መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2013-08-16 19:08:46
A+ A- ገጹን ለማተምለግብጽ ሰላምለግብጽ ሰላም እንዲወርድና በተቀናቃኝ ኃይሎች መሃከልም ውይይት እንዲዳብር ሁላችን ለንግሥተ ሰላም ለሆነችው እመቤታችን ድንግል ማርያም እንድንለምን ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በካስተል ጋንደልፎ እኩለ ቀን ላይ ባቀረቡት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ተማጥነዋል፣
ከግብጽ የሚደርሱኝ ዜናዎች እጅግ የሚያሳቅ ዩ መሆናቸውን በማስታወስ ቅዱስነታቸው ለሕዝቡ ያላቸውን ቅርበት እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“በተከሰተው ችግር ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡና ለቤተሰቦቻቸው ለቈሰሉትንና ለሚሰቃዩት ሁሉ በጸሎቴ እንደማስባቸው ለማረጋገጥ እወዳለሁ፣ ሁላችን አብረን በዚችው በምናፈቅራት ግብጽ ሰላም እንዲወርድ ውይይት እንዲዳብርና ዕርቅ እንዲሆን እንጸልይ፣ የሰላም ንግሥት የሆነሽው እመቤታችን ድንግል ማርያም ለምኚልን፣ ሁላችን አብረን የሰላም ንግሥት የሆንሽው ማርያም ለምኚልን እንበል ሲሉ ተማጥነዋል፣
በትናንትናው የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ያስታወሱት ሌላ ጉዳይ ደግሞ የዛሬ 25 ዓመት ዝክረ ጥ ዑም ር.ሊ.ጳ ብፁዕ የሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስለ የሴት ልጆች ማንነትና ተል እኮ ያቀረቡት ሐዋርያዊ መል እክት ነው፣ መል እክቱ ሙልየሪስ ዲጚታተም የሚል ር እስ ኖሮት ስለ ሴት ልጆች መብትና ጥሪ የሚያስተምር ነበር፣ ቅዱስነታቸው የመል እክቱ ይዘት እጅግ ሃብታምና መጠናት ያለበት ስለሆነ ዛሬም ትምህርቱን እንደገና ተመልክቶ መጥናቱና ማስፋፋቱ እንደሚሻ ገልጠዋል፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ በዓመተ ማርያም በመታወጁ ሁሉንም ነገር በእመቤታችን መንጽር ስለሚመለከተው በመል እክቱ መደምደምያ ላይ የተጻፈውን ለእመቤታችን የሚቀርብ ጸሎት ሁላችን እንድንጠቀመው እንዲህ ሲሉ አሳስበዋል፣
“በዚሁ ሐዋርያዊ መል እክት ተጽፎ ያለውን ጸሎት ሁላችን ጸሎታችን እንድናደርገው ይሁን፤ በእመቤታችን ድንግል ማርያም አምሳል የቀረበውን የሴት ልጆች ሁሉ ቅዱስ መጽሓፋዊ መግለጫን እያተነተን እያንዳንድዋ የሴት ልጅ ማንነትዋና ጥሪዋን እንድታውቅ ዘንድ እንጸልይ፣ ብለዋል፣
የእመቤታችንን ሕይወት ልዩ የሚያደርገውና የሰማይ ጉዞዋን እንዴት እንደጀመረችው ሲገልጹም እንዲህ ብለዋል፣“እንደ እውነቱ ከሆነ እንደእመቤታችን ድንግል ማርያም ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ጥሪ እሺ ብለን በምንመልስበት ጊዜ ለዘለዓለማዊ ሕይወት ያቀና የሰማይ ጉዞ አችን እርምጃ ይጀምራራል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ከእርሱ ጋራ እንድንሆን ዘለዓለማዊ ሕይወትም እንድናገኝ እንዲያው የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖረን ይፍልጋል እንዲሁም ከእርሱ ጋር በቤቱ ለዘለዓለም እንድንኖር ይፈልገናል፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ በአደባባዩ የተገኙትን ሁሉ አመስገንው የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ