መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2014-08-04 19:12:32
A+ A- ገጹን ለማተምየር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (03.08.14)RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር እንደሚያደርጉት ሁሉ ትናንት ዕለተ ሰንበት በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ በብዙ ሺ ከሚገመቱ ምእመናን ጋር እኩለ ቀን ላይ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።

ቅድስነታቸው የዕለቱ ቃለ ወንጌል ጠቅሰው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳቦ እና አሳ በማባዛት ያሳየው ተአምር ዘክረዋል።

ይህ የሚያሳየው በዚች ዓለም ላይ ተከፋፍለን ተባብረን እና በወንድማማችነት እንድንኖር የሚያመላክት እንደሆነ አመልክተዋል።

አያይዘው ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ተአምር ርሕራሔ መፈቃቀድ መተባበር መከባበር እንደሚያስተምረን ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ትናንት ዕለተ እሁድ ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚህ ነው ስንሰቃይ ከኛ ጋ ይሰቃያል ስለ እኛም ይሰቃያል ርህሩህ አምላክ ስለ ሆነም በሽተኞች አዳነ ብለዋል።

የተወደዳችሁ ምእምናን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ በመከተል ለተቸገሩ መርዳት መንከባከብ ይጠበቅብናል እምነታችን በቃል ሳይሆን በተግባር ማሳየት አለብን የኢየሱስ ክርስቶስ መድኀኒታችን ትምህርት ተረድተን ማተግበር አለብን ርሕራሔ እና ፍቅር ማሳየት አለብን በማለትም ቅድስነታቸው በማያያዝ አገንዝበዋል።

ለችግር የተጋለጡ እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን ፊት ለፊት ሲገጥሙን ፊታችን ማዞር የለብንም፡ መርዳት መተባበር እና መፈቃቀድ ያስፈልጋል በማለት ቅድስነታቸው በማያያዝ ተናግረዋል።

በቅዱስ ቁርባን በኩል ዘወትር ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋ መገናኘት እንዳለብን አጽንኦት ሰጥተው ያሳሰቡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ክርስትያናዊ ካቶሊካዊ ርህራሔ እንዳይለየን በማሳስብ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምእመናን እና ሀገር ጐብኝዎች ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።
Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ