2010-02-05 13:38:29

በናይጀሪያ የመሪነት ሥልጣን ክፍተት


የናይጀሪ ርእሰ ብሔር ባደረባቸው የልብ ኅመም ምክንያት ባንድ በሳውዲ አራቢያ በሚገኘው ሆስፒታል እየታከሙ መሆናቸው ሲታወቅ፣ መሪው ለህክምና ከናይጀሪያ ከወጡበት ከባለፈው ዓመት ህዳር ወር ወዲህ በአገሪቱ RealAudioMP3 የርእሰ ብሔር ሥልጣን ክፍተት መፍጠሩ እና ይህ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ የጆስ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢግናቲዩስ ካይጋማ ከፊደስ የዜና አገልግሎት ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

ርእሰ ብሔር ኡማሩ ያር አድዋ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸው እንዲያስረክቡ አሊያም ሙሉ የሥልጣናቸው ኃላፊነት በጊዝያዊነት የርእሰ ብሔር ሥልጣን ክፍተት በመሸፈን ላይ ለሚገኙት ለምክትል ርእሰ ብሔር ጉድላክ ሆናዛን እንዲያዘዋውሩ ከተለያዩ የአገሪት የፖለቲካ አካላት እና ማኅበረሰብ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑም ፊደስ አክሎ አስታውቀዋል።

በጆስ ከተማ የተቀሰቀሰው ሁከት እንዲሁም እራሱን ሜንድ በሚል አህጽሮተ ቃል የሚጠራው የናይጀሪያ የደልታው ክልል ነጻ አውጪ ግንባር ከአገሪቱ መግንሥት ጋር የተደረሰው የቶክስ አቁም ስምምነት እንደማያከብረው በማሳወቁ፣ እነዚህ ተከስተው ያሉ ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ጉዳዮች ለመቆጣጥር እና መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ እና ለአገሩቱ ደህንነት ጽኑ ያመራር ውሳኔ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ተከስቶ ያለው የርእሰ ብሔር ሥልጣን ክፍተት ካልተወገደ በስተቀረ መፍትሔ ለማፈላለግ አስቸጋሪ እንደሚሆን የጠቀሱት የተለያዩ አበይት የአገሪቱ 17 እለታዊ ጋዜጦች በሕክምና ላይ የሚገኙት ርእሰ ብሔር ያር አድዋ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ይፋዊ ጥሪ ማስተላለፋቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።







All the contents on this site are copyrighted ©.