መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2014-05-24 19:08:45
A+ A- ገጹን ለማተምየክርስትያን ጤንነት የሚታወቀው በደስታው ነው፣ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ “የአንድ ክርስትያን ማኅተም ደስታ ነው፣ ይህ ደስታ በብርቱ ስቃይና ፈተና ጊዜም ሳይቀር በልባችን ውስጥ መኖር አለበት” ሲሉ ክርስትያኖች በምንም ምክንያት ኃዘንተኛ መሆን እንደሌለበት ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ እንድናፈቅርና በደስታ የተሞላን እንድንሆን ያስተምረናል ሲሉ የደስታችን ምክንያት ገልጠዋል፣
አያይዘውም ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ስለ ብዙ ጉዳዮች እንደተናገረ ሆኖም ደጋግሞ የተናገራቸው በሶስት ቃላት ሊጠቀለሉ እንደሚችሉ እኚህም ሶስት ቃላት ሰላም ፍቅርና ደስታ መሆናቸውን አመልክተዋል፣ ስለሰላም ሲናገር “እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ሰላም አይደለም ሰላሙም ለሁል ጊዜ ከእኛ ጋር የሚሆን ነው” ብሎናል፣ ስለፍቅር ሲያተርምርም የት እዛዞች ሁሉ ፍጻሜ መሆንዋንና በእግዚአብሔር ፍቅርና በጓደኛ ፍቅር እንደሚጠቃለልም ግለጦናል፣ እኛ የምንፈረድባቸው ጉዳዮችም በወንጌል ማቴዎስ 25 ላይ ዘርዝሮልናል፣ በዮሓንስ ወንጌል የተመለከትን እንደሆነ አፍቅሩ ብሎ ብቻ ት እዛዝ አይሰጥም አፍቅሩ ብሎ በፍቅሬም ጸንታችሁ ኑሩ ይለናል፣
“የአንድ ክርስትያን ጥሪ ይህ ነው፤ በእግዚአብሔር ፍቅር ጸንቶ መኖር፤ የእግዚአብሔር ፍቅርን እያስተነፈሱ ልክ ኦክስጅን በሕይወታችን እንደሚያስፈልገን ፍቅርን እያስተነፈስን መኖር ነው፣ የዚህ ፍቅር ጥልቀት ለመግለጥም እግዚአብሔር አብ እኔን እንደሚያፈቅረኝ እኔም እንደዛ አፈቀርክዋችሁ በማለት ይህ ፍቅር ከአባቱ የሚመጣ መሆኑን ያመለክታል፣ በአባቱና በእርሱ መካከል ያለው የፍቅር ግኑኝነት በእኛና በኢየሱስ መሃከልም አለ፣ ለዚህም ነው በዚሁ ከእግዚአብሔር አብ በሚመጣ ፍቅር ጸንተን እንድንኖር አደራ የሚለን፣ ሰላሙም ልክ እንደዛ ነው ከዓለም ሳይሆን ከእርሱ የሚመጣ ሰላም ነው፣ ከዓለም የማይመጣ ፍቅርም ከእግዚአብሔር አብ የሚመጣ ፍቅር ነው፣ በኢየሱስ ፍቅር ጸንተን የመኖራችን ተጨባጭ ምልክት ት እዛዞቹን መጠበቅ መሆኑን በወንጌሉ ይገልጣል፣ በፍቅሩ ጸንተን የኖርን እንደሆነ ይህ ፍቅር ት እዛዞቹን ለመፈጸም ይረዳናል፣ ስለዚህ ፍቅር ልክ እንደ ፈትል ከእግዚአብሔር አብ ከኢየሱስ እና ከእኛ ጋር የሚያገናኝ ነው፣ ሶስተኛ ደስታ ነው፣
“ደስታ የክርስትያን ምልክት ነው፣ ደስታ የሌለበት ክርስትያን እንደ የታመመ ክርስትያን ነው፣ ሌላ መግለጫ የለውም፣ የክርስትያን የጤንነት መምዘኛው ደስታ ነው፣ ስለዚህ ደስት የማይታይበት ክርስትያን ክርስትያን ነኝ ለማለት አይችልም፣ ደስታ የክርስትና ማኅተም ነው ለማለት እንችላለን፣ በስቃይ ጊዜም ይሁን በፈተና ጊዜ እንዲሁም በስደትም ቢሆን ይህንን ደስታ ሊጠቀው የሚችል ማንም የለም፣ የመጀመርያ ክፍለ ዘመን ሰማዕታት ለሰማዕትነት ሲጓዙ ልክ ወደ ሰርግ እንደሚጓዙ በደስታና በዝማሬ ነበር የተጓዙት፣ የክርስትና ደስታ ሰላምንና ፍቅርን ይጠብቃል፣
“በሕይወት ዘመናችን ታላቅ ስራ የሰራ ግን ተረስቶ ያለ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ልጠይቃችሁ ከእናንተ ስንት ናችሁ መንፈስ ቅዱስን የምትለምኑ? እጆቻችሁን ለማንሳት አትሞኵሩ የተረሳው ታላቁ ስጦታ መሆኑን ብቻ እወቁ፣ ሰላም የሚሰጠን ለማፍቀር የሚያስተምረን በደስታም የሚሞላን ይህንኑ ታላቅ ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ በጸሎታችን ጌታን ስጦታህን ጠብቅ ብለን እንለምናለን፣ ይህ ማለትም ጌታ በውስጣችን ያለውን መንፈስ ቅዱስ እንዲጠብቅልን ነው የምንለምነው፣ እግዚአብሔር ይህን ጸጋ ይስጠን፣ ያ ሰላም የሚሰጠን ለማፍቀር የሚያስተምረንና በደስታ የሚሞላን መንፈስ ቅዱስን ዘወትር በውስጣችን ይጠብቅልን፣ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን ከ10 ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቻቸውና በዚሁ መገናኛ ለሚከታተልዋቸው “በእግዚብሔር እንድትመራ የወሰነች ነፍስ ሁላ በምንም ተአምር አትሳሳትም ከመንገድም አትወጣም” ሲሉ አጭር መል እክት እንደጻፉ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ