መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ቤተ ክርስቲያን >  2014-06-20 18:25:11
A+ A- ገጹን ለማተምበዓለ ቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር በቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራነንሰ ባዚሊካ ቀድሰው እስከ ታላቁ የቅድስት ማርያም ባዚሊካ የቅዱስ ቍርባን ዑደት መርተዋል፣
በቅዳሴው ባደረጉት ስብከት “ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።” የሚለውን ከኦሪት ዘዳግም 8፤2 መነሻ በማድረግ “እነኚህ የኦሪት ዘዳግም ቃላት የእስራኤል ታሪክን የሚመለከት ሆኖ እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ነጻ እንዳውጣቸውና ለአርባ ዓመታት ያህል በምድረ በዳ ወደ ምድረ ተስፋ ባደረጉት ጉዞ እንደመራቸው ይጠቅሳል፣ የተመረጠው ሕዝብ ወደ ተባሉት ቦታ ደርሰው ተረጋግተው በጥሩ ሁኔታ መኖር ሲጀምሩ ግን ወዲያውኑ እግዚአብሔርን መርሳት ጀምሩ ያ በእግዚአብሔር ቸርነትና እርዳታ ያሸነፉት ስቃይንም ረሱት፣ ለዚህ ነው ቅዱስ መጽሓፍ እንዲያስታውሱትና በምድረበዳ ያደረጉት ጉዞ በረሃብና በጭንቀት ጊዜ እግዚአብሔር ያደረገላቸው በማስታወስ ዝክር እንዲያደርጉ የሚነግራቸው፣ ጥሪው ወደ ነበርክበት ዋና ሁኔታ ማለትም በሁሉመናህ በእግዚአብሔር በመጠጋትና በእርሱ በመተማመን ያኔ የኑሮ ትግሉን በእግዚአብሔር እጅ በመተው እንዳሳለፉት ሊያስረዳ ቅዱስ መጽሓፉ “ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥” ይላል፣
ከሥጋዊ ረሃብ ባሻገር የሰው ልጅ ሌላ ረሃብም አለው፣ ይህ ረሃብ በምድራዊ እንጀራ ሊታገስ አይችልም፣ ይህ ረሃብ የሕይወት ረሃብ የፍቅር የዘለዓለማዊ ሕይወት ረሃብ ነው፣ ያ በኦሪት ከሰማይ የተሰጣቸው መናም አጠቃላዩ የጸአት ጉዞ የዚህ ትርጓሜም ነበረው፣ በሰው ልጅ ውስጥ ላለው ለዚሁ ጥልቅ ረሃብ ማስታገሻነት እንደ ት እምርት ወይም ምሳሌ የቀረበ ነው፣ ኢየሱስ ይህንን ምግብ ይሰጠናል፣ ስለሆነም እርሱ ራሱ ሕያው እንጌራ ሆኖ ለዓለም ሕይወት ይሰጣል (ዮሓ 6፤15) በዳቦ መልክም ስጋው እውነተኛ ምግብ ነው በወይን መልክም ደሙ እውነተኛ መጠጥ ነው፣ እንደ ማና ስጋዊ ረሃባችን ብቻ የሚያስታግስ አይደለም፣ የክርስቶስ ሥጋ ሕይወትና ዘለዓለማዊ ሕይወት ሊሰጥ የሚችል እንጀራ ነው ምክንያቱ ደግሞ ይዘቱ ፍቅር ስለሆነ ነው፣
በቅዱስ ቍርባን ጌታ ለእኛ ያለው ፍቅር ይገለጣል፣ የዚሁ ፍቅር ታላቅነትም ጌታ ገዛ ራሱን እንደ ምግብ ያቀርብልናል በነጻ የተሰጠ ፍቅር በመሆኑም ለማንኛው የተራበና ኃይሉ ለደከመው በነጻ የሚሰጥ ነው፣ በእምነት መኖርን ማጣጣም ማለት ደግሞ በጌታ እንዲመሩና ኑሮን በሚጠፋ ቍሳዊ ንብረት ሳይሆን በማይጠፋው መንፈሳዊ እውነት ማኖር ነው፣ የማይጠፋው እውነት የምንላቸው የእግዚአብሔር ስጦታ የሆኑ የጌታ ቃልና ስጋው ናቸው፣
አከባቢያችን በደምብ የተመለከትን እንደሆነ ከጌታ ያልሆኑ ብዙ መግቦች እናያለን፣ አንዳንዶቹ ገንዘብን ይመገባሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ጀብዱነትና ከንቱነትን ይመገባሉ ሌሎች ደግሞ ስልጣንና ትዕቢትን ይመገባሉ፣ ነገር ግን በእውነት የሚመግበንና የሚያጠግበን ያ ጌታ የሚሰጠን ምግብ ብቻ ነው፣ ጌታ የሚሰጠን እንጀራ ከሌሎች የተለየ ነው፣ ምናልባት ተሳስተን ዓለም እንደሚሰጠን ጣዕም ያለው እንዳይመስለን፣ እና በሲና ምድረበዳ እስራኤላውያን እንዳደረጉት ማለትም በግብጽ ይበሉት የነበሩትን ሥጋና ሽንኵርት መንፈቃቸው ነገር ግን የነበሩትን ባርነትና ጭንቀት በመርሳት እኛም ሌላ ምግብ ልንሻ የሚቻል ነው፣ እብራውያን ያኔ ዝክር ነበራቸው ያ ሁሉ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ያስታውሱ ነበር ይህ ዝክር ግን የታመመ ዝክር ነበር ባርያ ዝክር ሆኖ ነጻ አልነበረም፣
በዛሬው ዕለት እያንዳንዳችን እኔስ? የት ሆኜ መብላት እፈልጋለሁ? በየትኛው ማዕድ መመገብ እሻለሁ? በጌታ ማዕድ ወይስ በባርነት ሥር ሆኜ ደስ የሚያሰኙ የሚመስሉኝን ምግቦች መመገብ እወዳለሁ? ዝክር የማደርገው የማስታወስ ሁኔታዬ እንዴት አለ? ያ ሕይወት የሚሰጠኝ የሚያድነኝ የጌታ እንጀራን ነው የማስታውሰው ወይስ የባርነት ሽንኵርትና ሥጋ? ነፍሴን በየትኛው ዝክር እመግባታለሁ? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፣
እግዚአብሔር አባታችን “አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።” ይለናል፣ ዝክራችን እናሳድስ፣ የሚያሳስተውንና የሚያበላሸንን የውሸት እንጌራን እንወቀው ምክንያቱም የኃጢአት የግልወዳድነት ፍሬ ነውና፣
ከጥቂት ግዜ በኋላ በቅዱስ ቍርባን በእውነት በመካከላችን ያለውን ኢየሱስን ተክትለን ዑደት እናደርጋለን፣ ጌታ ኢየሱስ ገዛ ራሱን በእርሱ አማካኝነት ለኛ የሚሰጠው ኅብስቱ የእኛ መና ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ባሮች ከሚያደርገን ምግብ የተመረዘ ምግብ ፈተና ሰውረን፤ በራስ ወዳድነትና በዓለማዊ ዝክር ባሮች ላለመሆን ነገር ግን ያንተው ህያው ዝክር የአዳኙ ፍቅርህ ዝክር የሆነ ዝክር እንድናደርግ ዝክራችንን አንጻልን ብለን እንለምነው አሜን ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ