መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-06-08 10:23:02
A+ A- ገጹን ለማተምየር.ሊ.ጳ መርሐ ግብር፤በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት በማለት የሚታዉቁ አብዛኛውን ጊዜ ለዕረፍት በሚሆኑ የሐምሌና የነሐሴ ወር ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ባሉበት የቅድስት ማርታ እንግዳ መቀበያ እንደሚቀመጡ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ በመጣው መግለጫም ከፊታችን ሐምሌ 8 ቀን ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ ከተሰየሙ ጀምሮ በየቀኑ የተለያዩ ቡድኖችን በቅድስት ማርታ ቤተ መቅደስ በማግኘት አብረው የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚቆምም አሳስበዋል፣
የቤተ ር.ሊ.ጳ የአስተዳደር ክፍል እንዳመለከተውም በዚሁ የበጋ ወራት ቅዱስነታቸው የሚያደርግዋቸው በግል ግኑኝነት እንዲሁም በልዩ ግኑኝነቶች ሰዎችን ተቀብለው ማነጋገር አይደረጉም፣ በወርሓ ሓምሌ በሚከተሉት ቀናት ማለትም ሓምሌ 3-10-17 እና 31 ሳምንታዊ የር.ሊ.ጳ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አይደረግም፣ ነሓሴ 7 ቀን ጀምሮ በቫቲካን ከተማ ይጀምራሉ፣ ሓምሌ 14 ቀን ቅዱስነታቸው የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮንና ጸሎትን በካስተል ጋንደልፎ ከሚገኘው ሐዋርያዊ አደራሽ ይፈጽማሉ፣ ከሓምሌ 22 እስከ 29 ቀን ደግሞ 28ኛውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመምራት በብራዚል ይሰነብታሉ፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ