መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ፍትሕን ሰላምን >  2013-10-04 15:57:09
A+ A- ገጹን ለማተምብፁዕ ኣቡነ ሞንተነግሮ፦ ታዛቢ ሆኖ መቅረት ያብቃRealAudioMP3 አንዲት 500 ስደተኞች ያሳፈረች ባለ ሞተር ጀልባ በኢጣሊያ ላምፔዱሳ ደሴት ወዳለው የባህር በር ክልል እንደደረሰች በመገልበጥና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደረሰባት የቃጠሎ አደጋ ሳቢያ የብዙ ሰዎች ስደተኛ ሕይወት ለሞት አደጋ መጋለጡ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ በባርህ በሩ ክልል የነበረው የላምፔዱዛ ነዋሪ ሕዝብ ስደተኞችን ለማዳን የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ መታየቱና ስደተኛው ለመርዳት የተረባረበው የክልሉ ሕዝብ አራት ሕፃናት አንዲት እርጉዝ ወጣት የሚገኙባቸው በጠቅላላ የ 200 ሙት አካል ከባሕር ሲያወጡ በሞት አፋፍ ላይ የነበሩት የ 115 ሰዎች ሕይወት ማዳናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ሌሎች 250 ስደተኞች በባሕር ስጥመው መቅረታቸው ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ያመለክታሉ።
የደረሰው የቃጠሎ አደጋ እንደሚገመተውም ከሆነ ስደተኞች እንዲረዱና በባሕር በሩ ክልል በነበረው ሕዝብ እንዲታዩና እርዳታ ለማጋኘት ምልክት ለመስጠት አልመው የፈጠሩት ሊሆን እንደሚችል ነው የሚነገረው። የተከሰው አደጋ በመመልከትም የክልሉ የኢጣሊያ የባህር ኃይሎች ነዋሪው የክልሉ ሕዝብ ጭምር ስደተኞችን ለመርዳት መረባረባቸውም ሲገለጥ፣ ከሞት አደጋ ከተረፉት ውስጥ አንድ የቱኒዚያ ዜጋ ምናልባት የሕገ ወጥ ስደተኞች ከቦታ ቦት የሚያንቀሳቅሱ ወንጀለኞች አባል ሊሆን ይችላል በሚል ጥርጠራም በቁጥጥር ስር መዋሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ካስተላለፉት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የኢጣሊያው ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖለታኖ፦ “አእምሮን የሚነካ እጅግ የሚያሳዝን የንጹሓን እልቂት” በማለት እንደገለጡት ለማወቅ ሲቻል፣ ርእሰ ብሔር ናፖለቲኖ የኤውሮጳ ህብረት አገሮች ማኅበር በመዲትራኒያን የባህር ክልል የሚደረሰው የስደተኞች እልቂት እንዲገታ ብሎም ከቦታ ቦታ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩትን የወንጀል ቡድኖች ጸረ ሰብአዊ ተግበር ለመግታት እንዲሁም ተጠያቂዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችል በቂ ተግባር ይፈጽም ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አያይዘውም የኢጣሊያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. አንጀሊኖ አልፋኖ የኢጣሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ላዋራ ቦልድሪኒ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፔትሮ ግራሶ በበኩላቸውም በክልሉ በመገኘት ስደተኞች ጎብኝተው የደረሰው የሰው ሕይወት አደጋ በቅርብ በመመልከት፣ የተሰማቸው ጥልቅ ሃዘን ሲገለጡ መራሔ መንግሥት ኤንሪኮ ለታ፦ “የዚህ ዓይነት የሰው ልጅ ሕይወት እልቂት ለመግታት በእውነቱ ስደተኛው በሚነሳበት ክልሉ ጽኑ ቁጥጥር ወሳኝ ነው። ካልሆነ የዚህ ዓይነቱ አሰቃቂው አደጋ ለመግታቱ ያዳግታል” ሲሉ የኢጣሊያው ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካው ሰልፍ የአንድ ቀን ብሔራዊ የሓዘን ዕለት እንዲታወጅ ሃሳብ ሲያቀርቡ፣ የነጻነት ሕዝብ የተሰኘው የፖለቲካው ሰልፍ በበኩሉም የሕገ ወጥ ስደተኞች ኢጣሊያዊ ችግር ብቻ ሳይሆን ኤውሮጳን የሚመለከት ጉዳይ ነው እንዳለ ገልጠዋል።
የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ሞንተነግሮ ስለ ጉዳዩ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “እጅግ የሚዘገንነው ሞታንን መቁጠርና ይኽን ያክል ሰጠሙ ይኽን ያክል ኢጣሊያ ገቡ የሚባለው አነጋገርና ይኽ የስደተኞች ችግር የትም ከማያደርስ በኃሃዝ የመለክቱ ልማድ ተወግዶ የዚህ ዓይነቱ የንጹሐን ሕይወት ዕልቂት ዝም ብሎ መመልከቱ ሊያበቃለት ይገባል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅርቡ በላምፔዱዛ ሐውጾተ ኖልዎ ፈጽመው ከክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ከስደተኞች ጋር በመገናኘት የሰጡት ስልጣናዊ መሪ ቃል እግብር ላይ ማዋል በእውነቱ አስፈላጊ ነው። ዛሬ 80 ነገ 10…ከነገ ወዲያ 20 የሕገ ወጥ ስደተኞች በባህር ሰጠው ሞቱ ከሚባለው ሰውን በአኃዝ ብቻ የሚመለከተ ኢሰብአዊ አነጋገር መላቀቅ ያስፈላጋል፣ ስደተኛው ሕይወት ነው ታሪክም ነው፣ እንደተለመደው ቆጥሮ ዝም ሳይሆን ፍትሕ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። በማለት የሞት አደጋ ላጋጠማቸው እግዚአብሔር በመግንሥቱ እንዲቀባላቸው ተማጥነው የሰጡትን ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።
የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ “የዚህ አይነቱ የሞት አደጋ እንዳይከሰት ለስደተኞችና ተፈናቃዮች ጉዳይ በተመለከተ የሚቀርበው ጥሪ ምዕዳን በእውነቱ ተደምጦ ገቢራዊ ሆነዋል ለማለት ያዳግታል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውንም በላምፔዱዛ ሲያካሂዱ አለ ምክንያት አልነበረም” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኤማኑኤላ ካምፓኒለ አስታውቀዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ