2010-06-07 14:20:53

አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. የቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በጳጦስ ከተማ መጀመራቸው ይላሉ የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ ቅዱሳት ጵውሎስ እና ባርናባስ ቆጵሮስ በመግባት ሐዋርያዊ ተልእኮአቸውን በጳጦስ ከተማ መጀመራቸው የሚያስታውስ፣ ጳጦስ በአስፍሆተ ወንጌል ታሪክ አቢይ ሥፍራ RealAudioMP3 ያላት መሆኑዋ የሚያሳስብ፣ ይኸንን ታሪክ የሚያስታውስ፣ አስፍሆተ ወንጌል በቆጥሮስ ያለውን ታሪካዊ ሂደቱን የሚዳስስ ነው። ይኽ ደግሞ የቆጵሮስ ርእሰ ብሔር፣ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ክርይሶስቶሞስ እና ቅዱስ አብታችን ያስታወሱት ታሪክ መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን በቅድስት መሬት ቀጥሎም በማልታ አሁንም በቆጥሮስ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ የቅዱስ ጳውሎስ የኢዮቤል ዓመት አቢይ ትኩረት የሰጠ መሆኑ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ለክርስትያን አንድነት ያሳየው የሐዋርያዊ ተልእኮ ጥረት መርህ በማድረግ በሁሉም በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ውህደት እንዲረጋገጥ የጠራ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው ብለዋል።

ይኽንን በመከተልም በቅዱስ ኤጂዲዮ የሚጠራው የካቶሊክ እንቅስቃሴ እንዲሁም የተለያዩ የአቢያተ ክርስትያን የጋራው ድርገት ለክርትያኖች አንድነት የተለያዩ ግኑኝነቶች እንዲከናወኑ ያነቃቃ መሆኑም ገልጠዋል።

ቆጵሮስ ምዕራቡን እና ምሥራቁን አለም የምታገናኝ ድልድይ መሆንዋ ያረጋገጠ ጥሪ መሆኑ ያብራራ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው በማለት፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. በቫቲካን ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የመካከለኛ ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በይፋ ያሳወቀ የሲኖዶሱ ዓላማ ያበሠረ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው፣ ስለዚህ በኤውሮጳ ባህል ውስጥ ያለው ምሥራቃዊነት ባህል ያስተዋወቀ እና ይኸንን ባህል አቢይ ግምት የሰጠ ጉብኝት ነው ብለዋል።

የተካሄደው ሐዋርያዊ ጉብኝቱ የተዋጣለት መሆኑ አብራርተው፣ በአንድ ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያካሄዱት ሦስት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ስኬታማ መሆኑ ገልጠዋል። በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል የሚደረገውን የጋራው ውይይት አቢይ ግምት የሰጠ ጉብኝት ነው ብለዋል። በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና በብፁዕ ሊቀ ጳጳሳት ክርይሶስቶሞስ መካከል የተካሄደው ግኑኝነት እንደሚመሰክረውም አብራርተው፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ የቱርክ ማኅበረ ክርስትያን እና ውሉደ ክህነት ወክለው ይገኛሉ ተብለው ሲጠበቁ በሰው እጅ የተገደሉት ብፁዕ አቡነ ፓዶቨሰ ትልቅ ሐዘን ማስከተሉ አብራርተው፣ በቱርክ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ወክሎ የተገኘ አለ መኖሩ ጠቅሰው ለዚህች ቤተ ክርስያን አቢይ ጸሎት እንዲደረግ እና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ግኑኝነት በበለጠ ጥረት እንዲቀጥል ያሳሰበ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.