2009-05-27 17:38:04

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባዔ


RealAudioMP3 የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባዔ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የጉባኤው ጠቅላይ ስብሰባ በንግግር ሲከፍቱ የኢጣሊያ የወቅቱ ሁኔታ በመዳሰስ በተለይ ደግሞ የኢጣሊያው መንግሥት ስደተኞችን ለመቆጣጠር የእየተከተለው ያለው የስደተኞች የመቆጣጠሪያው ደንብ ስደተኛውን እግምት ውስጥ ያስገባ ሳይሆን፣ ያገር ውስጥ ጸጥታና ደህንነት ጥበቃ በሚል ፍላጎት የተመራ ሰብአዊነት እቅምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል።

የዚህ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባዔ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ ስለ ተካሄደው ጠቅላይ ስብሰባ አስመልከት ጋዜጣዊ መግልጫ ሲሰጡ፣ “የሚካሄዱት ያገር ውስጥ ሕዝባዊ ምርጫዎች ማዕከል በማድረግ ብቻ ቃል የሚገቡት እቅዶች መሠረት የሌላቸው ናቸው፣ ስለዚህ የፖለቲካ እቅዶች አርቀው የሚመለከቱ ለሁሉም ጥቅም ያቀኑ መሆን የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ማሳሰቡና አክለውም የስደተኞች ጉዳይ አስደገፈውም፣ “ስደት ጥንታዊ የማህበራዊ ክስተት ነው ስለዚህ ችግሩ እንዲፈታ በሚገባ ማስተዳደር እንጂ ክስተቱን ለማፈን ያለመ የስደተኞች የመቆጣጠሪያ ደንብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘነ መሆኑ ገልጠው፣ ኅብረ ባህል ከመከባበርና ከመቀባበል ሕግን በማክበር የተሸኘ መሆን ይገባዋል እንጂ፣ ኅብረ ባህል የለም ብሎ መካድ ስሕተት መሆኑ የብፁዓን ጳጳሳቱ ጉባኤ እንዳመለከተና፣ ፖለቲካው ያገልግሎት ጥበብ መሆኑ የፖለቲካ አካላት መገንዘብ እንደሚኖርባቸውም” ጉባኤው እንዳሳሰበ ብፁዕ አቡነ ክሮቻታ አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.