መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ናይ ፍቕሪ ሥራሕን ምትኅብባርን  >  2013-06-08 10:25:32
A+ A- ገጹን ለማተምየስደተኞች ጉዳይ፤ዓለማችንን አጥለቅልቆ ያለው የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጉዳይ ያሳሰባቸው የቤት ክርስትያን በለሥልጣናት በጳጳሳዊ የስደተኞችና ዘላኖች ግብረ ኖልዎ ምክር ቤት ኃልፊ ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ማርያ ቨልዮ የአንድ ልብ ወይንም ኮር ኡኑም ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራ የመሩት ከጋዜጠኞች ጋር በባቲካን የኅትመትና ዜና ክፍል አደራሽ “ክርስቶስን በስደተኞችና በኃይል በተፈናቀሉ ሰዎች እናገኘው” የሚል ደኩመንት ቀርበዋል፣ የደኩመንቱ ዓላማ ቤተ ክርስትያን እነኚህን ችግሮች ለመጋፈጥና ለስደተኞችና ተፈናቃዮች አዲስ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መምርያዎች ለመስጠት ሲሆን እንደ ደኩመንቱ ዘገባ መሠረት ከአንድ መቶ ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ከቤት ንብረታቸውና ከአገሮቻቸው ተሰደው ያሉ ሰዎች ከመንግሥታትና ከሲቪሉ ማኅበረሰብ መልስ እየተጠባበቁ መሆናቸውንም አመልክተዋል፣
ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ማርያ ቨልዮ በሰጡት መግለጫ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ይህንን የስደት ሁኔታ የሚገልጥ ደኩመንት ይጠባበቁት እንደንበርና ይዘቱም በኃይል የሚሰደዱ ሰዎች ሁኔታን እሳቸው ያቀረቡት አሽቸኳይ ግብረ መልስ የሚያስፈልጋቸው ልመናዎች እንዲሁም ፖሎቲካዊ መፍትሔዎች ተብለው የቀረቡ ብቁ አለምናቸውና ገና የእንግዳ ፍራቻ እንዳለ ይገልጣል፣
“እነኚህን ወንዶችና ሴቶች ቤታችውን ለቀው እንዲወጡ የሚያስገድድዋቸው ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው፣ ለዚህ ዓይነት ችግሮች ለመፍታትም መንግሥታት ዘወተር ከሚከተልዋቸው ደረቅ ሕጎች ለስለስ በማለት እንዲሰሩ የሕዝቦቻቸው አስተያየትም እንዲሻሻል መርዳት አለባቸው፣ ሲሉ መጀመርያ ልቦቻቸውን ከዛ ደግሞ ድንበሮቻቸውን ለተችገሩ ሰዎች መክፈት እንዳለባቸው ከገለጡ በኋላ የሚታመን እስታቲስካዊ መረጃ ለማግኘ እንኳ አስቸጋሪ ቢሆን ከአንድ መቶ ሚልዮን በላይ በዚህ ችግር ተዘፍቀው እንዳሉ ከእነሲሁም 16 ሚልዮን የሚሆኑ በውጭ አገሮች በስደት ሲገኙ ከ28 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ በየአገሮቻቸው ተፈናቅለው አለበቂ መጠለያና መሠረታዊ ነገሮች በበረሃዎች ተጥለው በረሃብ እርዛት ብርድና በጤና ችግን ያሉ ሲሆን የባሰው ደግሞ በገዛ መንግሥቶቻቸው የሚፈናቀሉ ቦታቸውን የልማት ፕሮችግቶች በሚል ሰበብ የተነጠቁ ከ15 ሚልዮን በላይ ሲሆኑ የዘመናችን አሳፋሪና አስከፊ ሁኔታ የሚግለጥ ደግሞ ከ12 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜግነት የተነፈገባቸውና ምንም የመብት ዋስትና የሌላቸው ናቸው፣ ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ድራማ ደግሞ የሰው ልጅ ንግድ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“የሰው ልጅ ንግድ አሳፋሪ ወረርሽኝ ነው፣ ሰልጥነናል ለማለት የሚሹ ማኅበረሰቦች ሁላችን ይህንን ነገር አለምንም ቅድመ ሁኔታ ማውገዝ ያለባቸውና እንዲያበቃ ሁነኛ እርምጃ መውሰድ ግዳጃቸው ነው” ሲሉ የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጉዳይ እጅግ እንደአሳሰባቸው ገልጠዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ