መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2013-10-07 19:23:40
A+ A- ገጹን ለማተምየሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባ ለተሰበሰቡ ምእመናንና ነጋድያን ሶሙንን በላምፐዱሳ ለተጐዱ ወገኖች ጸሎትና ኅልና እንዲያሳርጉ አሳስበው ለጥቂት ደቂቃዎች በጸጥታ ከተጸለየ በኋላ ልባችን እንባውን ያፈስ ዘንድ እንተወው ሲሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ገለጠዋል፣ RealAudioMP3
ቅዱስነታቸው አደጋው ከደርሰ እስካሁን እየጸለዩና እያስጸለዩ እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ የዚህ ዓይነት አሰቃቂ ትራጀዲ እንዳይደገም እንዲሰሩ በዚሁ አደጋ ለተጐዱ ወገኖችና ቤተሰቦቻቸውን እንዲያጽናኑና እንዲረዱ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው፣ ሁሌ እሁድ እንደሚያደርጉት ደግሞ የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኮዝ እንደ ሰናፍጭ ፍሬ የምታህል እምነት ታህል ካለችን ሆኖም ግን እውነተኛና ገር መሆን አለበት እንጂ ይህች ታናሽ እምነት በሰው ልጆች ዘንድ ሊደረጉ የማችሉ ነገሮችን ለመፈጸም ታስችለናለች ብለዋል፣
በላምፐዱሳ ስለተጉዱ ወገኖች እንዲህ ብለዋል፣
“ከእናንተ ጋር በመሆን ባለፈው ሓሙስ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ማስታወስ እወዳለሁ፣ ለእነዚሁ ወንድሞችንና እኅቶቻችን ለሆኑ ሴቶች ውንዶች እና ሕጻናት ለአንዴ በጸጥታ ጸሎተ ኅልና እናሳርግ፣ ልባችን እንባውን እንዲያፈስ እንተወው፣ በጸጥታ እንጸልይ፣ ካሉ በኋላ ባለፉት ቀናት በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ትውልድ አገር በአሲዚ ስላሳለፉት መንፈሳዊ ንግደት በማስታወስም እንዲህ ብለዋል፣
“ሊገርማችሁ በዚሁ መካነ ንግደት በአሲዚ ለመጀመርያ ጊዜ ነው በዓመታዊ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ክብረ በዓል መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ ጸጋ የተሰጠኝ፣ ለአሲዚ ሕዝብም ስላቀረበልኝ የሞቀ አቀባበል አመሰግናለሁ፣ እጅግ አመስግናለውሁ፣ ሲሉ ባለፈው ዕለተ ዓርብ በአሲዚ ስላደረጉት መንፈሳዊ ንግደት አስታውሰዋል፣ ስለዚሁ የቅዱስነታቸው መንፈሳዊ ንግደት በዕለቱ ጠቅለል ባለ ሁኔታ አቅርበንላችሁ ነበር፣ ዛሬ ደግሞ በሰፊው እናቀርብላችኋለን፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ትናንትና እሁድ የተነበበው ወንጌል ስለ እምነት የሚመለከት ሆኖ ከወንጌለ ሉቃስ 17፡5 “ሐዋርያትም ጌታን። እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ። የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።” የሚል ነበር፣ ቅዱስነታቸው ይህንን ጥቅስ ከዓመተ እምነት ጋር በማያያዝ እንዲህ ብለዋል፣
“እኛ እንደሐዋርያት ጌታ ኢየሱስን “እምነት ጨምርልን” እንበለው፣ አዎ ጌታችን ሆን እምነታችን እጅግ ትንሽ ናት! እምነታችን ደካማና ቀሰስተኛ ናት ነገር ግን እዳለ ላንተ እናቀርበዋለን ምክንያቱም አንተ ታበራታታለህ ታሳድጋተልሀ እንዲሁም ትጨምረናለህ፣ ሁላችን አብረን እንዲህ እንበል፣ ጌታ ሆይ እምነትን በውስጣችን አሳድግልን ጨምርልን፣ (3) ጌታ እምነት ይጨምርልን፣ ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ ለዚህ ጌታ የሚመልስን በወንጌል እንደተጠቀሰው “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህችም እውነተኛና በንጹሕ ልበ ሙሉነት ከሆነ በሰው ልጅ አስተሳሰብ ሊሆኑ የማይችሉትን ነገሮች ማድረግ እንድምንችል ነው፣
“እውነት ነው! ሁላችን ገር የሆኑ ትህትና የተሞሉ ሰዎች እናውቃለን ነገር እነኚህ ሰዎች ተራሮችን ሊነቅል የሚችል ታላቅ እምነት እንዳላቸውም እናያለን፣ እጅግ አስቸጋሪ ከሆነው ኑሮ ጋር የሚጋፈጡ አባቶችንና እናቶችን እንመልከት ወይንም አንዳንድ በሽተኞች በተለይ ደግሞ በጸና የታመሙትን ስንመለከት ሊጐበኝዋቸው ለሚሄዱ ሰዎች የመንፈስ ሰላም የሚለግሱ እናያለን፣ እነኚህ ሰዎች ስለሚያደርጉት ነገር ምንም ሳይሉ እምነታቸውን ይኖራሉ፣
“ቅዱስ ወንጌልን ለሁሉም ለማዳረስ ቁጥር ስፍር የሌላቸው መሰናግክሎችን የተሻገሩ ል ኡካነ ወንጌል ወንዶችም እና የሴት ልጆች እንመልከት፣ ይህ ጉዳይ ግን ለሁላችን የሚመለከት ነው፣
“እያንዳንዳችን በዕለታዊ ኑሮው በእግዚአብሔር ኃይልና በእምነት ኃይል ለክርስቶስ መመስከር አለበት፣ ያለችን እምነት እጅግ ታናሽ ናት ነገር ግን ኃይለኛ ናት፣ በዚች ኃይልም ነው ለክርስቶስ መመስከር ያለብን፣ ስለዚህ በሕይወታችን ኑሮ ክርስትያን መሆን አለብን፣ በምሰጠው ምስክርነታችን ክርስትያን መሆን ያስፈልጋል፣ ሲሉ ስለእምነትና ተግባር ካስተማሩ በኋላ ለዚሁ የእምነት ኃይል ከየትና እንዴት ልናሳድሰው እንድምንችልም እንዲህ ሲሉ ገለጠዋል፣
“በጸሎት አድርገን ከእግዚአሔር እናሳድሰዋለን፣ ጸሎት የእምነት እስትንፋስ ነው፣ መተማመን በተሞላበት በፍቅር ግኑኝነት ውይይት ሁሌ አለ ጸሎትም ነፋሳችን ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገው ውይይት ነው፣ የጥቅምት ወር ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የተሰጠ ወር ነው፤ የመቍጠርያ ወርም ተብሎ ይጠራል፣ በተለይ ደግሞ በቅዱስ መቍጠርያ እመቤታችን ድንግል ማርያም የምትታወቀው የፖምፐይ ማርያም ዘጥቀ ቅዱስ ሮዛርዮምን መማጠን እንዳለብን እንዲህ ሲሉ አሳስበዋል፣
“በዚሁ የእናታችን የመተማመን ተግባር በመንፈሳውነት እንተባበር ከእጆችዋም መቍጠርያን እንቀበል፤ መቍጠርያ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው፣ እንዲሁም የእምነት ትምህርት ቤትም ነው ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከጸሎተ መል አከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ባለፈው ቅዳሜ በሞደና የኢጣላያ ከተማ ሥር ዓተ ብፅ ዕናው የተፈጸመ ገና ወጣት ልጅ ሳለ በ14 ዓመት ዕድሜው የዘር አ ክህነት ተማሪ በመሆኑና የክርስትና ዘርን ለማጥፋት በታጠቁት ኮሙኒስቶች የተገደለው ብፁዕ ሮላንዶ ሪቪ በማስታወስ “በዛኛው ካህናትን ለማጥፋት ታጥቀው በነበሩበትና ብርቱ ስደት ተነስቶበት በነበረው ጊዜ ምንም አበሳ የሌለበት አንዲት አበሳው የዘር አ ክህነት ቀሚስ መልበሱ ብቻ የነበረው ሮላንዶ ሰማዕት መሆኑና ያ ያኔ ሊያጠፉት ታጥቀው የተነሱበት ክርስትና እንዳበበ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ነገር ግን በኢየሱስ ያለን እምነት የዓለምን መንፈስ ያሸንፋል! ለዚሁ ወጣት ሰማዕት እግዚአብሔርን እናመስግን! የወንጌል ጅግና መስካሪ ነበር፣ ዛሬን የሱን ዕድሜ ማለት 14 ዓመት ዕድሜ ካላቸው ወጣቶች ስንቶቹ ይሆኑ ይህንን እንደምሳሌ የሚመለከቱት? ይህ ሰማዕት ወጣት ብርቱ ነበር የት እንደሚሄድም ያውቅ ነበር፤ በልቡ ውስጥ የነበረውን የኢየሱስ ፍቅር ያውቅ ነበር ለዛም ተሰዋ፣ ለወጣቶች ታላቅ ምሳሌ ነው፣ ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነውና ሰላምታ አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ጉባኤ አስተምህሮውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ቅዱስነታቸው ዘወትር እንደሚያደርጉት ወደ አስር ሚልዮን ለሚጠጉ የትዊተር ደንበኞቻቸው በተለያዩ ቋንቋዎች ስል የምሕረት ወይንም ይቅር ባይነት ኃይል እንዲህ ሲሉ አጭር መልእክት ጽፈዋል “ምሕረት የሰው ልጆችን እና ዓለምን ከኃጢአትና ከክፋት ሊያድን የሚችል ኃይል ነው፣ ይላል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ