መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2014-01-31 16:00:46
A+ A- ገጹን ለማተምየሐዘብ መግለጫ መልእክትRealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በካናዳ ኪበክ ከተማ የሚገኘው ኢስለ ቨርተ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የአረጋውያን ማደሪያ ሕንጻ በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሳቢያ ሕይወታቸውን ላጡት ጌታ በመንግሥቱ እንዲቀበላቸውና ለተጎዱት ፈጣን ፈውስ ከጌታ ለሟቾች ቤተሰብ መጽናናት ከጌታ የሚማጠን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፓሮሊኒ ፊርማ የተኖረበት የሐዘን መግልጫ መልእክት ለሪሙስኪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፒየረ አንድረ ፉርኔር እንዳስተላለፉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት የሓዘኑን ተካፍይ መሆናቸውን የሞት አደጋ ያጋጠማቸው ሁሉ በጌታ ብርኃን እንዲኖሩ ለእግዚአብሔር ምኅረት በማስረከብ፣ ቅርበታቸውና ጸሎታቸውንም በማረጋገጥ የደረሰው የእሳታ ቃጠሎ አደጋ ለመቆጣጠርና ለማጥፋት የክልሉ የእሳት ቃጠሎ አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ያሳዩት ርብርቦሽና ለጋስነት አመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ