መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > መንእሰያት >  2014-03-12 16:14:57
A+ A- ገጹን ለማተምክራኮቪያ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን 2016 ዓ.ም.RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የ 2016 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በክራኮቪያ እንዲከናወን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መወሰናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የሚከናወንባቸው ቀናቶችም እ.ኤ.አ. ከ ሐምሌ 26 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 20 ቀን እስከ ሐምሌ 25 ቀን የሰበካዎች የወጣቶች ቀን ቀደም ብሎ እንደሚከናወን የ2016 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን www.krakow2016.com የተሰየመው ይፋዊ ድረ ገጽ ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት ሲያመልክት፣ የዜናው አገልግሎት አክሎ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 26 ቀን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የመክፈቻ በዓል፣ ከረቡዕ ሐምሌ 27 ቀን እስከ ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መርሃ ግብሮች የሚከናወንባቸው ቀናቶች መሆናቸውና፣ ሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን ወጣቶች ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልዩ የአቀባበል ሥነ ስርዓት እንደሚያከናውኑ አስታውቀዋል።
ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የመስቀል መንገድ እንደሚካሄድ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የዋዜማ ጸሎት አስተንትኖ ምስክርነት መንፈሳዊ መዝሙር የሚቀርብበት ዕለት ሲሆን ጧት እሁድ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መዝጊያ ዕለት ምክንያት መስዋዕተ ቅዳሴ መርተው ሥልጣናዊ ስብከት እንደሚያስደምጡና በዚያኑ የመዝጊያ ዕለት ቅዱስነታቸው ቀጣዩ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያስተናጋጅ አገር ስም በይፋ እንደሚገልጡ አስታውቀዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ