መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2013-12-27 15:44:22
A+ A- ገጹን ለማተምዳግም የዓይን የማየት ብቃት የመታደል ተአምርRealAudioMP3 የፍቅር አገልጋዮች ደናግል ዘቅድስ ኤሊዛቤጥ ማኅበር አባል እ.ኤ.አ. በ 1927 ዓ.ም. ምድራዊ ሕይወቷን ያጠናቀቀቸው እናቴ ማሪያ ተረዛ ደምጃኖቪች አማላጅነት የዓይን የማየት ብቃት ቀስ በቀስ በሚያዳክም ለዓይን መታወር በሚዳርገው በሽታ ተጠቅቶ የነበረው አንድ የተባበሩት አመሪካ መንሥስታት ዜጋ ሕፃን እ.ኤ.አ. በ 1960 ዓ.ም. ዳግም የዓይን መከፈት ጸጋ መታደሉ እውነተኛነቱ ከረዥም ዓመት ጥናትና የሥነ ሕክምና ምርምር ውጤት በኋላ ተረጋግጦ የፈውሱ ተአምረኛነት የሚያረጋግጠው የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ያቀረበው ሰነድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተቀብለው እውቅና በመስጠት እናቴ ተረዛ ደምጃኖቪች ብፅዕና እንዲታወጅላቸው የውሳኔውን ሰነድ ማጽደቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የእግዚአብሔር አገልጋይ እናቴ ማሪያ ተረዛ ደምጃኖቪች ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና ብሎም ቅድስና እንድታውጅላቸው መሠረተ ሃሳብ አቅራቢ ሲልቪያ ኮረኣለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. በ 1960 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ኒው ዮርክ ግዛት ይኖር የነበረው ሕፃን የአገሪቱ ዜጋ የፍቅር ደናግል ዘቅድስት ኤሊዛቤጥ ማኅበር ሥር በሚተዳደረው ትምህርት ቤት ተማሪ የዓይን ሕመም አጋጥሞት የማይድንና ቀስ በቀስ የዓይን የማየት ብቃት በማዳከም ለመታወር አደጋ የተጋለጠ መሆኑ ሐኪሞች የተናገሩለት ሆኖም ግን ቀስ በቀስ ከደናግሎቹ የእናቴ ማሪያ ተረዛ ደምጃኖቪች ምስል ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ የዓይን ማየት ብቃት ዳግም ቀስ በቀስ ለመጨበጥ በመቻሉ ጉዳዩ ሓኪሞች አስገርሞአቸው እንዲመለከቱት ወደ የዓይን ሕክምና ቤት ተወስዶ ከተመረመረ በኋላም የሥነ ዓይን ሕክምና ሊቃውንት እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ስለ መዳኑ ለማወቅ ባይችሉም ሕፃኑ ቀስ በቀስ የዓይን ብርሃን ዳግም እየታደለ መሆኑ የተናገሩለትና አጋጥሞት የነበረው የዓይን በሽታ ለመታወር አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ፈውስ የሌለው መሆኑ በሁሉም ዘንድ የተመሰክረለት ሕፃን ዳግም ከዚህ በሽታ ተላቆ ለማየት መብቃቱ በእናቴ ማሪያ ተረዛ ደምጃኖቪች አማላጅነት ከእግዚአብሔር የታደለው የፈውስ ጸጋ መሆኑ የሚብራራው ሰነድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊርማቸው አጽድቀዉታል።
ማሪያ ተረዛ ደምጃኖቪች ገና ከሕፃንነቷ ገዳማዊ ሕይወት ለመኖር የነበራት ጥሪ በመከተል መጀመሪያ የቀርመለሳውያን ደናግል ማኅበር አባል ለመሆኑ ጠይቃ ተቀባይነት አግኝታ እያለች ባጋጠማት የዓይን በሽታ ምክንያት የማየት ችግር ስለ ነበራትም ከዚሁ ጋር በተያያዘው ውሳኔ ለቀርመለሳውያን ደናግሎች ማኅበር ተልእኮ የሚያሰናክላት በሽታ በመሆኑ ከማኅበሩ ተሰናብታ ስታበቃ ትምህርቷን አጠናቃ በአስተማሪነት መተዳደር ጀምራ እያለች አሁንም ገዳማዊ ለመሆን ስለ ነበራት ጥልቅ ፍላጎት የእግዚአብሔር ጥሪ መሆኑ ለይታ የተገነዘበች መሆንዋ ከነፍስ አባትዋ ጋር መክራ፣ ታስተምርበት በነበረው በፍቅር ደናግል ዘቅድስት ኤሊዛቤጥ በሚተዳደረው ትምህርት ቤት ባለው ቤተ ጸሎት በመጸለይ ጌታ ፈቅዶት የፍቅር ደናግል ዘቅድስት ኤሊዛቤጥ ማኅበር ለመግባት ፈቃድ አግኝታ የሚጠየቅባት ሁሉ አጠናቃ አባል በመሆን የቅድስት ሥላሴ ተመስጦ ሕይወት በመኖር ስለዚሁ መንፈሳዊነት የሰጠቸው በመንፈሳዊ ሰነድ የተዘገበው ምስክርነት በአበይት የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ጥናትና ምርምር ተደርጎበት የመንፈሳዊው ተመስጥቶ ተመክሮውና ምስክርነቱ ትክክለኛ የሚል ውሳኔ የሰጡበት መሆኑ ገልጠው ኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና እንዲታወጅላት በመወሰንዋ አቢይ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ