መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2014-06-03 20:13:33
A+ A- ገጹን ለማተምየር.ሊ.ጳ የንግሥተ ሰማያት ጉባኤ አስተምህሮቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ ከስልሳ ሺ በላይ የሚሆኑ ም እመናንና ነጋድያን በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጌታ በክብር ሰማይ ማረግ የሚያመልክት የዕርገት በዓልን የሚመለከት ጉባኤ አስተምህሮ አቅርበዋል፣
ጌታ ኢየሱስ ከትንሣኤ በኋላ ለአርባ ቀናት ሓዋርያትን ለአዲስ ተለእኮ ካዘጋጃቸው በኋላ በአዲስ መልክ መካከላቸው እንደሚሆን በመግለጥ ወደ አባቱ ክብር ወደ ሰማይ እንደሚያርግና አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እንደሚልክላቸው ተስፋ ሰጥቶ ተሰናበታቸው፣ ቅዱስነታቸው ይህ መለያየት ሳይሆን ለዘለዓለም ከእኛ ጋር የሚሆንበት መንገድ ይህም በአዲስ አግባብ መሆኑንና የጉዞ አችን ዓላማ ወደ ሰማያዊ አባታችን መሄድ እንደሆነም አሳይቶናል በማለት የበዓለ ዕርገት ዋና ትርጉም ገልጠዋል፣
“ኢየሱስ ዘወትር በመካከላችን አለ፤ በሰው ልጅ ታሪክ ሂደትም በታላቅ ኃይልና በመንፈሱ ስጦታ እየሠራ ነው፣ ሁሌ ይሸኘናል፣ ምንም እንኳ በዓይኖቻችን ልናየው ባንችልም እርሱ ሁሌ አጠገባችን ይገኛል፣ በእጆቻችን ይዞም ይመራናል ብንወድቅም ያነሣናል፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ክርስቶስ ዘወትር ለሚሰደዱና ለሚቸገሩ ክርስትያኖች ይሸኛል፤ በእያንዳንዱ የሚሰቃይ የሰው ልጆች አጠገብ ይገኛል፤ ለእኛ ሁላችን ቅርባችን ነው፣ ጌታ ወደሰማይ ሲያርግ ለአባቱ አንድ ታላቅ ስጦታ ይዞለት ይሄዳል፣ ይህም ስጦታ ቍስሎቹ ናቸው፣
“ይህ ኢየሱስ ለአባቱ የሚያቀርበው ስጦታ ነው፣ ከመገረፉና ከመቸንከሩ በፊት የጌታ ኢየሱስ ሰውነት እጅግ ያማረ ነበር፣ ነገር ግን የችንካሮቹና የግርፋቱ ጠባሳዎቹን ይዞ ወደ ሰማይ ሄደ፣ ለአባቱም “ተመልከት አብየ አንተ የሰጠሄው የደህንነት ዋጋ ይህ ነው” ይለዋል፣ እግዚአብሔር አባታችን ደግሞ የኢየሱስ ቍስሎችን ባየ ቍጥር ሁሌ ይምረናል፣ ይህንን የሚያደርገው ደግሞ እኛ በጎ ሰዎች ሆነን ሳይሆን ቤዛችን ስለከፈለ ነው፣ የልጁ ኢየሱስ ቍስሎችን ሲመለከት እግዚአብሔር እጅግ መሓሪና እጅግ ታላቅ ይሆናል፣ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለሓዋርያ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱና ሕዝቦችን ደቀ መዛሙርቴ አድርግዋቸ” (ማቴ 28፡19) ይላቸው፣ ይህ ተልእኮ ሲመቸን ብቻ የምናደርገው የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ሁል ጊዜ መፈጸም ያለብን ትእዛዝ ነው፣ ስለዚህ የክርስትያን ማኅበር ሁሌ ለመሄድ ዝግጁ ለመሆን ነው ጌታ ያቋቋማት፣
“ምናልባት ከእናንተ የክላውዙራ ማኅበሮችስ ልትሉኝ ትችላላችሁ፣ አዎ የክላውዙራ ወይም የዝግ ማኅበሮችም ተለ እኮዋቸው ይህ ነው፣ ለዚህም እነኚህ ማኅበሮች በጸሎት ሁሌ ከገዛ ራሳቸውና ከሁሉ እየወጡ ናቸው ልቦቻቸው ለዓለም ክፍት ሆኖ በእግዚአብሔር አድማስ ለማየት የቻሉ ናቸው፣ እንዲሁም ሽማግሌዎችና ሕመምተኞች በጸሎታቸውና ከኢየሱስ ቍስሎች ጋር ባላቸው ውህደት ከገዛ ራሳቸው ወጣ በማለት ይሰብካሉ፣ ጌታ ሂዱ በማለት ትእዛዝ ብቻ ሰጥቶ ዝም አላለም “እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ቍ 20) ምክንያቱም ካለ ኢየሱስ ብቻችን ምንም ማድረግ አንችልምና፣“በሐዋርያዊ አገልግሎች ችሎቻችን ጥበቦቻን መዋቅሮቻንና ኃይሎቻችን ምንም እንኳ አስፈላጊ ቢሆኑ ብቻቸው በቂ አይደሉም፣ ኢየሱስ በመካከላችን የሌለና የእርሱ የመንፈስ ኃይል ካልሸኘን ሥራዎቻችን እጅግ የተራቀቁና በጥሩ ችሎታ የተዘጋጁ ቢሆም ፍሬ አልባ ናቸው፣ ሲሉ ትምህርታቸው ፈጽመው የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ