መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2013-11-25 18:51:43
A+ A- ገጹን ለማተምክርስቶስ የሁሉ ማእከል ነው፣RealAudioMP3 እ.አ.አ ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓም ባለፈው ዓመት በልኂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ የታወጀው የእምነት ዓመት ትናንትና ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተዘጋ፣ ቅዱስነታቸው የእምነት ዓመት በይፋ ሲደመደም አዲስ የእምነት ጉዞ በመጀመር ላይ መሆናችንና በአዲስ መንፈስ ለመጓዝ ይረዳል ያሉት ኢቫንጀሊ ጓውድዩም በሚል ርእስ ሐዋርያዊ ምዕዳን የያዘ መል እክት አስረክበዋል፣ በአደባባዩ ከስልሳ ሺ በላይ ከአምስት የተለያዩ የዓለማችን አህጉር የመጡ ነጋድያንና ምእመናን ነበሩ፣ ቅዱስነታቸው ለቤተ ክርስትያንና ለማኅበረሰብ ተወካዮች ኢቫንጀሊ ጓውድዩም የወንጌል ደስታ የሚለው ሰነድ አስረክበዋል፣ በቅዳሴው ጊዜ የተሰበሰበው መባ ደግሞ በቅርቡ በፊሊፒነስ በአደጋ ለተጉዱ ወገኖች እንዲሆን እንደተወሰነ ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አመልክተዋል፣ በዕለቱ ከተከናወኑ ነገሮች ዋነኛ ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ቅርያት ሆነው በር.ሊ.ጳ የግል ቤተ መቅደስ ተቀምጠው የነበሩ ለሕዝብ ት ዕይንት በይፋ እንደቀረበ ተመልክተዋል፣ እነኚህ የቅዱስ ጴጥሮስ አጥንቶች በአርⷎሎጂስቶች ተመርምረው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መንበረ ታቦት ስር በተደረገው ቍፋሮና ጥናት የተገኙ ናቸው፣
ቅዱስነታችው ባደረጉት ስብከት መጀመርያ ያተኰሩበት ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ዓመት እ.አ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2012 ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ 50ኛ ዓመት በማስታወስ የከፈቱት የእምነት ዓመት ላይ ነበር፣ ለዚህ ታላቅ ሥራም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣
“ይህ ጅማሪ በእግዚአብሔር አሳቢነት የተሰጠ ሲሆን ይህም የእግዚአብሔር ልጆች እና በቤተ ክርስትያን ወንድማሞችና እኅትማሞች የሚያደርገንን ምሥጢረ ጥምቀት በተቀበልንበት ቀን የሚጀምረው የእምነት ጉዞ ጣዕምን እንደገና ለማወቅ ዕድል የሚሰጥ ነው፣ ሲሉ የእምነት ዓመት መታወጅ እጅግ አስፈላጊ መኖሩን ካመለከቱ በኋላ በሥርዓቱ ላይ የተገኙትን የምሥራቃውያን ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያን ፓትርያርኮችና ታላላቅ ሊቀ ጳጳሳት ሰላምታን ምስጋና አቀርበዋል፣
“ከእነዚህ አባቶች ጋር የምለዋወጠው ሰላምታ እነዚህ አብያተ ክርስትያን ምሳሌያዊ በሆነ መተማመን ክርስቶስን በመመስከራቸው ብዙ ጊዜ ደግሞ ታላቅ ዋጋ በመክፈል ለሮማ ጳጳስ የሰጡትን እውቅናናን ለማመስገን ነው፣ በዚሁ ሰላምታ ለሁላቸውም ክርስትያኖች በቅድሱት መሬት በሲርያና በመላው ምሥራቅ ያሉ አማንያንን የሰላምና የስምምነት ስጦታን እንዲቀበሉ ያለኝም ምኞት እገልጣለሁ፣ ሲሉ የተለዋወጡት ሰላምት ከቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና እዛ ከነበሩ ተወካዮች ባሻገር ለሁሉም የምሥራቅ አብያተ ክርስትያን አማንያን እንደሚዘረጋ ገልጠዋል፣
ከሰላምታ በኋላ ወደ የዕለቱ ቃለ እግዚአብሔር መለስ በማለት ሁሉም ንባቦች ክርስቶስ የሁሉ ማእከል መሆኑን ማለት ክርስቶስ የፍጥረት ማእከል ክርስቶስ የሕዝብ ማእከል ክርስቶስ የታሪክ ማእከል መሆኑን እንደሚገልጡ አሳስበዋል፣
“ይህንን ማእከል ያጠፋን እንደሆነ በሌላ የተካነው እንደሆነ ጥፋት ብቻ ነው የምናገኘው ይህ ጥፋትም በተፈጥሮ ላይም ይሁን በገዛ ራሱ የሰው ልጅ ነው የሚከሰተው፣ ስለዚህ ክርስቶስን የሁሉ ማእከል አድርገን ሕይወታችንን የሚያቆሙ ደስታዎቻችንና ተስፋችን ሓዘኖቻችንና ስቃዮቻችን እናቅርብለት፣
“ኢየሱስ በማእከል ላይ ሲሆን የሕይወታችን እጅግ የጨለሙ ግዝያት ይበራሉ፣ በዛሬው ወንጌል እንደተገለጠው በስተቀኝ ከኢየሱስ ጋር ተሰቅሎ የነበረው ፈያታዊ እንደተፈጸመውም ከሁሉ ባሻገር ተስፋ ይሰጠናል፣ ኢየሱስ ለፈያታዊው የምሕረት ቃል እንጂ የፍርድ ቃል አልተናገረውም፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ምሕረት የመጠየቅ ብርታትን ያገኘ እንደሆነ ኢየሱስ ይህ ጥያቄ በከንቱ እንዲቀር አይፈቅድም፣ ይቅርታውን ይሰጣል፣
“እያንዳንዳችን የገዛ ራሱ ታሪክ አለን፣ እያንዳንዳችን ስሕተቶታችን ሓጢአቶቻችን የደስታ ግዝያትና የጨለማ ግዝያት አሉን፣ በዛሬው ዕለት ታሪካችንን መለስ ብለን በማስተንተን ወደ ኢየሱስ በመመልከት በልባችን ፈያታዊው እንዳለው በጸጥታ ጌታ በመንግስትህ አስታውሰኝ! አሁን በመንግስትህ ባለህበት ወቅት ኢየሱስ ሆይ እኔን አስታውሰኝ! ሕይወትየን ለመቀየርና በጎ ክርስትያን ለመሆን እፈልጋለሁ፣ መልካም ሰው ለመሆን ታላቅ ፍላጎት አለኝ ነገር ግን ኃይል የለኝም አልችልም ኃጢአተኛ ነኝ! ሆኖም ግን ኢየሱስ ሆይ በመግሥትህ አስታውሰኝ፣ አንተ ስለኔ ለማስታወስ ትችላለህ ምክንያቱም አንተ የሕይወቴ ማእከል ነህ! በመንግሥትህ ላይ ስለሆንክ አስታውሰኝ እንበለው ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ ቅዳሴ ተፈጽሞ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ለ36 የሚሆኑ ከ18 አገሮች ለመጡ የአምስቱ አህጉር የአብያተ ክርስትያናትና ማኅበሮች ተወካዮች በዕለቱ ያቀረቡትን ሐዋርያዊ ምዕዳን ኢቫንጀሊ ጓውድዮም የወንጌል ደስታ የሚለውን ሰነድ አስረክበዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ