መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ባህልን ኅብረተ-ሰብን >  2013-05-13 15:46:57
A+ A- ገጹን ለማተምየሕይወት ባህል ማስፋፋትና ማረጋገጥRealAudioMP3 ትላትና በመላ ኤውሮጳ የሕይወት ባህል ለማረጋገጥ ታልሞ የተነቃቃው ኤውሮጳዊ ስለ ሕይወት ቀን “እንደኛ ነው” በሚል መርህ ቃል ተሸኝቶ ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ። ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲከበርና በተለይ ደግሞ ጽንስ ማስወረድ በሚል ውሳኔ ሥር የሚሰበከው የሞት ባህል በሕይወት ባህል አማካኝነት አስወግዶ ሁሉም ስለ ሕይወት ይቆም ዘንድ የሚጠራ ዕለት መሆኑ ሲገለጥ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በሮማ ኤውሮጳ መንበረ ጥበብ ሕገ መንግሥታዊ የሰብአዊ መብትና ክብር ጉዳይ መምህር የሥነ ሕግና የሥነ ሰብአዊ መብትና ክብር ሊቅ ፕሮፈሰር ፊሊፖ ቫሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ይኽ ስለ ሕይወት የተሰየመው ቀን ሁሉም ከሚከተለው ሃይማኖትና ፖለቲካዊ ርእዮት ውጭ ሕይወት ክብር መሆኑ የሚመሰከርበት ቀን ነው። ስለዚህ ገና ሳይወለዱ ጽንስ በማስወረድ ለሞት የሚዳረጉት የሚታሰቡበትና ለዚህ የሞት ባህል አደጋ የተጋለጡት ያላቸውን የሕይወት መብት ለመመስከር ብሎም ይኽ መብታቸው በማንም እንዳይረገጥ ለሁሉም የሕይወት መልእክት የሚተላለፍበት ዕለት ነው ብለዋል።
በመላ የኤውሮጳ አገሮች የሕይወት ባህል ለማነቃቃትና ጽንስ ማስወረድ የሚባለው በሕግ የተፈቀደ ሆኖ በአንዳንድ አገሮች የሚፈጸመው የቅትለት ተግባር ጸረ ሰብአዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የሕይወት ባለ ቤት አለ መሆኑ አውቆ ሕይወት የሚሰጥ ጸጋ መሆኑ ተገንዝቦ ሕይወት ለመቀበል እንጂ ለማጥፋት የተፈጠረ አለ መሆኑ በተለያየ የሥነ ምርምር ዘርፍ ምስክርነት የሚሰጥበት የሚቀርብበት ዕለት ነው። ጽንስ ማስወረድ መብት ሊሆን አይችልም፣ የተጸነሰው ለሞት መዳረግ ወንጀል እንጂ መብት አይደለም፣ መብታችን ሕይወት ማቀብና ማክበር እንጂ መቅጨት አይደለም። ስለዚህ ማንም ፍጡር የሕይወት ባለ ቤት አይደለም ሁሉም አገሮች ከወንጀለኛ መቅጫ ሕጋቸው የሞት ፍርድ የሚለው አንቀጽ ለመሰረዝ የሚያደርጉት ጥረት ከሕይወት ባህል የመጨ ከሆነ በእውነት ጽንስ ማስወረድ የተፈቀደ ለማድረግ የሚደረገው ሂደት የሚቃወም ይሆናል፣ ስለዚህ ኤውሮጳ የሕይወት ባህል ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ነቅታ ይኽ የሕይወት ቀን የዜጎችን ኅሊና ለማነቃቃት የሚያገለግል የሕይወት ባህል ማስፋፋት አለ ምንም ልዩነት የሁሉም ኃላፊነትና የሚስተጋባበት ዕለት መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ