2011-09-14 14:58:07

የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ጉባኤ፥ “በጋራ መኖር ዕጣ ፈንታ ነው”


የዛሬ 25 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መልካም ፈቃድ መሠረት በአሲዚ በተለያዩ ኃይማኖቶች ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በአማኞች መካከልም ጭምር መቀራረብ መተዋወቅ እንዲኖር ያበረታታው ነቢያዊ መርሃ ግብር ፈር በማድረግ ሁሌ በየዓመቱ የቅዱስ ኤጂዲያ እንቅስቃሴ የሚያዘጋጀው የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖች የባህል የፖለቲካ አካላት እና የመንግሥታት RealAudioMP3 ልኡካን ጭምር የሚሳተፉበት የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋራ ውይይት መርሃ ግብር መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ይኽ የተካሄደው እና ትላንትና ጧት የተጠናቀቀው የሦስት ቀናት የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራው ጉባኤ በማስመልከት የሙዩኒክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ራይንሃርድ ማርክስ እና የቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ እንቅስቃሴ መሥራች የሥነ ታሪክ ሊቅ በጉባኤው ንግግር ያሰሙት ፕሮፈሶር አንድረያ ሪካርዲ በሰጡት የጋራ መግለጫ በመግለጥ፣ በጋራ የመኖር ጥበብ የኅብረተሰብ ጥሪ ነው። ተወደደም ተጠላም የጉባኤ ርእስ እንደሚያመለክተውም በጋራ መኖር ዕጣ ፈንታ ነው ብለዋል።

ተገናኝቶ በጋራ መወያየት እና መጸለይ ከመቅጽበት ታሪክን ይለውጣል ማለት አይደለም፣ ስለዚህ ሕዝቦችን ለማገናኘት እና ለማቀራረብ ቅርጸ ምድራዊ ትዕግሥት ይጠቃል ካሉ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. አሸባሪያን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ያወረዱት አሰቃቂው የሽበራ ጥቃት ኅብረ ባህላዊ እና ኅብረ ሃይማኖታዎ የጋራው ውይይት ውድቅ መሆኑ ያረጋገጠ ተግባር ነው ተብሎ እንዲንገረ ያደረገ ቢሆንም ስህተት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። በ 1986 ዓ.ም. የተጀመረው 25ኛው ዓመት የዘከረው ኅብረ ሃይማኖታዊ የጋራው ውይይት እና ግኑኝነት፣ 25 ዓመት በዓለም ታሪክ ውስጥ በውቅያኖስ እንደ የአንድ ወተት ጠብታ ነው። ሆኖም ግን የጋራው ውይይት በተለያየ መልኩ በባህል በሃይማኖት በመንግሥታት በጠቅላላ በተለያየ ዘርፍ እርሱም ዓለም አቀፋዊ ቅርጽ ባለው ደረጃ በማከናወን ሁሉም በውይይት የሚያምን እንዲሆንና በየዓመቱ ብቻ ሳይሆን ዕለት በዕለት የውይይት ባህል የሚዘራ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት “እግዚኣብሔር እንደ የግል ንብረት አለ ማሰብ፣ ኃይማኖት የሰላም ኃይል መሆኑ ያረጋግጥልና” በማለት የሰው ልጅ በጋራ ለመኖር የተጠራ መሆኑ አሳስበው ሁሉም ይኸንን እንዲገነዝብ በየዓመቱ የሚካሄድ የሁሉም ኃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሚመሰክረው ነው ሲሉ፣ የሚዩኒክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ማርክስ በበኩላቸውም፣ ክርስትያኖች ዓለምን እንደሚለጡ አልጠራጠርም፣ ሆኖም ግን ይህ እቅድ በፖለቲካው አመለካከት አጭር የቅርብ እቅድ ሳይሆን እያንዳንዱ ሰው አመለካከቱን መለወጥ የእርስ በእርስ መረዳዳት ተገናኝ ባኅርይ በትክክል መኖር በተሰኙት እቅዶች መሠረት ቀስ እያለ እውን የሚሆን ነው ካሉ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ወዲህ በራስ የመዘጋት፣ ሌላው ከእኔ ከተለየው ጋር ለመገናኘት አስፈሪ እየሆነ በሰው ዘር መካከል ጠቅላላ ሁኔታውን ያካተተ ተጠራጣሪነት እንዲስፋፋ ያደረገ ቢመስልም ቅሉ፣ የዚህ ዓይነቱ ግኑኝነት እንዱ ለሌላው ሥጋት እንዳልሆነ በመመስከር ሰላም የሚቻል መሆኑ የሚያስገነዝብ እና ሁሉም ለዚህ የሚያንጽ የጋራ ግኑኝነት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ ያስተላለፉት ዘገባ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋራው የውይይት ጉባኤ የተሳተፉት በኢጣልያ የናፖሊ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ክረሸንዚዮ ሰፐ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሰው ልጅ ልክ እንደ አንድ ደሴት ለገዛ እራሱ የተፈጠረ ወይንም በገዛ እራሱ ውስጥ የታጎረ ሳይሆን፣ ለሌላ ክፍት የሆነ ፍጡር ነው። በሰው ዘር መካከል ወንድማማችነት ምርጫ ሳይሆን የመሆናችን ባህርያዊ ግፊት ነው። ስለዚህ ይኽንን ከእግዚአብሔር የታደለን የመሆናቸው አድማስ ከኖርን እና በተለያየ መልኩ እንዲጎላ ካደረግን፣ ሁሉም ወዳጅ እንጂ ማንም የማንም ጠላት ሊሆን አይችል። ክርስትና ይኸንን ነው የሚያስተምረን። ሆኖም ግን በዓለማችን የሚታዩት ሰብአዊ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች የመከፋፈል ሕግ የሚያስፋፋ ተመስሎ ቢገኝም፣ ሁሉም ኃይማኖቶች ይኸንን ተገንዝበው በጋራ ለመኖር የተጠራን መሆናችን በማበከር እና በማስተማር ሰላም እንዲነግሥ በማድረጉ ረገድ በበለጠ መትጋት ይኖርባቸዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.