መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-12-18 15:58:49
A+ A- ገጹን ለማተምየሃሴትና ለጌታ ታላቅ ውለታ የምስጋና ቀንRealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተወለዱበት 77ኛ ዓመት “የሃሴት ቀንና ለጌታ ውለታ ምስጋና” በሚል መንፈስ ማክበሯ ሲገለጥ፣ ይኽ የተወለዱበት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንደ የሮማ ጳጳስ ያከበሩት ዓመተ ልደታቸው ምክንያት ከተለያዩ ዓለም አቀፍና ብሔራዊ አቀፍ አበይት አካላትና ከመላ አገሮች ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች በተለይ ደግሞ ከኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከተለያዩ ቤተሰቦች በቅርብ ከሚያውቋቸው ሰዎች የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት መተላለፉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ አጋጣሚ በራዲዮ ቫቲካን ለቋንቋ ስፓንሽ ክፍለ ስርጭት አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳሳትን ከ 1977 ዓ.ም. ጀምረው የሚያውቋቸው አንደ ቅዱስ አባታችን አርጀንቲናዊና አባ ጉይለርሞ ኦርቲዝ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዚጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አባታዊ ፍቅር ለእኛ ይለግሳሉ፣ ስለዚህ ለእኛ አባትነታቸውን የምናከብርበትና የምናመሰግንበት ቀን ነው” ብለው በርግጥ ማንኛውም ሰው የተወለደበትን ቀን ሲያከብር በዚያኑ ዕለት ማእከል ሆኖ ነው የሚውለው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ማእከል ሆነው እንዲታሰቡ ሳይሆን እንደሚታወቀውም ማእከልነት የማይሻ የትህትና መንፈሳዊነት የታደሉ ናቸው። እኛ ይኸንን ያላቸው የትህትና መንፈስ በማስተንተን የተወለዱበትን ቀን ማሰብና ማክበር ተገቢ ነው፣ በርግጥ እሳችው የተወለዱበት ቀን ሌሎች የሚያቁዋቸው ገሃድ ስላደርጉት ነው እንጂ የእሳቸው ፍላጎት ቢሆን ኖሮ በዝምታ የሚታለፍ ቀን ሆኖ በቀረ ነበር ብለዋል።
አባ ኦርቲዝ ይላሉ በአርጀንቲና የኢየሱሳውያን ማኅበር የዘርአ ክህነት ተማሪ ለመሆን ጥያቄ ሳቀርብ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ከመሆናቸው በፊት ብቻ ሳይሆን ገና ተራ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በአርጀንቲና ለማኅበሩ ቅርንጫፍ ጠቅላይ አለቃ ነበሩ፣ ቀጥለውም የኢየሱሳውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች አለቃ ሆነው የታመሙትን የተናቁትን ተነጥለው በተለያየ ችግር ተውጠው የሚኖሩትን ድኾች ሕፃናትን የድኾች መኖሪያ መንደሮችን እንድንጎበኝ እንድናጽናና መርተዉናል፣ አነዚህን የኅብረተሰብ ክፍል ለማስደሰት የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖራቸው የማያደርጉት ጥረት አልነበረም። እውነተኛ በላቀ አባትነት ፍቅር የሚገለጥ ሰብአዊነት የተካኑ ጽኑ ቆራጥ ከተማሪዎች ብዙ የሚጠብቁ ሆኖም ፈጽመው ትወድቅ ዘንድ ለብቻህ የማይተዉ ስትወድቅ ከጎንህ ሆነው የሚያበረታቱ አባት ናቸው፣ የእግዚአብሔር መሃሪነት የዋህነት በቅድሚያ ለማሳወቅ የሚጥሩ ባላቸው ግልጽነት እውነተኛውን የጌታ መሓሪው ፍቅር የሚያበስሩ ናቸው፣ እግዚአብሔር እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይም እሳቸውን ስለ ሰጠን ልናመሰግን ይገባናል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ