2010-12-06 15:58:13

የወርኃ ታኅሣሥ የር.ሊ.ጳ የጸሎት ሐሳብ


ሁል ግዜ በየወሩ እንደሚደረገው የወርኃ ታሕሣሥ የር.ሊ.ጳ. የጸሎት ሐሳብ ‘ብቻቸውን ስለሚኖሩት ሕመምተኞችና አዛውንቶች’ ነው፣ በሕይወታችን የሚያጋጥመን የሥቃይ ተመኵሮ በሕመምና በእርጅና ብቻቸውን የሚኖሩ ሰዎች የሚያሳልፉት የተስፋ መቍረጥና የሥቃይ ስሜት እንድረዳ በመርዳት በለጋስነት እንድንረዳቸው ይርዳን ዘንድ እንጸልይ፣ ይላል።
ቅዱነታቸው ስለ ሥቃይ በተለያዩ ግዝያት ተናግረዋል፣ በተለይም በተስፋ ድነናል በሚለው ሐዋርያዊ መልእክታቸው በሕይወታችን የሚያጋጥመንን መስቀል በብርታትና በትዕግሥት እንድንሸከመው ኣሳስበው ነበር። ሥቃይ ልዩ የፍቅር ተመኵሮ ሊሆን እንድሚችልም ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.