መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ፍትሕን ሰላምን >  2013-12-11 16:14:58
A+ A- ገጹን ለማተምዩክራይንና የአውሮፓ ኅብረትRealAudioMP3 በዩክረይን የያኑኮቪች መንግስት ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ከዚህ ቀደም የተደረሰው ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካው ስምምነት ሥር የቀረበው ውል አልፈርምም በማለቱ ምክንያት በአገሪቱ ይኸንን መንግሥት ለወሰደው ውሳኔ የሚቃወሙት የፖለቲካ ሰልፎች ያነቃቁት ሕዝባዊ አድማ በአገሪቱ አቢይ የፖለቲካ ቀውስ እያስከተለ መሆኑ ሲታወቅ፣ ይኸንን ተከስቶ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ መፍትሔ እንዲያገኝ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ያኑኮቪች ውይይት ብቸኛ መፍትሔ ነው በማለት በዚሁ ጉዳይ ላይ የሁሉም ተሳትፎ እየጠየቁ ቢሆንም ቅሉ፣ አሁም ውጥረት አለ መርገቡ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ስለ ጉዳዩ ከኡክራይን መንግሥት ጋር ለመወያየትም የኤውሮጳ ኅብረት የውጭ ግኑኝነት ተጠሪ ካተሪነ አሽቶን ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኪየቭ እንደሚገኙ መኒከቱ ያመለክታሉ።
የኡክራይን የውጭ ጉዳይ ሚኒ. መማክር ስብሰባ ማካሄዱ ሲገለጥ፣ ሕዝቡ አሁንም በአገሪቱ አደባባዮች የተያያዘው የተቃውሞ አድማ ካለ ማቋረጥ እየቀጠለም ሲሆን፣ ጉዳዩ በተመለከተ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ተክስቶ ያለው ውጥረት የስብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በተካነው አሠራር መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ሲል፣ ምክትል ርእሰ ብሔር ቢደን ለኡክራይን ርእሰ ብሔር ቪክቶር ያኑኮቪች ስልክ በመደውል በኡክራይን ተከስቶ ያለው ውጥረት አሳሳቢነቱ ሲመለክቱ፣ የኤውሮጳ ኅበረት ተረኛ ሊቀ መንበር የሊትዋኒያ መንግሥት የኡክራይን መንግሥት በመካሄድ ላይ ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ኃይልና ለከፋ ችግር የሚከጅል ስልት እንዳይጠቀሙ አደራ እንዳሉም መኒከቲ ያጠናቀሩት ዘገባ ይጠቁማል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የኡክራዩ ጉዳይ በተመለከተ የባልካንና ካውካሶ ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኤክኖሚያ ጉዳይ ሊቅ ዳኒሎ ኤሊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በኡክራይን ተከስቶ ያለው ሕዝባዊ አብዮት ቀዳሚ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የታየው በአገሪቱ መንግሥትና አመራር አካላት ለውጥ አስከትሎ የነበረው ቡርቱካናዊው አቢዮት መሠረት ሁለተኛ አብዮት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፣ አንደኛው አብዮት አረጋግጦት የነበረው ለውጥ ወደ ነበረበት ተመሰዋል። አሁንም ቢሆን የኤውሮጳ ኅበረት ደጋፊው ሕዝብና የፖለቲካ ሰልፎች ተከስቶ ያለው ሁኔታ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ነው። ስለዚህ ለለውጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለው፣ ብዙ ሕዝብ ርእሰ ብሔር ያኑኮቭይችን በመቃወም በአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ አድማ እያካሂደ ነው፣ ሆኖም በዚህ ሕዝባዊ አድማ ከመሳተፍ የተቆጠበው አብላጫው ሕዝብ ሊባል ይቻላል በሰጠው ድምጽ በሥልጣን ላይ ያወጣቸውና ርእሰ ብሔር ለመሆን የበቁት ያኑኮቭይች ደጋፊ ነው፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ በአገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ የተወሳሰበ ነው።
አገሪቱ የብራስለስ ወይንም ሩሲያዊ ፖለቲካ መከተል በሚል ምርጫ ላይ ያለች ይመስላል፣ ሁለቱን መንገድ መከተሉ እጅግ ያዳግታል፣ በርግጥ ነው ኡክራይን ከሩሲያ ጋር የቆየ ጽኑ ግኑኝነት ያላት አገር ብትሆንም ቅሉ ያኑኮቪይች ኡክራርይንን በሩሲያ እቅፍ ላይ ለማኖር ፍላጎት አላቸው ብሎ ለመናገሩ ያዳግታል ፍላጎቱም የላቸውም ካሉ በኋላ፣ ርእሰ ብሔር ውጥረቱ ለማርገብ በማለት ከሳቸው በፊት አገሪቱን በርእሰ ብሔርነት የመሩትን ክራቭቹክ፣ ኩችማና የሸንኮ ለውይይት ጠርተዋል፣ ውሳኔውም አገራዊ አንድነት ለማረጋገጥ ያለመ እንደሚመስልም አብራርተው፣ ሆኖም ከዚህ ሊካሄድ ከተወሰነው የውይይት ጉባኤ ስምምነት ይረጋገጣል ብሎ ለመናገር ያስቸግራል ብለዋል።
በመጨረሻም በአገሪቱ ተከስቶ ያለው ሁኔታ በሕዝባዊ ምርጫ በመሪነት የተቀመጠው መንግሥት የአመራር አመታቱን ከማጠናቀቁ በፊት የምርጫው ቀነ ቀጠሮ የሚያስቀድም ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ምርጫው ማስቀደሙ መፍትሄ ሊሆን ይችላል ለማለት አይቻልም፣ ርእሰ ብሔር ያኑኮቭይች የመረጠው ሕዝብ ብዛት በቀላሉ የሚገመት አይደለም በመሆኑም ሕዝባዊ ምርጫ ተመሳሳይ ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል ቀድሞ ማሰቡ ይበጃል ብለው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ