መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-07-03 15:40:59
A+ A- ገጹን ለማተምየሃይማኖታዊ ተግባር ተንከባካቢ ተቋምRealAudioMP3 የቅድስት መንበር የሃይማኖታዊ ተግባር ተንከባካቢ ቀቋም ጠቅላይ አስተዳዳሪ ፓውሎ ቺፕሪኣኒና ምክትላቸው ማሲሞ ቱሊ ከነበራቸው ኃላፊነት በገዛ ፈቃዳችው እንደለቀቁ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ ሲያመለክት፣ ሁለቱ አካላት በዚህ የቅድስት መንበር ተቋም ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ መሆናቸው አስታውሶ፣ ከነበራቸው ኃላፊነት በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ባስተላለፉት መላክት ዘንድ ኃላፊነቱን መተቋሙና ለቅድስት መንበር እርባና በሚል ምክንያት መሆኑ አስታውቀዋል።
የዚህ የሃይማኖት ጉዳይ ተንከባካቢ ተቋም የመስተዳድር ምክር ቤትና የብፁዓን ካርዲናሎች ድርገት ሁለቱ አካላት ያቀረቡትን ኃላፊነት የማስረከብ ፍላጎት አዘል መልእክት በመቀበልና በማጽደቅ ለጊዜው ኃላፊነቱ በተቋሙ ሊቀ መንበር በዶክተር ኤርንስት ቮን ፍረይበርግ እጅ እንዲሆን መወሰኑም የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ አክሎ፣ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው የተሰናበቱት ቺፕሪያኒና ቱሊ በማስመልከት ዶክተር ፍርየበርግ ባስተላለፉት መልእክት ሁለቱ አካላት በዚህ ተቋም በማገልገል የሰጡት አስተዋጽኦ የሚመሰገን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ጉዳይ መግለጫ ጠቅሶ፣ ከኃላፊነት ስለ መልቀቅና ከዚህ ጋር አያይዞ ስለ ተወሰደው ውሳኔ የቁጠባ ማስታወቂያ ባለ ስልጣን እንዲያወቀው መደረጉም በማብራራት፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዚህ ሃይማኖታዊ ተግባር ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም ሊቀ መንበር ኤርነስት ቮን ፍረይበርግ በሎንደን ለአንድ የኢጣሊያ ባንክ ቤት የገንዘብ ሃብት እንቅስቃሴ ጉዳይ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉት በሮላንዶ ማራንቺ ምክትል አስተዳዳሪነትና ተባበሪነት የሚደገፉ ሲሆን፣ በተለያዩ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ባንክ ቤቶች ዘንድ የገንዘብ ሃብት መድንና አስከባሪ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉት አንቶኒዮ ሞንታረሲ በተቋቋመው ልዩ ድርገት በተባባሪነት እንዲያገለግሉ መሾማቸውም አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ፦ የተቋሙ ዋና አስተዳዳሪና ምክትል አስተዳዳሪ ሩቅ ባልሆነ የጊዜ ገደም ውስጥ እንደሚሸሙ በመግለጥ፣ የሃይማኖት ተግበር ተቋም እ.ኤ.አ. በ 1942 ዓ.ም. ቅድስት መንበርና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግል የተመሠረተ መሆኑና ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ግኑኝነት ያላቸው በአገረ ቫቲካንና በሕገ ቀኖና ሥር የሚመሩት ማኅበራትና ተቋማት ህጋዊ አካላት ሃብት የሚንከባከብ በአንድ የብፁዓን ካርዲናሎች ድርገት ሥር የሚመራ 114 ሠራተኞች ያሉት በልኡላዊው አገረ ቫቲካን ብቻ ብቸኛ መቀመጫ ያለው መሆኑ ያስታውሳል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ