መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ባህልን ኅብረተ-ሰብን >  2014-04-09 16:03:20
A+ A- ገጹን ለማተምበዋሽንግተን "Cortile dei gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ ዓውደ ጥናትRealAudioMP3 የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል መርሃ ግብር የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት ያነቃቃው መርሃ ግብር በመቀጠል እ.ኤ.አ ሚያዝያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚጠቃለል የተለያዩ የሃይማኖት ተከታይ ምእመናንና የበላይ መንፈሳውያን መሪዎችን ያሳተፈ ዓበይት የዓለም ፖለቲካዊና ባህላዊ ጉዳይ ሥር እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዋሽንግተን በሚገኘው በከነዲ ማእከል እያካሄደ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በመካሄድ ላይ ስላለው ዓውደ ጥናት አስመልከተው የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የዓለማዊነት ባህላዊ ትሥሥር ተጽእኖ የምዕራብ ባህል ተጽእኖው ባየለበት ዓለም የባህል የአህዛብ ቅጥር ግቢ መርሃ ግብር በዋሽንግተን ማካሄዱ አቢይ ትርጉም አለው ብለው፣ በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጥናት ርእሰ፦ እምነት ባህልና የጋራ ጥቅም” የሚል መሆኑም ገልጠው በኅብረተሰብና በመንግሥት መካከል ኅብረተሰብ በማህጸኑ በተለያየ መልኩ የሃይማኖት ገጠመኝ የሚኖር ይኽ ገጠመኝ ደግሞ ኅብረአዊነት ለበስ ነገር ግን የራዝ ገዝ ሁነት በስፋት የሚታይበት መሆኑም ገልጠው፣ ስለዚህ ይኸንን መለያ በሚገባ ለይቶ በማጤን ዓውደ ጥናቱ የተለያዩ የፖለቲካ አካላት በተለይ ደግሞ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሁለቱ የፖለቲካ ሰልፍ ተወካዮች የሥነ ባህል ሊቃውንት የሚያሳትፍ የተለያዩ ሃይማኖት ያካተተ ከተለያዩ የተለያዩ የሃይማኖት መናብርተ ጥበብ የተወጣጡ ሊቃውንትና ተማሪዎች የሚያሳትፍ መሆኑ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ