መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-06-08 10:28:04
A+ A- ገጹን ለማተምየጀርመን አገራዊ የቅዱስ ቍርባን ኮንግረስ:በጀርመን በኮሎን ከተማ ከትናንትና ወዲያ የጀርመን አገራዊ የቅዱስ ቍርባን ኮንግረስ ከመላው ጀርመን በተሰበሰቡ ምእመናን በተለይ ደግሞ ወጣቶች አሸብርቆ በክፍት ሜዳ ላይ ታላቅ መንፈሳውነት የታየበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አርገዋል፣ 40 የሚሆኑ ከመላው ጀርመን የመጡ ጳጳሳት እንደተሳተፉም ከቦታው የመጣ ዜና አመልክተዋል፣ መገናኛ ቦታቸው በሪኖ ወንዝ ነበር አጋጣሚም ብዙ ዝናም ስለዘነመ አከባቢው ሁሉ በውኃ አጥልቅልቆ በመኖሩ በቅዳሴው ስለዚሁ ጉዳይም ጸሎት አሳርገዋል፣ ቅዳሴው በኁባሬ ያሳረጉ የኮሎን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ⶎአኪም መይሰር እና የጀርመን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሮበርት ዞሊሽ ነበሩ፣ በቅዳሴው ስብከት ያቀረቡ ብፁዕ አቡነ ዞሊሽ እያንዳንዱ ቍርጠኛ ውሳኔ በማድረግ ክርስትያናዊ ሕይወቱን በመኖር የክርስቶስ መል እክትን ለዘመናዊው ዓለም እንዲያደርስ አደራ ብለዋል፣
ጸሎቱና አስተንትኖው በቦታው ቀጥለዋል፣ በተለይ ደግሞ የጀርመን አገራዊ የወጣቶች ቀንም ከዚሁ ታላቅ በዓል ጋር በመተሳሰር ስለተከበረ ትናንትና ከ6 ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የተሳተፉት በብፁዕ ካርዲናል መይሰር የተመራ መሥዋዕተ ቅዳሴና የተለያዩ የትምህርተ ክርስቶስ ዝግጅቶች እንዲሁም መንፈሳዊ መዝሙሮችና አስተንትኖ የታከለበት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ተካሄደ፣ ማምሻውን ደግሞ ኤኩመኒካዊ ጸሎተ ስብሓተ ሰርክ እና ዑደት በማካሄድ በታላቅ መንፈሳውነት እንደተፈጸመ ከቦታው የደረሱ ዜናዎች አመልክተዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ