መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ፍትሕን ሰላምን >  2013-06-21 16:04:47
A+ A- ገጹን ለማተምዓለም አቀፍ የተፈናቃዮች ቀንRealAudioMP3 ትላትና በመላ ዓለም አለም አቀፍ የተፈናቃዮች ዕለት መዘከሩ ሲታወቅ ቀኑን ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ-ሙን ባስተላለፉት መልእክት በተለየዩ የዓለማችን ክልል ተፈናቅለው የሚገኙት ዜጎች ወደ መጡበት አገራችው ለመሸኘት እንዲቻል በገዛ አገራቸው የመረጋጋት ሰላም እንዲሁም የሕይወት ዋስትናና ጸጥታ እንዲረጋገጥላቸው ማድረግ ወሳኝ ነው እንዳሉ ተገልጠዋል።
በመላ ዓለም በአሁኑ ወቅት ከ 45 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ሕዝብ በተለያዩ ምክንያቶች በተለይ ደግሞ ፖሊቲካዊ ኤክኖሚያዊ ሃይማኖታዊ ጎሳዊ አድልዎ ተገዶ ቤቱንና ንብረቱን ጥሎ አገር ውስጥ ወይን በውጭ አገር ተፈናቅሎ የሚኖር መሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ካወጣው የምረጃ ሰነድ ለማወቅ ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ብቻ 7.6 ሚሊዮን ሕዝብ መፈናቀሉ ይኽ የዓለም አቅፍ ድርጅት ካወጣው ሰነድ ለመረዳት ሲቻል፣ የሕዝብ መፈናቀል ምክንያት አንዱ ጥርነትና አመጽ ሲሆን በአኃዝ ከተመለከተው የተፈናቃዩ ብዛታ 55 በመቶ ከአፍጋኒስታን ከሶማሊያ ከኢራቅ ከሲሪያና ከሱዳን በተፈናቀለው ሕዝብ የሚሸፈን መሆኑ ሲገለጥ፣ ተፈናቃዩ በብዛት የሚጎርፍባቸው አገሮች ጀርመን ፈረንሳይ ብሪጣንያ ስዊድንና ሆላንድ ሲሆኑ በኢጣሊያ በ 2012 ዓ.ም. የፖለቲካ ጥገኝነት አቅራብ ስደተኛና ተፈናቃይ ብዛት 17,352 እንደነበርም ከተባብሩት መንግሥታት ድርጅት ሰነድ ለመረዳት ተችለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ