መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ፍትሕን ሰላምን >  2013-08-02 15:30:40
A+ A- ገጹን ለማተምየስዊዘርላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫRealAudioMP3 ትላትና በስዊዘርላንድ ብሔራዊ በዓል መከበሩ ሲገለጥ፣ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፦ “የቤተ ክርስቲያን ድምጽ በኅብረተሰብ” በሚል ርእስ ሥር የሎሳና ጀነቭና ፍሪበርግ ጳጳስ የአገሪቱ ብፅዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ሞረሮድ ፊርማ የተኖርበት መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ በተላለፈው መልእክት ክርስቲያን መሆን በሁሉም መስክ ውጤት ያለው በቃልና በተግባር የሚኖር እምነት ማለት ነው። እንዲህ ካል ሆነ ግን ክርስቲያን መሆን ትርጉሙን ያጣል የሚል ሃሳብ የተብራራበት መሆኑም ሲታወቅ፣ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት በቀጥታ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር የሚማጸን ቃል የተኖረበት መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳቱ ባስተላለፉት መልእክት በማስታወስ የአንድ ኅብረተሰብ ኃያልንቱ የሚመዘንነ እጅግ ለተናቁት በድኽነት ለተጠቁት ባልተረጋጋ ሕይወት ለሚኖሩት የአገሪቱ ዜጎች ያለው የመልካም አሳቢነትና ተግባር ነው። በዚሁ ዘርፍ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አስተዋጽኦ ቀዳሚ መሆኑና ክርስቲያናዊ አመለካከትና ውሳኔ የግል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ምንም’ኳ ብዙዉን ጊዜ የማኅበረ ክርስቲያን ተግባርን ቃል ከወንጌል ቃል ጋር የማይጋጠም ሲሆን ይኽ ደግሞ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ታማኝነቱን የሚነካ ነው። ይኸንን በመገንዘብ ቤተ ክርስቲያን ብዙውን ጊዜ ይፋዊ ይቅርታን ጠይቃለች፣ ስለዚህ አንዳንዴ የካህናት የምእመናን ተግባር እንቅፋት ወንጌልን የሚያፍን ሆኖ ቢገኝም ቅሉ ይኽ ጉዳይ የወንጌል የማበሰሩ ተግባር ውድቅ አያደርግም፣ ለኅብረተሰብ እንቅፋት ሃይማኖት ሳይሆን ለሃይማኖት ቦታ የማይሰጥ ኅብረተሰብ መሆኑ የሚያብራራ መልእክት መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ