መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ፍትሕን ሰላምን >  2014-03-12 16:12:13
A+ A- ገጹን ለማተምዓለም አቀፍ የሕጻናት መርጃ ድርጅት መግለጫRealAudioMP3 ዕልባት ባጣው የሶሪያው ውስጣዊ ግጭት ሳቢያ 5.5. ሚሊዮን የአገሪቱ ሕጻናት ለአደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መርጃ ማኅበር ትላትና ስለ ሶሪያ ሕፃናት ወቅታዊ ሁኔታ ርእስ ሥር ባወጣው መግለጫ ጠቅሶ፣ አስቸኳይ የስብአዊ አርዳታ እንዲቀርብ አደራ በማለት፣ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የተጠቂው ሕፃናት ብዛት በእጥፍ እጅግ ከፍ ማለቱና አንድ ሚሊዮን የሚገመቱት ሕፃናት ግጭቱ በሚካሄድባቸው ክልሎች ታግተው የቀሩ ሲሆን፣ ለእነዚህ ሕፃናት አስፈላጊውና አሰቸኳይ የሰብአዊ እርድታ ለማቅረብ እጅግ አዳጋች መሆኑና፣ 1.2 ሚሊዮን ወደ ጎረቤተ አገሮች መሰደዳቸውና 4.3 ሚሊዮን በገዛ አገራቸው ውስጥ የተፈናቀሉ መሆናቸው የድርጅቱ መግለጫ የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
10 ሺሕ የሚገመቱ ለሞት አደጋ መጋለጣቸውና 8 ሺህ የሚገመቱ ወላጅ አልባ ሆነው መቀረታቸውና 37 ሺሕ 498 ደግሞ በስደተኞች መጠለያ ሰፈር የተወለዱ፣ 3 ሚሊዮን ሕፃናት በትምህርት ገበታ ላለ መሳተፍ መገደዳቸው ሲር የዜና አገልግሎት የሕፃናት መርጃ ማኅበር መግለጫ ጠቅሶ፣ በጎረቤት አገሮች ከተሰደዱት ሕፃናት ውስጥ አንዱ አስረኛው ሕፃን ሰራተኛ ለመሆን አደጋ የተጋለጠ፣ አንድ አምስተኛው ሕፃን ልጃገረዶች ገና ለአቀመ አዳም ሳይደርሱ የሚዳሩ መሆናቸውና ይኸንን ሁሉም የጠቀሰው የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት የሶሪያ ሕፃናት አስቸኳይ የተሟላ ሰብአዊ ስነ አእምሮአዊ ድጋፍ ብሎም በሚገኙበት ክልል የሕፃናት የስበአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲረጋገጥላቸው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ያላሰለሰ ጥረት የማድርግ ግብረ ገባዊ ግዴት አለበት የሚለው ሃሳብ የድርጅቱ ጠቅላይ አስተዳዳሪ ኤንቶንይ ላክ ሰነዱን አስደግፈው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳበከሩ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ