መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-07-03 15:38:07
A+ A- ገጹን ለማተምብፁዕ ካርዲናል ቫን ቱዋን ለብፅዕና ኣዋጅ መቃረብRealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2002 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቨትናም ተወላጅ እ.ኤ.አ. በ 1975 ዓ.ም. በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ እንደተሰየሙ በቨትናም በነበረው ሥርዓት ለእስር ተዳርገው 9 ዓመት በተነጠለ ዝግ ጽኑ እስር በጠቅላላ 13 ዓመት ለወህኒ ቤት ተዳርገው የተሰቃዩት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና እንዲታወጅላቸው በቨትናም በነፍስ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፍራንስዋ ኻቪየር ቫን ቷን ገድለ ታሪክና የቅድስና ገድለ ታሪክ ብሎም የመሰከሩትና የኖሩት ቅዱስ እሴት ማእከል በማድረግ የተካሄደውን ጥልቅ መንፈሳዊ ሰብአዊ ቲዮሎጊያዊ ጥናት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ፓዶቫ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ አንጦኒዮስ ባሲሊካ በሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚጠናቀቅና ከቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ በባዚሊካው የጉባኤ አዳራሽ የክቡር ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፍራንስዋ ኻቪየር ቫን ቷን እ.ኤ.አ. ከ 1968 እስከ 1973 ዓ.ም. የደረሱት ስድስት ሐዋርያዊ መልእክቶች ማእከል ያደረገ አውደ ጥናት እንደሚካሄድና እነዚህ ስድስት ሐዋርያዊ መልእክቶች በቫቲካን ማተሚያ ቤትና የፍትህና ሰላም ጉዳይ በሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት አሳቢነት ታትሞ ለንባብ መብቃቱም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የነፍሰ ኄር ብፁዕ ካሪናል ፍራንስዋ ኻቪየር ቫን ቷን የቅድስና ገድለ ታሪክ አጥኚና ብፅዕና ብሎም ቅድስና እንዲታወጅላቸው መሠረተ ሃሳብ አቅራቢ ዶክተር ቫልደርይ ሂልገማን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፍራንስዋ ኻቪየር ቫን ቷን በሕይወት ዘመናቸው በቨትናም በነበረው የኮሚኒዝም ሥርዓት መንግሥት ለእስር ተዳርገው የተሰቃዩ፣ ሆኖም ብፁዕነታቸው እምነታቸውንና ቤተ ክርስቲያንን ሳይክዱ እምነታቸውን ሳያዋውሉ በቃልና በሕይወት ወንጌልና እምነት የመሰከሩ፣ በወህኒ ቤት ታጉረውባት የነበረቸው ትንሽ ቤት የመንፍሳዊ ማእከል በማድረግ የእምነት የፍቅርና የተስፋ ሰማእት ለመሆን የበቁ ናቸው ካሉ በኋላ በእስር እያሉ ይጠባበቁዋቸው የነበሩት የወህኒ ቤት የጸጥታ ኃይል አባላት፣ እርስዎ ከእስር ነጻ ከተባሉ በተራዎት እኛን ያሳድዳሉን? ያፈቅሩናልን? በማለት ለሚያቀርቡላቸው ለነበረው ጥያቄ ክርስትና ብቀላ እያውቅም ምህረትና ፍቅር ነው፣ ስለዚህ ወንድሞቼ ናችሁ አፈቅራችኋለሁም፣ በማለት ለሚሰጡት መልስ የጸጥታ ኃይል አባላቱ ልብ ከመንካት አልፎ የነበራቸው የእምነት ጽናት ያስገርማቸው እንደነበር” ገልጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፍትህና ሰላም ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶን በበኵላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፍራንስዋ ኻቪየር ቫን ቷን የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉ መሆናቸው አስታውሰው፣ አባ ፍራንስዋ ኻቪየር ቫን ቷን ጳጳስ እንዲሆኑ ከተሰየሙ በኋል የኖላዊ አርማ በማድረግ የመረጡት Gaudium et spes-ኃሴትና ተስፋ የሚል እንደነበርና ይኽ አንዱ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ ርእስ ለሐዋርያዊ አገልግሎታቸው መርህ በማድረግ በሳቸውና በምእመናን ዘንድ እንዲኖር በማድረግ የክርስቲያን ኃሴትና ተስፋ ወንጌልና ወንጌል መኖር መሆኑ በቃልና በሕይወት የመሰከሩ የቤተ ክርስቲያን ልጅ በማለት ገልጠዋቸዋል።
የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ በበኩላቸውም ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን የተስፋ መስካሪ በተለይ በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል፣ ወንጌልና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የማህበራዊ አንቀጸ እምነት ትምህርት በቃልና በሕይወት አብሳሪና መስካሪ በመሆን ያገለገሉ ናቸው ካሉ በኋላ ብፁዕነታቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የማህበራዊ አንቀጸ እምነት ትምህርት አስተዋጽኦ ለማሰናዳት በተደረገው ጥረት ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን ጋር በመሆን ይኸንን አስትዋጽኦ በሚያጠናቅረው ድርገት አብረው እንደሠሩና በተካሄዱት የጥናት ስብሰባዎች የነበራቸው ትዕግስት ንቃትና ጥበብ የሚደነቅ መሆኑ አብራርተው፣ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ቫን ቷን መላ ሕይወታቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርና ይኸንን ፍቅር ማእከል በማድረግ የኖሩ ናቸው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ