መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-08-13 19:27:08
A+ A- ገጹን ለማተምመዓርገ ጵጵስና :ባለፈው ወርሀ ሰነ 28 ቀን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አባ የማሕበረ ልዑካን ማህበር አባል አባ ቫርገስ ቶታምካራ በደቡባዊ ምዕራምብ ኢትዮጵያ የነቀምቴ ረዳት ጳጳስ መሰየማቸው የሚታወስ ነው ።
አባ ቫርገስ ቶታምካራ እኤአ በ1959 በህንድ ቶትቫ በተባለ ቦታ መወለዳቸው እና በማሕበረ ልዕካን ጥምህርታቸው ካጠናቀቁ በኃላ በ1987 መዓርገ ክህነት መቀበላቸው ይታወቃል።
አባ ቫርገሰ ቶታምካራ ዛሬ ነሐሰ 13 ቀን እዚህ ሮም ውስጥ የማሕበረ ልዑካን በርካታ ካህናት እና ጥሪ የተደረገላቸው መንፈሳውያን ማሕበራት እና ምእመናን በተገኙበት በለኦንያኑም ቤተ ክርስትያን ከብጹዕ አቡነ ሉካ ብራንዶሊኒ እጅ ቅብአተ ጵጵስና ተቀብለዋል ።
በወቅቱ ብፁዕ አቡነ ተኦዶሩስ ቫን ሩይቨን የነቀምቴ ክልል ሐዋርያዊ መስተናብር መሆናቸው ይታወቃል። በነቀምቴ ዞን ሰባት ሚልዮን 241 ሺ ህዝብ እንደሚኖር እና ከዚህ 55 ሺ 453 ካቶሊካውያን እንደሆኑ በ28 ካህናት የሚገለገሉ 91 ቆምስናዎች 85 ደናግሎች 21 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እንደሚገኙበትም ተገልጸዋል።ዛሬ ጵጵስና መዓርግ የተቀበሉ አባ ቫርገስ ቶታምካራ በኢትዮጵያ ከአስር ዓመታት በላይ ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጠታቸው ይታወቃል።

Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ