መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-07-10 12:42:08
A+ A- ገጹን ለማተምዜና ዕረፍትጥቀ ክቡር አባ ገብርኤል እስጢፋኖስ በ85 ዓመት ዕድሜአቸው ትናንትና ማክሰኞ 09.07.2013 በሕመም ምክንያት በአሥመራ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣ ነፍሰ ኄር አባ ገብርኤል በቫቲካን ረድዮ በአምሓርኛና ትግርኛ ክፍል አላፊ ሆኖው ለስምንት ዓመታት አገልግለዋል፣
እ.አ.አ ጥር 23 ቀን ጥሪ 1928 ዓም በካቶሊካዊ ኤጳርቅና ከረን የሚገኝ ሽናራ በሚባል መንደር በኤርትራ ተወለዱ፣ ከስምንት ወንድማሞች ሁለተኛ ነበሩ፣ ቤተ ሰባቸው ከሕጻንነት ጀምረው ለቤተ ክርስትያን አገልግሎት ስለሰጥዋቸው በአሥመራ በደብረ ኪዳነ ምሕረት ክልል መንፈሳዊና ማኅበረሰባዊ ትምህርት እየቀሰሙ አድገዋል፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አሥመራ በነበረው ቪቶርዮ አማኑኤል ሶስተኛ የጣልያን ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፣
እ.አ.አ. በ1943 ዓም ከረን በሚገኝ ዘርአ ክህነት ገቡ፣ በከረን ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው እንዲሁም የፍልስፍናና የንባበ መለኮት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፣ እ.አ.አ. ታሕሥስ 8 ቀን 1949 ዓም ከሁለት ባልደርቦቻቸው ጋር የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመማር ቫቲካን ውስጥ ወደ ሚገኘው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ ኢትዮጵያዊ ኮለጅ ቫቲካን ተላኩ፣
እ.አ.አ ኅዳር 23 ቀን 1956 ዓም በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ገብረኢየሱስ እጅ ቫቲካን በሚገኘው በደብረ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስትያን መዓርገ ክህነት ተቀበሉ፣
እ.አ.አ ከ1958 እስከ 1962 ዓም የሕጊ ቀኖናና የሲቪላዊ ሕግ የዶክተረይት መዓርግ አግኝተዋል፣ እ.አ.አ ስኔ 12 ቀን 1962 ዓም የአሥመራ ሃገረ ስብከት ጳጳስ የነበሩ የዝክረ ጥዑም ብፁዕ አቡነ አብርሃ ፍራንስዋ ጸሓፌ ትእዛዝ ሆነው ተሾሙ፣
እ.አ.አ ጥር 7 ቀን 1963 ዓም ከሮም ወደ አሥመራ ተመልሰው በትጋትና ታታሪነት ክህነታዊ ተል እኮ አቸውን ፈጽመዋል፣ እ.አ.አ በመጋቢት ወር 1974 ዓም የዓለም አቀፍ ር እሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ የሕገ ቀኖና ኮሚሽን አባል ተሹመው ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል፣
አባ ገብርኤል በአሥመራ ሃገር ስብከት ካበረከትዋቸው ታላላቅ ነገሮች አንዱ የቍምስናዎች ትምህርት ቤቶች ማቋቋም ሲሆን ከብፁዕ አቡነ አብርሃ ጋር ጐን ለጐን ተሰልፈው ብዙ መሥዋዕት የከፈሉ ካህን መሆናቸው ይነገራል፣
እንደ የአሥመራ ሃገረ ስብከት ጸሓፌ ትእዛዝ መጠን ደግሞ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ታላቅ አበርክቶ እንዳደረጉም የቅርብ ግኑኝነት የነበራቸው ሰዎች የሚመስከሩት ጉዳይ ነው፣
ዕድሜ በመግፋትና በቂ ጤና ባለማግኘት ወደ አሥመራ እስኪመለሱ ድረስ ከስምንት ዓመታት በላይ የቫቲካን ረድዮ የአማርኛና የትግርኛ ክፍል አላፊ ሆነው አገልግለዋል፣
እግዚአብሔር ለነፍሰ ኄር አባ ገብርኤል ዘለዓለማዊ ዕረፍት ለቤተ ሰቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው እንዲሁም ምሳሌያቸውን ለሚከተሉ ውሉደ ክህነት ጽናቱን ይስጠን፣ አሜን፣
አባ ቡሩኽ ወልደጋብር
ገዳም ቫልቪሾም ዘሲታውያን
ላቲና ኢጣልያ
10 ሓምለ 2013 ዓምፈ
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ