2012-03-05 13:10:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ብዙ ጊዜ ሕይወት ጨለማ መሿለኪያ ነው። ብርኃን የሚያገኘው በእግዚአብሔር ላይ ከሚጸናው እምነት ነው”።


በኪንሻሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞንሰንግዎ ፓሲንያ የተመራው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና የቅርብ ተባባሪዎች የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ መሥተዳድር ዓበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች እና ብፁዓን ጳጳሳት የተሳተፉበት በቫቲካን የተካሄደው የአንድ ሳምንት ሱባኤ ቅዳሜ ጧት RealAudioMP3 መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው በሱባኤው ፍጻሜ የተካሄደው የሳምንት ሱባኤ ሂደት ዝርዝር መግለጫ መሠረት ባሰሙት ቃል፣ በቅድሚያ ሱባኤውን የመሩት ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞንሰንግዎ ፓሲንያ በስማቸው እና በቅርብ ተባባሪዎቻቸው የእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን የበላይ አካላት ብፁዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ስም አመስግነው፣ ውኅደት ከእግዚአብሔር ጋር ምን ማለት መሆኑ ለማብራራት ለመጸለይ እና ለማስተንተን በመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የዮሐንስ መልእክት ቃል መሠረት ቅርጽ ይዞ የተመራው የአቢይ ጾም ሱባኤ፣ በሥነ ትንተና ባላቸው በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና የመንፈሳዋዊነት ተመክሮ ተደግፈው የሰጡት የአስተንትኖ ስብከት ወደ እግዚአብሐር አጥብቆ የተመለከተ በመሆኑ በዚህ ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ በሚመለከተው እይታች አማካኝነት ውህደት የሚያረጋገጠው ፍቅር በጥልቅ ማብራራታቸውንም አመስግነው፣ ፍቅር ተምረናል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ፣ አክሎ ብፁዕ ካርዲናል ሞንሰንግዎ ፓሲንያ አንድ ባደረባቸው ሕመም ሳቢያ የአልጋ ቁራኛ ሆነው በኅሊና መሳት ደረጃ የሚገኙትን የቅርብ ወዳጃችውን በማስታወስ ሕይወት ጨለማ መሿለኪያ ቢመስልም የብርሃን ጭላንጭል አርቆ የሚያይ ውበትን የሚያዳምጥ መሆኑ ባላቸው ተመክሮ በማረጋገጥ፣ ባሰሙት ስብከት ያብራሩትን ሃሳብ ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፣ ብዙው ጊዜ በድቅድቅ ጭለማ ያለን ሆኖ ቢሰማንም እና በጨለመ መሿለኪያ ብንገኝም በእምነት ብርሃንን ለማየት እንደሚቻልና ጥኡም የመዝሙር ቅኝት በማዳመጥ የእግዚአብሔር ውበት፣ እግዚአብሔር የፈጠረው ሰማይና ምድርን ሰውን ልጅ እንገነስዘባለን፣ እምነት ከእግዚአብሔር ለሚገኘው ብርሃን ምስክር ነው እንዳሉ ያመለክታል።
ብፁዕነታቸው ምንም’ኳ የአፍሪቃ ባህል ልጅ ቢሆኑም በባህል ያለው ልዩነት የክርስቶስ ምሥጢረ አካል ላይ ያለው ውህደት የማይነካ መሆኑ ባቀረቡት የሳምንት የአስተንትኖ ስብከት የሰጡት ማረጋገጫ እውነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን የቤተ ክርስትያን አካል በአጋጣሚ ልዩነቶች የሚነካ አይደለም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.