮኸለ አት ሳይንተስ ሊቀ ጳጳስ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የትብብርና የድጋፍ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ በርናርድ ሁሰት ወድማማችችነትና ቤተ ክርስቲያዊነት ላይ ባተኮረ ንግግር ጉባኤውን እንዳስጀመሩ የገለጠው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አክሎ በዚህ ለሦስት ቀናት በቀጠለው ጉባኤ በፈረንሳይ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ቨንቱራ መሳተፋቸውና ትላትና የጉባኤ መዝጊያ መሥዋዕተ ቅዳሴ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የፓሪስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንድረ ቪንግት ትሮይስ የተካሄደው ጉባኤ ፍፃሜ የረቀቀው ሰነድ አስደግፈው ባሰሙት ስብከት ዲያቆናዊነት የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የአባላቶቿ ጥሪ መሆኑ በማብራራት በፈረንሳይ ይኽ ዓይነቱ ጉባኤ እንዲካሄድ ያነቃቃውም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ Deus caritas est-እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት አዋዲ መልእክት መሆኑ በማስታወስም፣ ዓዋዲ መልእክቱ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ፦ “ቃለ እግዚአብሔር ማበሠር፣ ቅዱሳት ምሥጢራትን መሥራትና የሚሠዋ ፍቅር አገልግሎት” የሚል መሆኑ የተሰመረበት ቅዉም ሃሳብ እንደተነተኑም አስታውቀዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ