መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-05-13 15:37:45
A+ A- ገጹን ለማተምቅድስት ድንግል ማርያም ትረዳን ዘንድ እንተባበራትRealAudioMP3 ዓለም አቀፋዊው “የማርያም ራዲዮ-Radio Maria” ያዘጋጀው አንደኛው ዓለም አቀፍ ማሪያቶና ይኽም በተለያዩ አገሮች የማርያም ራዲዮ ጣቢያ ለማቆም ለሚደረገው ጥረት በመንፈሳዊና በቁሳዊ ረገድ ለማበረታታት ለሚደረገው የራዲዮ ማሪያ ስርጭቱን መስፋፋት እንቅስቃሴ ቅድስት ድንግል ማርያም ትረዳን ዘንድ እንርዳት በሚል ቃል ተመርቶ ሲካሄድ የሰነበተው መርሃ ግብር ትላትና እሁድ እ.ኤ.አ. ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቀጥታ በዚህ በ 64 አገሮች በአምስቱ ክፍለ ዓለም በሚገኘው በራዲዮ ማሪያ በኩል ባስተላለፉት ሥልጣናዊ መልእክት፦ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በተለይ ደግሞ ውድ አረጋውያን፣ በተለያየ ምክንያት ለብቻችሁ ተገልላችሁ ተነጥላችሁ የምትኖሩት ውዶቼ፣ በወህኒ ቤት የምትገኙት የተጨቆናችሁት በድኽነት ጫንቃ ሥር የምትገኙት በኅመም የምትሰቃዩት ውዶቼ ሁሉ፣ በቫቲካን ረዲዮ በኩል የሮማ ጳጳስ ድምጽ ወደ ሁሉ ዓለም ይደርሳል፣ በዚህ አጋጣሚም በራዲዮ ማሪያ በኵል ይኸው ሞትን አሸንፎ የተነሳው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰጠን ፍቅርና ተስፋ ለሁላችሁ ቅርበቴ በማረጋገጥ በፍቅሩና በተስፋው ከናንተ ጋር ነኝ በዚህ በተባረከው የራዲዮ ማሪያ ቤተሰብ ባዘጋጀው አንደኛው የማሪያቶና መርሃ ግብር ሁሉንም መልካም ፈቃድ ያላቸው በዚህ ወንጌላዊ ልኡክነት በአምስቱ ክፍለ ዓለም በ 65 አገሮች መንፈሳዊ ሥርጭቱን የሚዘረጋው ራዲዮ ማሪያ የሚሳተፉ ሁሉ በርቱ እላለሁ” በማለት ሐዋርያዊ ቡራኬ መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ