2009-06-23 17:54:56

የቅዱስ ፓድረ ፕዮ አርአያነት


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶልስ ትናንት እሁድ ወድ ቅዱስ ፓድረ ፕርዮ አገር ወደ ሳን ጆባኒ ሮቶንዶ የአንድ ቀን ሓዋርያዊ ጉብኝት መፈጸማቸውን አመልክተን ነበር። RealAudioMP3

ቅዱስነታቸ ው በተጠቀሰው ሓዋርያዊ ጉብኝት የቅዱስ ፓድረ ፕዮ አስከሬን በክብር ብታቀበበት ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተው ጸሎተ-ኅሊና አሳርገዋል።

በቅዱስ ፕሮ ዘፒየትረልቺና ቤተ ክርስትያን ውስጥ ከሓምሳ ሺህ በላይ የሚገመቱ ምእመናን የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው ስብከት አሰምተዋል።

በቅዳሴው መጨረሻ መንፈሳዊ መልእክት አስተላልፈው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት መርተዋል፣ ከቀትር በኋላም ከካህናትና ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው ቃለ ምዕዳን ኣሰምተዋቸዋል። RealAudioMP3

በመጨረሻም ቅዱስ ፓድረ ፕዮ በመሠረቱት እና በአቋቋሙት ሆስፒታል ተገኝተው ለሕሙማንና ለሆስፒታሉ ሠራተኞች የሚያጥናናና የሚያበረታታ ንግግር አድርገዋል። RealAudioMP3








All the contents on this site are copyrighted ©.