መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ፍትሕን ሰላምን >  2013-08-07 15:46:28
A+ A- ገጹን ለማተምናይጀሪያ፦ ጸረ ሰብአዊ ጥቃትRealAudioMP3 ባለፉት ቀናት በናይጀሪያ ገዛ እራሱ ቦኮ ሃራም በማለት የሰየመው በአገሪቱ ሰሜናዊ ክልል በስፋት የሚንቀሳቀሰው አክራሪው እስላማዊ ታጣቂ ኅይልና በአገሪቱ መደበኛ ሠራዊት መካከል በተካሄደው ውጊያ 35 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ፣ ናይጀሪያ ከካሜሩን ጋር በሚያዋስነው ክልል በተካሄደው ውጊያ ጭምር አንድ የጸጥታ ኃይል አባልና 17 የአክራሪው እስላማዊ ኃይል አባላት ሕይወታቸው ሲያጡ፣ በማላም ፋቶር ክልል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ 19 ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸው ከአገሪቱ የሚሰራጩት ዜናዎች ያመለክታሉ።
ዓለም አቀፍ የጸረ ሰብአዊ ወንጀል መቅጫ ፍርድ ቤት አቃቤ ዳኛ ፋቱ በንሱዋድ በናይጀሪያ የሚንቀሳቀሰው ቦኮ ሃራም የተሰየመው አክራሪው እስላማዊ ኃይል በተመለከተ ባወጡት ይፋዊ ሰነድ፣ አክራሪው ታጣቂ ኃይል በጸረ ሰብአዊ ወንጀል የመቅጫ ህግ መሠረት የክስ መዝገብ ለመክፈት እቅድ ያላቸው እንደሚመስል ካሰራጩት ሰነድ ለመረዳት ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2009 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም. ባለው የዓመታት ገደብ ውስጥ አክራሪው እሳላምዊ ኃይል 1,200 ንጹሓን ዜጎች ለሞት መዳረጋቸውንም ሰነዱ ይጠቁማል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ