መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  

     መታወቂያ ገጽ > ጕባኤ ኣስተምህሮን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔርን >  2014-08-11 16:12:44
A+ A- ገጹን ለማተምየር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (11.08014)ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር እሁድ እንደ ሚያደርጉት ሁሉ ትናትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን እና ሀገር ጐብኝዎች ጋር መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል። ቅድስነታቸው መጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ኢየሱስ ክርስቶስ በውሃ ላይ ሲራመድ ሐዋርያቱ በነበራቸው ደካማ እምነት ግራ እንደተጋቡ አመልክተው፡ እኛስ ስንት ግዜ ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ርቀን በምንገኝበት ግዜ ፍርሀት ይዘናል መጠራጠር እንጀምራለን ይህ የእምነታችን ብርታት መለኪያ እንደሆነ አመልክተዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ባይታይም ሁሌ ከኛ ጋር እንደሚጓዝ እንደምከታተለን እና እንደሚደግፈን ማወቅ መረዳት ያሻል ብለዋል።
ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ለመታደግ እንደ አንድ መርከብ ባሕር ላይ ስታንሳፍፍ ባሕር ላይ ከመስጠም እንደምትታገል መሆንዋ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስገንዝበዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በማያያዝ እንዳመልከቱት ቤተ ክርስትያን በመሪዎችዋ ቁራጥነት እና ዓይነታቸው ሳይሆን በእምነተ ሃይማኖት እንደምትታደግ አስገንዝበዋል። እንግዲህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአደጋ እና ከእኩይ ተግባር ሁሉ እንደሚጠበቀን የተረጋገጥን መሆን እንዳለብን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማምለክ አለብን እምነታችንን አጽንተን መከተል አለብን በማለትም አሳስበዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የዒራቅ ህዝብ በተለይ ማሕበረ ሰብ ክርስትያን እየተሳደደ መሆኑ ሁኔታው በእጅጉ እንዳሳሰባቸው እና አክለው < ሕጻናት ከቤት ንብረታቸው ሲሸሹ በርሃብ እና በጥም እየሞቱ መሆናቸው ሴቶች እየተጠለፉ ህዝብ በግፍ ሕይወቱ እያጣ መሆኑ ጠቅሰው አሰቃቂው ተግባር መገታት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ዒራቅ ውስጥ አብያተ ክርስትያኖች መቃጠላቸው ንብረት መብረሳቸው አስታውሰው ዓለም አቀፍ ማሕበረ ሰብ የዒራቅ ሁኔታ ትኩረት እንዲሰጥ ተማጽነዋል ።
በየእስላም አክራሪዎች ዒራቅ ውስጥ በሰው ፍጥረት እና በንብረት እየተካሄደ ያለው ብርሰት ጸረ እግዚአብሔር እና ሰብአዊነት መሆኑ ጠቅሰው እንዲገታ ተማጽነዋል። ለተቸገረው የዒራቅ ህዝብ ሰብአዊ ረዲኤት በመስጠት ላይ የሚገኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሞግሰው አመስገነዋል። በመካከለኛው ምስራቅ በጋዛ ሰርጥ በእስራኤል እና ፍልስጢኤማዊ ሐማስ ይካሄድ የነበረና ለግዜው ጋብ ብሎ የነበረው ግጭት እንደገና ማገረሸቱ በመጥቀስ በእጅጉ የሚያሳዝን እንደሆነ አመልከተው እንዲገታ ጠይቀዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላሙ እንድያወርድ ምእመናን እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች አደራ ብለዋል።
በመጨረሻም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከመገ ወድያ ረቡዕ ነሐሰ 13 ቀን በደቡብ ኮርያ ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደሚነሱ እና ምእመናን በጸሎት እንዲሸንዋቸው በማሳሰብ በአደባባዩ ለተገኙ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው እና መልካም ቀን ተመኝተው ተሰናብተዋል፣

Share


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ