መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-09-19 18:31:12
A+ A- ገጹን ለማተምየአባ ኾዘ ጋብርየል ብሮኸሮ ሥርዓተ ብፅዕና፤ባለፈው ቅዳሜ በአርጀንቲና የሳንታ ፈ ሊቀ ጳጳስና የአርጀንቲና ጉባኤ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኾዘ ማርያ አራንሰዶ ቅዱስነታቸውን ወክለው የአባ ኾዘ ጋብርየል ብሮኸሮ ሥር ዓተ ብፅ ዕና ፈጽመዋል፣ ቅዱስነታቸው ለብፅ ዕነታቸው በጻፉት መል እክት “የአባ ኾዘ ዓይነት እረኞች ከመካከል ተገፍተው በክልል ለሚገኙ የእግዚአብሔር ፍቅርንና ምሕረትን የሚያጓጉዙ ናቸው” ሲሉ ከድኆችና ከተነጠሉ ወገኖች ጋር በብርታት የኖረውን ባለፈው ክፍለ ዘመን ታላቅ የቅድስና ተጋድሎ ያሳልፈ አባ ኾዘን በማስታወስ ዛሬም የዛው ዓይነት ካህንትና እረኞች እንደሚያስፈልጉን አሳስበዋል፣
አባ ኾዘ ከ200 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ በሚሆነው ቍምስናቸው በበቅሎ እና በእግራቸው እየተጓዙ ከቤት ወደ ቤት እየጐበኙ የሚያስፈልጋቸው ነገር እንዳለ በመጠየቅና ለሱባኤና ለመንፈሳዊ አስተንትኖ እየጠሩ የቅዱስ ኢግንስጽዮ ዘሎዮላ መፈሳዊ ሱባኤ እያተማሩ እንዳለፉት ሁሉ አሁን ደጋግሜ በግ በግ የሚሸቱ እረኞች የምለውም የዚሁ ዓይነት እረኞች ካህናት እንደሚያስፈልጉ ለማመልከት ነው ይህም ማለት በድሆች መካከል ድኃ ሆኖ የእግዚአብሔርን ፍቅርን ለእያንዳንዱ የሚያዳርስ ነው ሲሉ ብፁዕ አባ ኾዘ ጋብርየል ብሮኸሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ መንፈሳዊ እረኝነት እንዳስተማሩ ገልጠዋል፣
ብፁዕ አባ ኾዘ ይህንን ሲያደርግ ግን ዋና የሐዋርያዊ ግብረ ተል እኮው ማእከል የነበረው ጸሎት መሆኑንም አስታውሰዋል፣ ብፁዕ አባ ኾዘ በቍምስናዋ በደረሰበት ጊዜ መጀመርያ ያደረገው ኮርዶባ በሚባለው መንፈሳው ቦታ ሁላቸው ሱባኤ እንዲያደርጉ በመጥራት ነው፣ በኮርዶባ የመንፈሳዊ ሱባኤ ማዕከል አለ፣ በዚሁ ቦታ ባለው ታላቅ መስቀል ፊት ተንበርክከው ሁሉም እንዲጸልዩ ንስሓ እንዲገቡ ያደርጉ ነበር፣ ዋናው የብፁዕ ኾዘ ታታሪነትም አደራ ከተሰጡት ነፍሳት አንዲ እንኳ እንዳትጠፋ ሌት ተቀን በሚቃጠል መንፈሳዊ ቅናት መሥራት ነበር፣ በዚህም በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ ም እመናን የጽድቅ መሣርያ እንደሆኑም ቅዱስነታቸው በመል እክታቸው ገልጠዋል፣
ሥር ዓተ ብፅ ዕናውን የፈጸሙ ስለ ቅዱሳን የምታስብ ማኅበር ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶም ስለ ብፁዕ ኾዘ ሲናገሩ፤
“ለም እመናን መልካም ነገርና ቅዳስና ሁሉንን የሰጡ ካህን ነበሩ በተለይ ደግሞ ለድሆች፣ ምንም እንኳ በኮዶባ ዪኑቨርሲቲ በፍልስፍና ሊቅነታቸውን ቢያስመሰክሩም አንገጋገራቸው ገርና ቀለል ያለ ሆኖ በአከባቢው ቋንቋና አገላለጽ ይጠቀሙ ነበር፣ በዚህም ሁላቸው የሚሉትን ይረዱትና ይጠቀሙበት ነበር፣ ስብከቱ ልባቸውን ይነካ ነበር፣ ደረቅ የሆኑ ኃጢአተኞችን ሳይቀር ንስሓ እንዲገቡ ያደርግ ነበር ሲሉ የብፁዕ አባ ኾዘ ልዩ ስጦታ ገልጠዋል፣
ብፁዕ አባ ኾዘ ለስብከተ ወንጌል ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን በሁሉ መስክ ያገልግሉ ነበር ለምሳሌ ብ1867 ዓም ላይ በኮዶባ የኮለራ ወረርሽኝ ባጋጠመ ጊዜ አባ ብሮኸሮ አለምንም ፍርኃትና ሥጋት ሕዝቡን ለመርዳት ከተረዋወጡ አንደኛ ነበሩ፣ እንዲሁም ለአብያተ ክርስትያናት እና ለቤተ መቅደሶች ሕንጸትም ከሕዝቡ ጋር በመሆን ሰርተዋል፣ ብዙ መንገዶችም ጠርገዋል፣ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ዋና ሥራውን ማለትም ስበክተ ወንጌልን አልዘነጋም፣ እንዲያው በቅዱስ ኢግናጽዮስ ዘለዮላ መንፈሳዊ ሱባኤ የተመሠረተው ስብከተ ወንጌሉ ብሮኸርያዊ ስብከተ ወንጌል ተብሎ እንዲጠራ አደረገው፣
“በቅዱስ ኤግናጽዮስ መንፈሳዊ ሱባኤ የተከናወነ ብሮኸርያዊ ስብከተ ወንጌል የነፍስ መንጽያ የመንፈሳዊ ኃይላት ትምህርት ቤት እና የመጥፎ ልማድ መቃብር ለማለት ይቻላል፣ አባ ኾዘ መንፈሳዊ ሱባኤ የእግዚአብሔር እውነት ብርሃንን ለማግኘትና የደነድኑ ልቦችም ሳይቀር በጸጋው እንዲሸነፉ የማድረግ ኃይል እንዳለው ተማምነው ይሰሩበት ነበር፣ ለወንድሞቹ ካህናትም ዘወትር በቅዱስ መዝገብ ጸንተው እንዲኖረው ቃለ እግዚአብሔርን በልግስና እንዲሰብኩ ይቅሬታ ለማለት እንዳይሰለቹ ጸሎት እያሳረጉ ጌታን እያከበሩ ምሕረት እያደረጉ ክህነታዊ አገልግሎታቸውን በደስታ እየፈጸሙ እንዲኖሩ ያሳስቡ እንነበር በመግለጥ ምሳሌያቸው ለመከተል አሳስበዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ