2010-02-05 13:37:19

አፍሪቃ ኅበረት፣ የሴቶች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ


በመላይቱ አፍሪቃ የሴቶች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲከበር እና ለዚህ እቅድ ገቢራውነት ለሚከናወኑት የተለያዩ የባህል የፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ እንቅስቃሴዎች ማስፈጸሚያ እና ሴቶች በተለያዩ መስክ RealAudioMP3 ለማነጽ ለሚወጠኑት እቅዶች ማስተግበሪያ የሚደገፍ ለሴቶች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ የአፍሪቃ ህብረት አንድ የገንዘብ ድርጅት ማቋቋሙ ተገልጠዋል።

የዚህ ህብረት አዲሱ ሊቀ መንበር የማላዊ ርእሰ ብሔር ቢንጉ ዋ ሙዛሪካ ይህ የአፍሪቃ ኅብረት ያነቃቃው እቅድ በሁሉም መስክ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ እና አለ ሴቶች ተሳትፎ የሚደረጉት እና የሚወጠኑት የተለያዩ የልማት የሕንጸት እቅዶች ሙላት እንደማይኖራቸው የሚመሰክር ነው፣ በአፍሪቃ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ማነቃቃት ማክበር እና ዋስትና መሰጠት እጅግ አስፈላጊ ነው እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ርእሰ ብሔር ሙዛሪካ ሁሉም የአፍሪቃ መሪዎች ይኸንን አዲሱ ስለ ሴቶች መብት እና ፈቃድ ማስተግበሪያ የተቋቋመው የገንዘብ ድርጅት በመደገፍ ለሴቶች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በሕግ ሂደት ዋስትና እንዲያሰጡት እ.ኤ.አ. በ 2003 ዓ.ም. ኅብረቱ በማፑቱ ያረቀቀው የውል ሰነድ በየአገሮቻቸው የሕዝብ ተወካዮች እና የሕግ መወሰኛ የበላይ ፍርድ ቤት አማካኝነት ያጸድቁት ዘንድ አደራ እንዳሉም ሚስና በመገልጥ፣ በቅርቡ የኅብረቱ መሪዎች በአዲስ አበባ ባካሄዱት ጉባኤ በኅብረቱ የሴቶች ተሳትፎ እና ሴቶች ለመሪነት ምርጫ ለማነቃቃት እና ለመደገፍ መስማማታቸው የዜናው አገልግሎት አክሎ አረጋግጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.