መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-08-05 16:08:54
A+ A- ገጹን ለማተምብፁዕ ካርዲናትል ቱርክሶን በጃፓንRealAudioMP3 የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶን በጃፓን እ.ኤ.አ. እስከ ነሐሴ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚቀጥል ሐዋርያዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. መጀመራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የዚህ ይፋዊ ጉብኝት መሠረታዊ ምክንያትም በሂሮሺማና ናጋሳኪ በ 1945 ዓ.ም. የተጣለው የአቶሚክ ቦምብ ፍንዳታ ያስከተለው እልቂት መታሰቢያ ምክንያት ሲሆን፣ የጃፓን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አሥር ቀናት ስለ ሰላም በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 6 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የአቶሚክ ቦምብ ሰለባ የሆኑትን ለማስታወስ ልዩ የጸሎት የባህል መርሃ ግብር መወጠኑም አስታውቀዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን ነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ሂሮሺማ በሚገኘው ካቴድራል ስለ ሰላም የረርገው መሥዋዕተ ቀዳሴ መምራታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ነሐሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገሪቱ ከሚገኙት ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ማለትም የቡድሃ የሺንቶይና የፕሮተስታንት ሃይማኖት የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያካሂዱና እ.ኤ.አ. ነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ብፁዕነታቸው ወደ ናጋሳኪ በመሄድ እዛው በሚገኘው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ማእከል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሰላም ውይይት መርሃ ግብር ተሳትፈው እዛው በሚገኘው በከተማይቱ የተዘክሮ አደባባይ በሚከናወነው የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ከተሳተፉ በኋላ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ናጋሳኪ ስለ ዓለም ሰላም የሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ አስታውቀዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ