መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-07-08 16:12:05
A+ A- ገጹን ለማተምየር ሊ ቃ ጳ ፍራንሲስ ላምፐዱሳ ጉብኝት ፡ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ማለዳ በደቡባዊ ጣልያን በሲሲሊ ክልል የምትገኘው
ደሴት ላምፐዱሳን በግል ለመጐብኘት ከሐዋርያዊ መንበራቸው ተነስተው ረፋድ ላይ በሮም ሰዓት አቁጣጠር ደሴት ላምፐዱሳ ገብተዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ደሴት ላምፐዱሳ ከመግባታቸው በፊት ባለፉት ዓመታት ከሰሜናዊ አፍሪቃ ደሴቲቱ ለመግባት ሲሞክሩ ባሕር ውስጥ ሰጥመው ለሕለፈት የተዳረጉ በብዙ ሺ የሚገመቱ አፍሪቃውያን በማሰብ የአበባ ጉንጉን በሕር ላይ ጥለዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ደሴት ላምፐዱሳ እንደገቡ ደሴቲቱ ውስጥ ተጠለው የሚገኙ አፍሪቃውያን ስደተኞች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል ። ፓፓ ፍራንሲስ ስደተኞቹን አንድ በአንድ ሰላምታ ስትቶዋቸዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባለፈው ወርሃ መጋቢት ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ከቫቲካን ሲወጡ ዛሬ የመጀመርያ ግዝያቸው ነው ።የርእሰ ሊቃነ ጳጳሱ ደሴት ላምፐዱሳ ጉብኝት ዋነኛ ዓላማው መዲተራንያን ባሕር አቋርጠው ደቡባዊ ጣልያን ለመግባት ለሕልፈት ለታደረጉ ምስኪን አፍሪቃውያን ለመጸለይ እና እዚያው ለምገኙ ለመጐብኘት ያለመ እንደሆነ ይታወቃል።የፓፓ ፍራንሲስ ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ድሆች ላይ ያተከረ እንደሚሆን እና ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ከነሱ ጐን መቆም እንደሚተበቅባት ከወዲሁ መግለጣቸው የሚታወስ ነው።ባለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ሀገራቸው እና ቀያቸው ትተው ከሰሜናዊ አፍሪቃ ወደ ኤውሮጳ የፈለሱ አፍሪቃውያን በበዙ ሺ የሚገመቱ ሲሆን ባህር ላይ ሰጥመው የቀሩም እንዲሁ በሺዎች እንደሚቆጠሩ ይታወቃል።ባለፈው ዓመት እኤአ አቆጣጠር 2012 ከሊብያ ደቡባዊ ታልያን ለመግባት ተሞከሩ 500 ስደተኞች ባሕር ላይ ሰጥመው መቅረታቸው ይታወሳል ።
የአፍሪቃውያን ስደተኞች ፍልሰት አሁንም ባለበት እንደቀጠለ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ደሴት ላምፐዱሳ ከመግባታቸው ክጥቂት ሰዓታት በፊት 165 አፍሪቃውያን ስደተኞች ከሊብያ ላምፐዱሳ መግባትቸው ተዘግበዋል።
በቱኒሲያ እና ለምፐዱሳ መካከል ያለውን ርቀት 113 ኪሎሜትር ብቻ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚሁ መስመርም በብዙ ሺ የሚገመቱ ስደተኞች ደሴት ላምፐዱሳ እንደሚገቡ ተነግረዋል።በጣልያን የስደተኞች ምክር ቤት ዳይረክተር ክሪስቶፈር ሃይን ዛሬ አቨኒረ ለተባለ ካቶሊካዊ ጋዜጣ እንደገለጡለት የፓፓ ፍራንሲስ ደሴት ላምፐዱሳ ጉብኝት ፡ በኤውሮጳ አቀፍ ደረጃ ለስደተኞች ትኩረት እንዲሰጥ የሚረዳ መልካም አጋጣሚ ነው።የዩኒሰፍ ጣልያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ተቋም የበላይ ሐላፊ ጂያኮሞ ጐረራ በበኩላቸው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ደሴት ላምፐዱሳ ጉብኝት አስመልክተው ሲናገሩ መዲተራንያን ባህር ላይ በርካታ ሕጻናት እና አርጉዝ ሴቶች ባሕር ላይ ሰጥመው መቅረታቸው አስታውሰው ጉብኝቱ ለላፉ እና ላሉ ሰብአዊ ክብራቸው መላሽ መሆኑ ገልጠዋል።
በሲሲሊ የአግሪጀንቶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ሞንተ ነግሮ እና የደሴቲቱ ከንቲባ ጁስፒና ኒኮሊኒ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።
ቅድስነታቸው አረና ወደ ተባለው የስፖርት ሜዳ ተጉዘው በሺ የሚቆተሩ ምእመናት እና ምእመናን በተገኙበት ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ባለፈው ቅርብ ግዜ ስደተኞች ባሕር ውስጥ መስጠማቸው እንደተሰማ እና ስደተኞቹ ያሳፈሩ ጀልባዎች የተስፋ ጉዞ ከማድረግ የሞት ጉዞ በማድረጋቸው ስደተኞቹ ባሕር ውስጥ ሰጥመው ቀሩ ሕይወታቸውም ጠፋ በማለት ጋዜጦች በተደጋጋሚ ለንባብ ማብቃታቸው አስታውሰው ፡ >> ልቤ ውስጥ የሚያሰቃይ እሾክ ተሰማኝ እና ወደ ደሴት ላምፐዱሳ በመሄድ ለሕልፈት ለታደረጉ እንዲጸሊ እዚያው ለተጠለሉት ለመጐብኝት እንዲሁም እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ሁኔታ እንዳይደገም ሕልናችን ለማነቃቃት መጥቻለሁ ስሉ ስብከዋል ።
በማያያዝም ለላምፐዱሳ እና ሊኖሳ ነዋሪዎች የጸጥታ ኀይሎች ለአግሪጀንቶ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ሞንተ ነግሮ ለከንቲባ ከንቲባ ጁሰፒና ኒኮሊኒ ለስደተኞቹ ያደረጋችሁት ለምታደርጉት ሰብአዊ ርዳታ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል ፓፓ ፍርንሲስ ።ደሴቲቱ ውስጥ የሚገኙ እና ዛሬ ማታ የራማዳን ጾም ለሚጅምሩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መልካም ጾም ተመንተውላቸዋል ።
የተወደዳችሁ ስድተኞች ቤተ ክርስትያን ሰብአዊ ክብር ያለው ሕይወት ታሳልፉ ዘንዳ አጠገባችሁ እንደምትቆም ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ።ቅድስነታቸው ዛሬ ረፋድ ላይ በሰድቡብዊ ጣልያን የሲሲሊ ክልል ደሴት ላምፐዱሳ በአረና የስፖርት ሜዳ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ያሰሙት ስብከት በማያያዝ አዳም ሐጢአት እንደፈጸመ እግዚአብሔር አዳምን የጠየቀው የመጅመርያ ጥያቄ አዳም የት አለህ ፣ የሚል ነበር ካሉ በኃላ ፡ አዳም አቅጣጫው አጥፍቶ ኀያል የሆነ ሁሉም ለመቆጣጠር ምሰላት ጭራሽ እግዚአብሔር ለመሆን በፍጥረት ላይ ቦታው አጣ በማላት ሰብከዋል። አያይዘው እግዚአብሔር ቃኤልን ውንድምህ አቤል የት ላላ ብሎ እንደጠየቀው አስታውሰው እግዚአብሔርን ለመተካት ማሰብ እና መፈለግ ስህተት ስህተትን ተከትሎ ሞትን ያስከትላል ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሱ ፡ ሁለቱ የእግዚአብሔር ጥያቄዎች ዛሬም ይደወላሉ ብለዋል። ዛሬም ራሴን ጨምሮ የሰው ልጅ አቅታጫው እየሳተ ነው ያሉ ፓፓ ፍራንቸስኮ በምንኖርባታ በዚች ዓለም ላይ ጥንቃቄ ይጐለናል እግዚአብሔር ለሁላችን የፈጠረው በሚገባ አልጠበቅንም ብለዋል ።
እግዚአብሔር ቃኤልን ወንድምህ የት አለ የደሙ ድምጽ እኔ ጋ ደርሰዋል ማለቱም አስምረውበታል ።የእግዚአብሄር የምረት ጥያቄ ለሁላችን ነው የወደዳችሁ ህዝበ ክርስትያን ብለዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ስብከታቸው በማያያዝ ።


ፓፓ ፍራንሲስ ስብከታቸው በማያያዝ ውድ የሆኑ እኅቶቻችን እና ውንድሞቻችን በተለያዩ ምክንያት ሀገራቸው እና ቀያቸው ጥለው ለተሻለ ሕይወት እና ሰላም እዚህ ለመድረስ ሞክረው ባሕር ላይ ሰጥመው ቀርተዋል እንዴት የሚያስዝን ነው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፡ በሕይወታቸው የቀሩስ ሰብአዊ ትብብር መስተንግዶ አጥተው የሚያለቅሱስ ለሚሰቃዩስ ምን እድርገናል ብለን ህልናችን እንመርምር በማለት አጽንኦት ሰጥተው ሰብከዋል። ይህ ሲል ግን በአጠቃላይ የሰው ሁኔታ ማለቴ ነው እንጂ የደሴት ላምፐዱሳ ነዋሪዎች ላደረጋችሁት እና ለምታደርጉት ሰብአዊ ርዳታ እና ትብብር በድጋሜ ላመሰግናቹ እወዳለሁ ብለዋል ቅድስነታቸው ።
በአጠቃላይ ሁላችን ከግብዝነት ርቀን ሰብአዊ እና የወንድማማችነት ትብብር ሰብአዊ ሐላፊነት እንዲኖረን ያስፈልጋል በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰው ክብር መሆኑ ተገንዝበን በጎ መስራት ርህርሆች መሆን ለተቸገሩ ለሚሰቀያ መቆም አለብን
ካሉ በኃላ ስብሃት ለግእዚአብሔር ይሁን በማለት ስብከታቸውን አትቀልለዋል።
ከሥርዓተ ቅዳሴ እና ከቀትር በኃላን በሰላም ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል።


Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ