2011-11-14 13:59:46

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ በሽል ላይ የሚደረግ ሥነ ምርምር የሞት ባህል ነው


በቫቲካን ዓለም አቀፍ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ላይ ያተኮረ፣ ሥነ ምርምር፣ የሰው ልጅ መጻኢና ባህል በሚል ርእስ ሥር የተመራ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የሕይወት ግንድ ለሕይወት የተሰየመው ማኅበር በጋራ ያዘጋጁት፣ ባለፈው RealAudioMP3 ሳምነት የተካሄደው የሦስት ቀናት ዓወደ ጥናት በማስመለከት የዚህ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተካሄደው ዓወደ ጥናት የተዋጣለት እንደነበር ጠቅሰው፣ ሥርወ ሕይወት ሕዋስ ወይም የሕይወት ግንድ የሚመለከተው ጥያቄ የሥነ ሕክምና ጉዳይ ወይም የሥነ ሕይወት ብሎም የግብረአዊነት ጥያቄ ብቻ እንዳልሆነ የተመሠከረበትና እንዲሁም ጥያቄው ፈጽሞ ከሥነ አካል ጉዳይ ጋር ብቻ ከሚለው አመለካከት ልቆ የሚሄድ ሰፊ እና የተወሳሰበ ጥያቄ መሆኑ የተብራራበት ነበር ብለዋል።
በሥነ ምርምር ረገድ በሥርወ ሕይወት ሕዋስ ወይንም የሕይወት ግንድ መሠረት የሚደረገው ጥናት እና ምርምር በተለይ ደግሞ የጎልማሳ ሕዋስ ጥንተ ክፍለ አካል ወይንም ሥርወ ሕይወት ሕዋስ የሰውን ልጅ እጅግ የሚያሰቃየው የተለያየ ቀስ በቀስ የሚያመክነው በሽታ የመሳሰሉት እንዱሁም መድሃኒት ገና ያልተገኘላቸው በሽታዎች ጭምር ብቸኛና በተለይ ደግሞ በሽል ላይ የሚደረገ ሥነ ምርምር መሠረታዊ መፍትሔ ይሆናል የሚለው አፈ ታርክ ምን ያክል መሠረት እንዳለው እና በተለይ ደግሞ ይህ በሥርወ ሕይወት ሕዋስ ወይንም የሕይወት ግንድ ላይ የሚደረገው ሥነ ምርምር ለተለያዩ ከባድ በሽታዎች ፈውስ ያስገኛል የሚለው በተለያየ ዘርፍ የሚቀርበው አስተያየት የገመገመ ዓውደ ጥናት እንደነበር ገልጠዋል። አለ ምንም ሥነ ምግባራዊ ችግር በቀጥታ በሥርወ ሕይወት ሕዋስ ወይንም የሕይወት ግንድ መሠረት የሚደረገው ምርምር እርሱም ከደም ከቅልጥም ከሚገኘው ሥርወ ሕይወት ሕዋስ አማካኝነት ሥነ ምርምሩ ማፋጠን ይቻላል ስለዚህ ሽል ለዚህ ዓይነት የምርምር ሂደት ለሞት መዳረገ የሞት ባህል ነው ካሉ በኋላ ይህ የሥነ ምርምር ሂደት የሥነ ሕይወት እና የሥነ ምግባር ጉዳይ የሚመለከት ነው። ሕዝብ የሥነ ምርምር ጉዳይ ቀለል ባለ መንገድ እንዲረዳው እና ግንዛቤውም ጭምር እንዲኖረው ለመደገፍ፣ ምርምሩ በተማራማሪዎች የሥነ ሕክምና ሊቅ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ያሳሰበ፣ በሌላው ረገድም በሥነ ምርምር ሥነ ሕክምና ፍልስፍና እና ቲዮሎጊያ መካከል ውይይት እንዲኖር የሚል ራእይ ያደረገ ዓወደ ጥናት ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.