መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2013-08-19 19:01:23
A+ A- ገጹን ለማተምእምነትና አመጽ ተቃራኒዎች ናቸው፣ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺ ከሚቆጠሩ ም እመንና ነጋድያን ጋር አብረው የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት በግብጽ እየተካሄደ ያለው ዓመጽ እጅግ እንዳዛዘናቸው በግለጥ በአገሪቱ ንግሥተ ሰላም የሆነችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ሰላም እንድታወርድ ጸሎት አሳርገዋል፣ ዘወትር እንደሚያደርጉት የዕለቱን ቃለ ወንጌል መንሻ በማድረግም ስለ እምነት “እምነት እንደጌጥ ለመቆናጀት የምንመርጠው ሃይማኖታው አኗኗር አይደለም” ሲሉ በእውነት በተግባር ልንኖረው እንደሚያስፈልግና እምነትን ተገን አድርገው ዓመጽ ላይ ያሉ ሰዎች ታላቅ ስሕተት እንደሚፈጽሙ ምክንያቱም እምነትና ዓመጽ ፈጽመው ስለማይስማሙ በአንድነት ሊጓዙ አይችሉም ሲሉ አስተምረዋል፣ እምነት ዓመጽን ይቋወማል! እምነት ገለለተኛ አይደለችም፣ እስከ ሰማዕትነት ቆራጥ ውሳኔ ለማድረግ ያስችላል፣ ዓመጽን ያወግዛል ሲሉ ስለ እምነት ከተናገሩ በኋላ ባለፉት ቀናት በፊሊፕንስ ባጋጠመው የመርከብ አደጋ ለተጐዱ ወንገኖችንም በጸሎት አስታውሰዋል፣
ቅዱስነታቸው ስለእምነት ይዘት ሲናገሩ፤ እምነት የሕይወት መሠረታዊ ሚዛን አድርጎ የሚመርጠው እግዚአብሔርን ነው! እግዚአብሔር ደግሞ ባዶሽ አይደለም! ገለልተኛም አይደለም! እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዳስተማረን ክፋትን መካድ ለእኔ ይመቸኝ የሚለው ግላዊ ጥቅምን በመካድ ምንም እንኳ መሥዋዕትነት የሚጠይቅና ግላዊ ጥቅሞችን መካድ ቢጠይቅም መልካም ነገርን እውነትን ፍትሕን መምረጥ ያስፈልጋል፤ ለዚህም ነው በዛሬው ወንጌል ኢየሱስ ለሐዋርያት “በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፥ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ” ይላቸዋል፣ ቅዱስነታቸው ይህንን ሲገልጹ፤
“ይህ ማለት እምነት ለጌጥ ለቍንጅና የሚያዝ ነገር አይደለም፤ ኑሮን ሕይወትን የምናውብበት ጥቂት የሃይማኖት ነገር አይደለም፣ እምነት እግዚአብሔርን እንደ የሕይወት መሠረታዊ ሚዛን መምረጥን ይጠይቃል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ባዶሽ አይደለም፣ ገለልተኛም አይደለም፣ እግዚአብሔር ሁሌ አዎንታዊ ነው፣ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ ፍቅርም አዎንታዊ ነው፣ እግዚአብሔር አካል ገጽ ስም አለው፤ እግዚአብሔር ምሕረት መተማመን ራሱን የሚሰጥ ሕይወት ነው፣ ኢየሱስ በዓለማችን መጥቶ ሁሉን ከነገረንና ካሳየን በኋላ እግዚአብሔር እንደማናውቀው ሆነን ልንኖር አንችልም፤ የባሰውኑ ደግሞ ይዘት እንደሌለው ባዶሽ ሃሳባዊ ነገር ስም ብቻ ይዞ የቆመ አድርገን ልንመለከተው አይገባንም፣
“ኢየሱስ ሰላማችን ነው፤ ኢየሱስ ዕርቃችን ነው! ነገር ግን ይህ ሰላም የመቃብር ቤት ሰላም አይደለም፤ ገለልተኝነት አይደለም፣ ኢየሱስ ገለልተኛ አይደለም፣ ኢየሱስን መከተል ማለት ክፋትንና ራስ ወዳድነትን በመካድ ምንም እንኳ መሥዋዕትነት የሚጠይቅና ግላዊ ጥቅሞችን መካድ ቢጠይቅም መልካም ነገርን እውነትን ፍትሕን መምረጥ ይጠይቃል፤ ይህም ኢየሱስ ያለውን መከፋፈልን ያስከትላል! እጅግ ጽኑ የሆኑት መተሳሰሮችንም ሳይቀር ይከፋፍላል፣ እዚህ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ የሚከፋፍለው ኢየሱስ አይደለም! እርሱ ምርጫ ያቀርባል! ሚዛን ይሰጣል! ለገዛ ራስ መኖር ወይንስ ለእግዚአብሔርንና ለሌሎችን ለማገልገል መኖር ይሻል? ለእኔነቴ ማገልገልና መታዘዝ ወይስ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይሻላል? እነኚህን ምርጫዎች ካቀረበ በኋላ ቅራኔው መከፋፈሉ እንዴት እንደሆነ ተመልከቱ፣ ሲሉ ከገለጡ በኋላ ሌላ ብርቱ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ትርጓሜም እንዳለ በተለይ ደግሞ ይህንን ቃላት እንደየዓመጽ መሣርያ እንዳይሆኑ “ይህ የወንጌል ቃል ከነጭራሹ እምነትን ለማስፋፋት ዓመጽ እንድንጠቀም አይፈቅድም፣ እንዲያው የኢየሱስ ትምህርት የዚህ ተቃራኒ ነው፣ የክርስትያን ኃይል የእውነትና የፍቅር ኃይል ለማንኛውም ዓመጽ ያወግዛል፣ እምነትና ዓመጽ ፈጽመው አይስማሙም፣
“እምነትና ጽናት አብረው ይጓዛሉ፣ ክርስትያን ዓማጺ አይደለም ነገር ጽኑ ኃያል ነው፣ ይህ ኃይል ከየት ይገኛል? ብለን የጠየቅን እንደሆነ የትሕትና ኃይል ነው፤ የፍቅር ኃይል ነው፣” ካሉ በኋላ የመለያየቱና መቋወሙ ጉዳይ በኢየሱስ ጊዜም እንደነበረ ለማመልከት ደግሞ “ከኢየሱስ ቤተሰቦችም መካከል የኢየሱስ አካሄድና ስብከትን የማይቀበሉ እንደነበሩ ወንጌል ይነግረናል ሆኖም ግን ለእመቤታችን ድንግል ማርያም እምነት ምስጋና ይድረሰውና በመጨረሻ እነርሱም የመጀመርያቱ የክርስትያን ማኅበር አባላት ሆኑ” ስለዚህ አሁንም በእመቤታችን አማላጅነት መተማመንና መጸለይ እንደሚያስፈልግ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ኢየሱስን ብቻ ለመመልከትና ምንም ዋጋ ቢያስከፍልም እርሱን ዘወትር ለመከተል እንድንችል ዘንድ እመቤታችን ድንግል ማርያምን እንለምናት፣” ሲሉ ተማጥነዋል፣
ቅዱስነታቸው በዕለቱ ከነበሩ የቃለ እግዚአብሔር ንባቦች በዕብራውያን መል እክት መለስ ብለውም “በዚሁ የእምነት ዓመት ሓዋርያዊ እንደሚመክረን ትኵረታችን ወደ ኢየሱስ ማድረግ አለብን ምክንያቱም እምነት ከእርሱ ስለሚመጣ፤ በእምነት አማካኝነትም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ውሉዳዊ ግኑኝነትን እሺ አመን ብለን ስለምንቀበል ነው” ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከጸሎቱ በኋላ እምነት የነፍስ የኃይል ምንጭ መሆኑን እንደገና ገልጠው ስለፊሊፒኑ የመርከብ አደጋ ሰለባ ለሆኑትና ቤተሰቦቻቸው ጸልየው በተለይ ደግሞ ስለግብጽ ሰላም እንዲህ ብለዋል፣“በግብጽ ሰላም እንዲወርድ ጸሎታችንን እንቀጥል ሁላችን በኅብረት እንጸልይ! የሰላም ንግሥት የሆንሽ ማርያም ሆን ለምኚልን! ሁላችን እንደገና የሰላም ንግሥት የሆንሽ ማርያም ሆይ ለምኚልን” በማለት ከሕዝቡ ጋር ከጸለዩ በኋላ ለሁሉም አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ