መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2013-12-23 10:31:37
A+ A- ገጹን ለማተምኢየሱስ:- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው:የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ: - ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! የዛሬው ግንኙታችን የዘመነ ምጽአት መንፈሳውነት አንዣብቦ ባለበት ወቅት እንዲሁም ለልደት በዓል የሚያቀርበን የልደት መዘጋጃ ጸሎተ ታስዕት በምናሳርግበት ወቅት በመገኘት ለብርሃነ ልደቱ እየተጓዝን ባለንበት ወቅት ስለ ኢየሱስ ልደት ለመናገር እወዳለሁ፣ በዓለ ልደት ማንኛው መጠራጠርና ተስፋ መቍረጥን አሸንፎ መተማመንና ተስፋ የሚሰጠን በዓል ነው፣ የተስፋችን ምክንያት ደግሞ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ገናም በእኛ ይተማመናል፤ ነገር ግን ይህንን አስተንትኑ እግዚአብሔር አባት ከእኛ ጋር እጅግ ርኅሩኅ መሆኑን አስተውሉ!ከሰው ልጆች ጋር አብሮ ለመኖር ይመጣል፣ ከሰው ልጆች ጋራ አብሮ ለመኖርና የሰው ልጅ በደስታና በኃዘን የሕይወት ዘሙኑ በሚኖርበት ከእርሱ ጋር ሁሉን ለመሳተፍ ምድር መኖርያው እንድትሆን መረጠ፣ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ምድራችን “የእምባ ሸሎቆ” አይደልችም ነገር ግን እግዚአብሔር ድንኳኑን ያኖረባት የእግዚአብሔር የሰው ልጆች መገናኛ እንዲሁም በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል አጋርነት የሚታይባት ናት፣ እውነተኛ ሰውና እውነተኛ አምላክ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እግዚአብሔር የእኛ የሰው ልጆች ሁኔታን ለመሳተፍ ከእኛ አንድ እስከ መሆን ደረሰ፣ ሆኖም ግን ሌላ ከዚህ የላቀና እጅግ አስገራሚ ነገር አለ፣ የእግዚአብሔር በሰው ልጆች መካከር መኖር ኃሳባዊ በሆነ አኳሃን እና በማይጨበጥ መንገድ አይደለም እውን የሆነው፣ ነገር ግን በዚሁ መከፋፈል ክፋት ድህነት ትዕቢትና ውⷛ በሞላበት በዚሁ በምንኖርበት ተጨባጭ በሆነችው ምድራችን እውን ሆነ፣ እርሱ ታሪካችንን ካለው አጠቃላይ ጫናውና ውስንነት እንዲሁም ድርማዎች ጋር እንዳለ ሊሳተፈው ፈለገ፣ እንዲህ በማድረግም ወደር በሌለበት መንገድ የይቅር ባይነት ባህሩና በሰው ልጆች ላይ ያለውን ፍቅር አሳየን፣
እርሱ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው! ኢየሱስ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው! ይህንን ታምናላችሁን? (ሕዝቡ አዎ ብሎ መልሰዋል) አሁን አንድ ነገር እናድርግ! ሁላችን አብረን ይህንን እምነታችን እንግመስክር! ኢየሱስ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ሁላችን አብረን እንድገመው! እስቲ እንደገና! (ሕዝቡ፤ኢየሱስ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው!) መልካም እግዚአብሔር ይስጥልን፣
ኢየሱስ ማለት በችግሮቻችንና በሥቃዮቻችን ታሪክ የሚሸኘንና ከዘለዓለም እስከ ለዘለዓለም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፣ የኢየሱስ ልደት እግዚአብሔር ለአንዴና ለሁል ጊዜ ከሰው ልጆች ጎን በመሆን የተገለጠበት በዓል ነው፤ ይህንን ያደረገው ደግሞ ሊያድነን ከኃጢአቶቻችን ሊያላቅቀን ከችግሮቻችን ሊያድነን መጣ፣ ከዚህ ታላቁ የቤተልሔም ሕጻን ስጦታ ይመጣል፣ ይህ መንፈሳዌ ኃይል ሆነ ወደ እግዚአብሔር ይመራናል በድካሞቻችንና ተስፋ መቍረጦች እና ኃዘኖቻችን ጠልቀን እንዳንቀር ይረዳናል፣ ልባችን በማሞቅ ይቀይረናል፣ የኢየሱስ መወለድ እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር እጅግ የተፈቀርን መሆናችንን ያበስረናል፤ ይህንን ፍቅር ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ይሰጠናልም፣ ስለዚሁ ደስ የሚያሰኝ የወልደ እግዚአብሔር ስለእኛ መወለድ ምሥጢር ስናስተነትን ሁለት ነገሮች ለማግኘት እንችላለን፣ አንደኛው በጌታ ልደት እግዚአብሔር እላይ ሆኖ ዓለምን የሚገዛ ሳይሆን ወደ ደረጃችን ዝቅ የሚልበት እግዚአብሔር ትሕትና የሚለብስበት ወደ መሬት ወርዶ ትንሽና ድሃ የሚሆንበት ምሥጢር የሚገልጥልና እኛ እርሱ ለመምሰል ከፈለግን ከሌሎች የበለጥን አድርገን በማሰብ እንዳንታበይ ነገር ግን ትሕትና ተላብሰን ሌሎችን ማገልገል እንዳለብንና ከትናንሾች ትናንሽ ከድሆች ደግሞ ድሃዎች መሆን እንዳለብን ያስተምረናል፣ ለዚህም አንድ ትሕትና ያልተላበሰ ክርስትያን ማየት እንዲሁም ለማገልገል የማይፈልግና በዕብሪት ተነፍቶ ወዲያ ወዲህ የሚል ክርስትያን ማየት እንዴት ያለ መጥፎ ነገር መሆኑን እንገነዘባለን፣ ይህ ዓይነት ሰው ክርስትያን አይደለም አረሜን ነው፣ እውነተኛ ክርስትያን ያገለግላል በትሕትናም ራሱ ዝቅ ያደርጋል፣ ትናንሽና ድሃ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ብቻቸውን ሆኖ እንዳይሰማቸው በትሕትና እናገልግላቸው፣ አጋርነታችንና እጐናቸው መቆም በቃላት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር አጠገባችን መሆኑን በሚያሳዩ ተግባሮች ይሁን፣
ሁለተኛው ደግሞ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እንደኛ ሰው እስከመሆን ከደረሰ ለወንድማችን ወይንም ለእህታችን ያደረግነው ማንኛው ነገር ለእርሱ አደረግነው ማለት ነው፣ ራሱ ኢየሱስ በወንጌሉ ይነግረናል፣ ለእነዚህ ትናንሾች ያበላ ያጠጣ ያለበሰ ያፈቀረ ለእግዚአብሔር ልጅ እንዳደረገው ነው፣ በተቃራኒው ደግሞ ይህንን ማድረግ በመዘንጋት ወይንም በመርሳት ለትናንሾችና ድሆች ያልተቀበለ ያላበላ ለእግዚአብሔር ልጅ እንዳልተቀበለ መሆኑን በወንጌለ ማቴዎስ 25፡35-46 ይገልጥልናል፣ ሓዋርያው ዮሓንስ በአንደኛ መል እክቱ 4፤20 “የሚያየውን ወንድሙን የማያፈቅር ሁሉ የማያየውን እግዚአብሔርን ለማፍቀር አይችልም” ይለናል፣ የኢየሱስ ክርስቶስና የእኛ እናት በሆነችው እመቤታችን ድንግል ማርያም አማላችነት በመተማመን በዚሁ ቅርብ ግዝያት ለምናከብረው በዓለ ልደት በጓደኞቻችን ገጽታ በተለይ ደግሞ ደካማዎች በሆኑና በተነጠሉ ሰዎች ገጽታ ስለኛ ሰው የሆነው የኢየሱስን ገጽታ አይተን እንድንችል ትርዳን፣ ለሁሉም ፍቅራችንና መልካም ተግባራችንን እንድንለግስ ትደግፈን፣ እንዲህ በማድረግ የኢየሱስ ብርሃን ነጸብራቅ በመሆን በቤተ ልሔም በረት የተወለደው ኢየሱስ ብርሃኑን ለሁሉ እናዳርሳለን፤ እንዲሁም በውስጣችን የምንመኘው ደስታና ሰላምን በመስጠት ብርሃኑ በሰዎች ልቦች እንዲያንጸባርቅ እናደርጋለን፣ እግዚብሔር ይስጥልኝ፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ