መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2014-05-27 10:37:22
A+ A- ገጹን ለማተምየርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፡ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባለፈው ቅዳሜ በዮርዳኖስ አማን ላይ የጀመሩት ሐዋርያዊ ዑደት ፈጽመው ትናንት ረፋድ ላይ ከአማን ቤተልሔም ገብተዋል።
ቤተ ልሔም ከአማን 75 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደምትገኝ የሚታወስ ሲሆን ቅድስነታቸው በሆሊኮፕተር መጓዛቸው ይታወቃል።ፓፓ ፍራንሲስ ቤተ ልሔም እንደገቡ በኢየሩሳሌም እና ፓለስጢና የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ መስተናብር ብጹዕ አቡነ ጁሰፐ ላጻሮቶ በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ፓትርያሪክ ፎዓድ ጥዋል የቅድስት ሀገር ጠባቂ ፍራንቸስካዊ አባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ እና ሌሎች ብጹዓን አበው እና የፓለስጢና የራስ ገዝ አስተዳደር ከፈተኛ ባለስልጣት ደማቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል።ቤተ ልሔም ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ 10 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ 25 ሺ ህዝብ እንደሚኖርባት ይታወቃል ። በእብራይስጥ እና በዓረብ ቋንዎች ቤተ ልሔም የዳቦ ቤት ማለት እንደሆነ ይታወቃል ።
ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በመኪና በቀጥታ ወደ ፕረሲዳንት አዳራሽ ተጉዘዋል ። የፓለስጢና ራስ ገዝ አስተዳደር መሪ ፕረኢድንት ማሕሙድ ዓባስ እና የአገዛዙ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ለርእሰ ሊቃነ ጳጳጳሳት ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል ።የፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ ንግግር አድርገዋል ። ቅድስነታቸውም የፕረሲዳንትሩ ንግግር ካዳመጡ በኃላ ፓፓ የሚከተለውን ብለዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ተከታዮቻቸው ከየፓለስጢና ራስ ገዝ መሪ እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገናኝተው ተወያይተዋል ። ከግንኝነቱ በኃላ ፓፓ ፍርንሲስ እና ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ ስጦታ የተለዋወጡ ሲሆን ከጋዛ ሽርጥ እና ምዕርባዊ ዮርዳኖስ ዳርቻ የመጡ የክርስትያን ማሕበረ ሰባት ወኪሎች ለቅድስነታቸው መልዕክት ማስረከባቸው ተመልክተዋል።
ከዚህ በኃላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰኙ ብጹዕን አበው እና የፓለስጢና ራስ ገዝ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት የዲፕሎማሲ ሰዎች በጋራ በአንድ አዳራሽ የተቀመጡ ሲሆን ፡ ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ እና ርእሰ ሊቃነ ጳጵዓሳት ፍራንሲስ ንግግር አድርገዋል ።ከዚሁ ሥርዓት በኃላ ቅድስነታቸው ሁለት ኪሎሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ቤተ ልሔም አደባባይ የተጓዙ ሲሆን የቤተ ልሔም ከንቲባ እና በርካታ ውሉደ ክህነት አቀባበል አድርጎውላቸዋል ።ፓፓ ፍራንሲስ በዚሁ የቤተልሔም አደባባይ ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል። በዚሁ አደባባይ ከጋዛ ሰርጥ እና ከገሊላ የመጣ ሕዝበ እግዚአብሔር የዚሁ ሥርዓተ ቅዳሲ ተሳታፊ መሆኑ ተመልክተዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚሁ ሥርጳተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ከሥርዓተ ቅዳሴ በኃላ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከምእመናን ጋር የንግስተ ሰማይ ጸሎት ደግማዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የንግስተ ሰማያት ጸሎት በደገሙበት ግዜ ባደረጉት ንግግር በዚሁ የሰላም ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት መካን በመሆን ለርስዎ ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ እና ለየእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንድያወርድ በጋራ እንድንጸልይ ቫቲካን ውስጥ በሚገኘውን ቤተ ላስተናግዳችሁ እውዳለሁኝ ብለዋል።
የፓለስጢና ራስ ገዝ አስተዳደር መሪ ፕረርሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ እና የእራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞም ፐረስ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐሳብ መቀበላቸው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ስታውቀዋል። ይሁን እና እኩለ ቀን ላይ ሲሆን ከቤተ ልሔም አደባባይ አቅራብያው ወደ ሚገኘው ገደመ ፍራንቸስካውን ተጉዘው ከየፓለስጢና ቤተ ሰቦች እና ስደተኞች ጋር ማእድ ተቀምጠዋል።
ቅዱስ አባችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ሰንበት ከቀትር በኃላ ከገዳመ ፍራንቸስካውያን ወደ ልደታ ማርያም ባሲሊክ የተጓዙ ሲሆን ፡ ባሲሊኩ ውስጥ በግል ጸልየዋል።በልደታ ካተድራል ክጸለዩ በኃላ ወደ የቤተልሔም የፎንክስ ማእከል ተጉዘው እዚያው ከሚገኙ ስደተኞች ጋር ተገናኝተዋል ።
በዚሁ ፎንክስ የተባለ ማእከል ደይሽ አይዳ በይት ጂብሪን ከተባሉ ቦታዎች የመጡ ስደተኞች የሚኖሩበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል ።ስደተኞቹ አብዛኛዎቹ ሕጻናት መሆናቸው እና ሕጻናቱ ክርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጠዋል።ፓፓ ፍራንሲስ ከሕጻናቱ ከተወያዩ በኃላ ቤተ ልሔም ላይ ወደ ሚገኘው የሆሊኮፕተር ማረፍያ ተጉዘዋል ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ በዚሁ ቦታ ተገኝተው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሸኝተዋል። በዚህም የፓለስጢና ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ተጠቃልለዋል።
ፓፓ ፍራንሲስ ትናትና ከቀትር በኃላ ከቤተ ልሔም በየዮርዳኖስ ሆሊኮፕተር ወደ እስራኤል ወደ ተልቪቭ በን ጉርዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በረዋል ።
ተልአቪቭ ከቤተልሔም 56 ኪሎሜትር ርቃ ትገኛለች ።
በንጉርዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ እና ጥቅላይ ሚኒስትር በንያሚን ኔታንያሁ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቀባበል አድርጎውላቸዋል ።ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ቅድስነትዎ እንኳን ወደ እስራኤል ደህና መጡ እስራኤል የተለያዩ እምነቶች የሚከተል ህዝብ የሚኖርባት እና የምታስተናግድ ሀገር ናት ብለዋል ።
በዚሁ ክልል ሰላም የራቀበት ክልል ቢሆንም ሰላም ለማስፈን የሚቻለን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን ። ርእሰ ብ ሔር ሺሞን ፐረስ ንግግራቸው በማያያዝ እስራኤል ዲሞክርስያዊት ሀገር መሆንዋ ጠቅሰው ፡ የሃይማኖት እና ሐሳብ የመግለጽ መብት የምትጠብቅ ሀገር መሆንዋ ገልጠው እኒህ እሴቶች የተከበሩ እና የተጠበቁ መሆናቸው ለመግለጽ እወዳለሁ ካሉ በኃላ ለቅድስነታቸው በእስራኤል መልካም ቁይታ ተመኝቶላቸዋል።
ቅድስነታቸውም ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነው ንግግር አድርገዋል።
ከዚህ በኃላ ፓፓ ፍራንሲስ ከተልአቪቭ በሆሊኮፕተር ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ተጉዘዋል ። ተልአቪቭ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በ60 ኪሎሜትር ርቀት ትግኛለች።
ኢየሩሳሌም ለዓበይት ሃይማኖቶች ማለት ክርስትና ይሁዲ እና እስላም ማእከል መሆነዋ ይታወሳል ።
ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም እንደገቡ በቅድስቲቱ መካን ወደ ቤተ ሐዋርያዊ መልእክተኛ ተጉዘው ከየቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ከብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎሞዮ አንደኛ ጋር ተገናኝተዋል።
የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ከ50 ዓመታት በፊት ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድተና እና የቀድሞ የቁስጢንጥንያ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ አተናጎራ ኢየሩሳሌም ላይ ያደረጉት ግንኙነት የዘከረ እና ያተኮረ እንደሆነ ይታወቃል።የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እና የክርስትያኖች አንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ በዚሁ በፓፓ ፍራንሲስ እና ፓትርያሪክ ባርቶሎመዮ መካከል የተደረገውን ግንኙነት ተሳታፊ ሁነዋል።ቅድስነታቸው እና ፓትርያሪኩ በግል ተገናኝተው ከተወያዩ በኃላ በየግላቸው ወደ ቅዱስ መቃብር ተጉዘው በጋራ ኤኩመኒካዊ ማለት አንድነታዊ ሥርዓተ ቅዳሴ እና ጸሎት አድርገዋል ። በመጨረሻም በጋራ አባታችን በሰማይ የምትኖር ጸሎት ደግመው የሰላም ምልክት ተለዋውጠዋል።በመጨረሻም በኢየሩሳሌም ሰዓት አቆጣጠር ሰባት ሰዓት ላይ ፓፓ ፍራንሲስ እና ፓትርያሪክ ባርቶሎመዮ በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ፓትርያሪክ ባዘጋጁት እራት ተሳታፊ ሁነዋል ። በዚህም ህየትናትና እሁድ ውሎዋቸው ፍጻሜ ሁነዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚያደርጉት ሐዋርያው ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ ጥዋት ወደ አል ቅዱስ መስጂድ ተጉዘው የኢየሩሳሌም እና ኩላዊት ፓለስጢና ሙፍቲ ከሼክ ሙሐመድ አብማድ ሑሴን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።ቅድስነታቸው ከዓቢይ ሙፍቲ ጋር ተሰናብተው የምዕራብ ግድግዳ ወይም የኢየሩሳሌውም የልቅሶ ቅድግዳ ያድ ቫሸም ወደ ተባለ ቤተ መዝክር የተጓዙ ሲሆን የእስርኤል ርእሰ ብሔር እና ጠቅላይ ሚኒትር አቀባበል አድርግውላቨዋል እዚህ በግል ግድግዳው ፊት ተምበርክከው ጸልየዋል። በየክብር ደብተር ፊርማቸውን አስፍረዋል።
ያድ ቫሸም በናዚ ጀርመን በገፍ ያለቁ ሰባት ሚልዮን ይሁዲዎች ለመዘከር የተመሰረተ ቦታ ነው ። ከዚህ ወደ ዓቢይ ሲኖጎግ ተጉዘው ከዓቢይ ራቢን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ፓፓ ፍራንሲስ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ወደ ቤተ መንግስት እስርኤል ተጉዘው ከርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ ጋር ተገናኝተዋል ።ፓፓ ፍራንሲስ ከዚህ ወደ ማእከል ጳጳሳዊ ተቋም ኢየሩሳሌም የተጓዙ ሲሆን ከጥንሽ ቆይታ በኃላ ጠቅልይ ምኒኒስትር በንያምኒ ኔታንያሁ ተቀብለው አነጋግረዋል ።
በኢየሩሳሌም ሰዓት አቆጣጠር አንድ ሰዓት ተኩል ተቍሙ ውስጥ የምሳ ሥርዓት ከተከናውነ በኃላ ወደ የገሊላ ሰዎች በተባለ መካን ወደ ሚገኘው ጥንታዊት የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ተጉዘው ከየቁስጢንጢንያ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ከብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎመዮ ጋር ተገናኝተው ተውያይተዋል በጋራ ጸልየዋልም ።
ከዚህ ግንኙነት በኃላ አሁን ዝግጅታችን በሚተላለፍበት ግዜ አቅራብያው ወደ ሚገኘው ጌተሰማኒ ቤተ ክርስትያን ተጉዘው ከመነኲስያት መነኮሳን እና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ተገናኝተዋል ።መስውዕተ ቅዳሴ መርተዋል። ከስርዓተ ቅዳሴ በኃላ ወደ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ለመመለስ ወደ በንጉርዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማርፊያ አቅንተዋል እዚ በሮም ሰዓት አቆጠጠር ከእኩለ ለሊት በፊት ቫቲካን እንዲገቡ ይጠበቃል።

Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ