2010-02-03 13:47:12

አፍሪቃ፣ የሰላም እና የደኅንነት ዓመት


እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. ለአፍሪቃ የሰላም እና የደኅንነት ዓመት ተብሎ እንዲሰየም የአፍሪቃ ህብረት ያቀረበው ውሳኔ በይፋ መጀመሩ ተገለጠ። የዚህ ውሳኔ አርማ የሆነው የችቦ ብርሃን ለማላዊ እና የወቅት የአፍሪቃ ኅብረት RealAudioMP3 ተረኛ ሊቀ መንበር ርእሰ ብሔር ቢንጉ ዋ ሙዛሪካ መረከቡ ሚስና የዜና አገልግሎት ሲያስታውቅ፣ በበአሉ ክንዋኔ ወቅት የአፍሪቃ ሕበረት ተጠሪዎች እንዳመለከቱት፣ ይህ ዓመት የአፍሪቃ ልማት እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በጦርነት በግጭት በድኽነት ለተጎዳው የአፍሪቃው ህዝብ ብሩህ ተስፋ የሚገለጥበት ዓመት እንዲሆን ማሳሰባቸውም ተገልጠዋል።

የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም እና የደህንነት ድርገት ተጠሪ ላማራ ራምታኔ በበዓሉ ስነ ሥርዓት ባሰሙት ንግግር፣ ጦርነት፣ በብዙ ሺሕ የሚገመት የአፍሪቃ ሕዝብ ለእልቂት ዳርገዋል፣ የአስከፊው የሰብአዊ ችግር መንስኤ፣ ልማትን የሚያሰናክል ነው በማለት 2010 ዓ.ም. አፍሪቃ ይህ የተጋረጠባት ችግር ለመወጣት የምትነቃበት ዓመት እንዲሆን ማሳሰባቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.