መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2013-10-21 18:11:09
A+ A- ገጹን ለማተምየር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ፣ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረግ በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ “ሳንደክምና ሳንሰለች ጸንተን መጸለይ እንዳለብን” አሳስበዋል፣ እንዲሁም የትናንትናው እሁድ በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀን በመሆኑ የክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተል እኮ ሌሎችን ወደ ገዛ ራስ ለመሳብ የሚደረግ ስብከት እንዳልሆነም ገልጠዋል፣ በዚሁ የስብከተ ወንጌል ተል እኮ ቀንም ባለፉት ቀናት በናይጅርያ የተገደለችለውን ለስብከተ ወንጌል የተላከች ኢጣልያዊት አፍራ ማቲነሊን አስታውሰዋል፣ እንዲሁም ባለፈው ማክሰኞ በብርቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በፊልፒንስ የተጐዱት ወንገኖች በማስታወስም አጋርነታቸውን ገልጠዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው የሉቃስ ወንጌል 18 ሲሆን ሳይታክቱ ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው ስለ አንድ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር ዳኛና አንዲት መበለት የሚናገር ምሳሌ ነበር፣
ቅዱስነታቸውም በዚሁ ምሳሌ በመመርኰዝ እግዚአብሔር ገና እኛ ሳንጠይቀው ምን እንደሚያስፈልገን እንደሚያውቅ ነገር ግን ሳንታክት ዘወትር እንድንጸልይ ዘንድ ጥሪ እንደሚያቀርብልን ገልጠዋል፣ የወንጌሉን ምሳሌን ከዕለታዊ የሕይወት ኑሮ አችን ጋር በማያያዝም እንዲህ ብለውል፣
“በዕለታዊ የሕይወት ጉዞ አችን በተለይ ደግሞ በአስቸጋሪ ጊዜ ማለትም በውሳጣችንን በውጭ ካለው መጥፎ ነገር በምንታገልበት ጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ አይርቅም ዘወትር በጐናችን ነው ያለው፣ እግዚአብሔርን በጐናችን ይዘን ነው የምንታገለው፣ ለዚህ ትግል ዋነኛ መሣርያችን ጸሎት ነው፣ ጸሎትም እግዚአብሔር ጐናችን እንዳለ ያረጋግጥልናል ምሕረቱና እርዳታው ዘወትር እንደሚሸኙን ያረጋግጥልናል፣
ነገር ይህ ከጠላት ጋር የምናደርገው ትግል እጅግ ብርቱና ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ስለሆነ ት ዕግሥትና ብርታት ይጠይቃል፣ ይህ ትግል በየዕለቱ መጋፈጥ ያለብን ትግል ነው፣ ደጋፊያችንና ወገናችን እግዚአብሔር ነው በእርሱ ያለን እምነት ደግሞ ኃይላችን ነው የእምነቱ መግለጫም ጸሎት ነው፣ ምክንያቱም እምነት ከጠፋ ጸሎትም ይጠፋል እኛም በጨለማ ብቻችን ቀርተን በጨለማ እንጓዛለን፣ በጨለማ የተጓዝን እንደሆነ ደግሞ በሕይወት ጉዞ አችን እንጠፋለን፣ ሳትታክት የምታደርገው ጸሎት ከእርሱ ጋር ሆነን እንድንታገልና በየዕለቱና በየጊዜው መጥፎ ነገርን በመልካም ነገር ለማሸነፍ በሚጠራን እግዚአብሔር ያለን እምነት መግለጫ ነው፣ ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑን ብዙ እናቶች ቤተ ሰቦቻቸውን ወደፊት ለማራመድ የሚታገሉና የሚጸልዩ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የማይታክቱ እናቶች ናቸው፣
“ሁላችን እነኚህን እናቶች ዛሬ እናስታውሳቸው፣ እነዚህ እናቶች በዚሁ ተግባራቸው የእምነትና የብርታት እውነተኛ ምስክርነት ይሰጡናል፣ የጸሎት አብነትም ናቸው፣ እንዘክራቸው!
“ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ውስጥ ያበራውን የእምነት ነበልባል ማስፋፋት ያስፈልጋል፣ አባት በሆነው ፍቅርና ምሕረት በሞላው እግዚአብሔር ያለንን እምነት እናስፋፋ፣ የክርስትያን አስፍሖተ ወንጌል ጠባብ የእምነት አስተያየትና ሁሉን ወዳንተ ለመሳብ የሚደረግ ተል እኮ አይደለም ነገር ግን የዚሁ የጌታ ነበልባል ሙቀትን እንደገና የሚያነሳሳ ለሁሉ የሚያዳርስና የሚያካፍል ነው፣ ለዚሁ ተል እኮ በጸሎትና በተጨባጭ ቁሳዊ ነገር የሚረዱትን ሁሉ ለማመስገን እወዳለሁ በተለይ ደግሞ የሮማ ጳጳስ የሚያቀርበውን የአስፍሖተ ወንጌል ጥሪ ተቀብላችሁ ለምትረዱ ሁሉ አመሰግናለሁ፣ ጌታ ኢየሱስ እስከ አጽናፍ ዓለም ወንጌሉን ለመስበክ አደራ ያለውም ለዚህ ነው፣
“በዚሁ ዕለት ወንጌልን ለመስበክ በመላው ዓለም ተሰማርተው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ እየሰሩ ያሉና ሕይወታቸው መስዋዕት እያደረጉ ላሉ ሰባክያነ ወንጌል ወንዶችና ሴቶች ቅርበታችንን እንገልጻለን፣ ለዚህ ምሳሌ የምትሆነን ለብዙ ዓመታት በናይጀርያ ሰባኪተ ወንጌል በመሆን ያገለገልች ኢጣልያዊት ም እመን አፍራ ማርቲነሊ ከጥቂት ቀናት ታፍና ተወስዳ የተግደለች ሴት ክርስትያኖችና ሙስሊሞች አብረው ያለቀሱላት ምክንያቱም ሁሉም ያፈቅርዋት ነበርና፣ አፍራ ማርቲነሊ ወንጌልን በሕይወት ሰበከች በሥራዋም አንድ ተቅዋም በመሥራት መሰከረች እንዲህ በማድረግም የእምነት ነበልባሉን ለሁሉ አዳረሰች መልካም ትግልም ታገለች፣ እንዲሁም ትናንትና በቡዳፐስት ብፅ ዕናው የታወጀው የሳለስያን ምእመን ሰባኬ ወንጌል እስተፋኖ ሳንዶር ሌላ ምሳሌ ነው፣ በሃንጋሪ የነበረው የኮሙኒስት መንግሥት ሁሉን የካቶሊክ ተቅዋሞች በዘጋ ጊዜ ብፁዕ እስተፋኖ ሳንዶር ስደትን በብርታት ተጋፍጦ በ39 ዓመቱ ተገደለ፣ ሲሉ ስለ አስፍሖተ ወንጌልና እያንዳንዱ ክርስትያን በጸሎትና በተግባር መርዳት እንዳለበት እንዲሁም በቃልና በሕይወት ወንጌልን መስበክና መመስከር እንዳለበት ካሳሳቡ በኋላ ባለፈው ማክሰኞ በፊሊፒንስ ስላጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጉዱት ወገኖች ደግሞ ቅርበታቸውን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“በኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ብፊሊፕንስ ለተጉዱ ወገኖች ቅርበቴን ለመግለጥ እወዳለሁ፣ እያንዳንዳችሁም በዚሁ ግዝያት የተለያዩ ውድሞቶች ስላጋጠምዋት ውድ አገር እንድትጸልዩ ጥሪ አቀርባለሁ፣ ሲሉ ትምህታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ጸሎተ መል አከ እግዚአብሔር አሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣ ይህ በእንዲህ ሳለ በጳጳሳዊ የባህል ምክር ቤት የተዘጋጀ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አከባቢ የአንድ መቶ ሜትር እና የእምነት ሩጫ በሚል ፕሮግራም የተዘጋጀ እሽቅድድም ከተመለከቱ በኋላ በዚህ ለተሳፉት ሁሉ አመስግነው በመጨርሻ በአርጀንቲና የሚከበረውን የእናት ቀን እንዲህ ሲሉ አስታውሰዋል፣
“ዛሬ በአርጀንቲና የእናት ቀን ይከበራል በአገሬ ለሚገኙ እናቶች ልዩ ፍቅራዊ ሰላምታዬን እግለጣለሁ ሲሉ ደምድመዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ