መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-11-22 14:29:38
A+ A- ገጹን ለማተምገዳማውያንና ባሕታውያን በታሪክ ውስጥ ናቸውRealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያን “Giornata pro Orantibus-ስለ ገዳማውያን መናንያንና ባሕታውያን የጸሎት ቀን” በምታከብርበት ዕለት ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሮማ ክፍለ ከተማ አቨንቲኖ በሚገኘው የቤነዲክቱስ ካማልዶላውያን መናንያን ደናግል ገዳም ሐውጾተ ኖልዎ እንዳከናወኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኸንን ሐውጾተ ኖልዎ ከማካሄዳቸው ቀደም ብሎ የቤነዲክቱስ ከማልዶልውያን መናንያን ደናግሎች ማኅበር በአቨንቲኖ ለሚገኘው ገዳም አመ-ምኒየት እናቴ ሚከላ ፖርቸላቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሮበራታ ጂሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችንን ለመቀበል በገዳሙ የታየው ጥልቅ መንፈሳዊነት ደስታ የተሞላው ሁናቴ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር አብሮ መጸለይና መገናኘት ጸጋ መሆኑ ይመሰክራል ብለዋል።
ስለዚህ ቅዱስ አባታችንን ለመቀበል በጥልቅ ጸሎት የተሸኘ ቅድመ ዝግጅት መከናወኑ ገልጠው፣ ገዳመ ባሕታውያን የሚለው ቃል ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወዲህ እያንዳንዱ የባህታውያንና መናንያን ማኅበራት የውስጥ መስተዳድር ደንብ ከተቀበሉት የመንፈሳዊ መርህ ጸጋ ሳይወጡ እንዳደሱ በማስታወስ፣ በእርግጥ ብህትውና መንኖ ከዓለም ተለይቶ መኖር የሚለው ጥሪ የሚኖርበት ቢሆንም ቅሉ፣ ይኽ ደግሞ ውስጣዊና አካላዊ መለየትን የሚያሰማ ነገር ግን ከዓለም ውጭ ለመሆን ሳይሆን በበለጠ በታሪክ በወቅታዊው ታሪክ ውስጥ ለመኖር የሚያበቃ ነው። መለየትን የሚያሰማ ምርጫ ነው፣ ሆኖም በበለጠ ገዛ እራስን በእግዚአብሔር ጸጋና እርሱ በለገሰው ጥሪ አማካይነት የእውነተኛው ብርሃን መስካሪ ሆኖ ለመኖር የሚያበቃ ምርጫ ነው። ገዳማውያን ባሕታውያን በጥልቅ ጸሎት ምእመናን ለማሳተፍ በሰዓታት የጸሎት ሊጡርጊያ መንፈሳውያን ነጋድያን ምእመናን በማስተናገድ፣ በከፋ ድኽነት ሥር የሚገኙትን በማስተናገድ በመደገፍ የእግዚአብሔር ቃል ያበስራሉ፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ጥልቅ ጥማት የሚስተናገድበት ቤት ነው ብለዋል።
ጸሎት እምነትን ይጠይቃል፣ እምነት ከሌለ መጸለይ ትርጉም የለውም፣ ስለዚህ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ቃል አብሳሪ ጸሎት ነው። እርግጥ ነው የእግዚአብሔር መንግሥት ከማሳወቅ ገዛ እራሳችንን ለማሳወቅ እንራወጣለን፣ ስለዚህ የመናንያነት ባህል ጸሎትና ሥራ በማዋኃድ በጽሞናና በብሕትውና ሕይወት አማካኝነት ገዛ እራስ ለማንጻት ለእግዚአብሔር ጸጋ ለም መሬት በመሆን አስፍሆተ ወንጌል የሚኖርበት ሕይወት እንጂ ገለልተኛነት ማለት አይደለም። በውስጣችን ቦግ በሚለው የክርስቶስ ብርሃን ዕለት በዕለት በጸሎትና በሥራ እየተመሩ ለመኖር የሚየደፍ የጥሪ ጸጋ ነው። የብሕትውና ሕይወት ጉዞ ቀላል አይደለም ምክንያቱም ጥልቅ እምነትና ገዛ እራስ ዝቅ ማድረግን መቅበርን ይጠይቃል፣ ጸሎት ከጌታ ጋር ጥልቅ የፍቅር ግኑኝነት ማለት ነው ብለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ